Thursday, January 1, 2015

ለምን ወለድናቸው?። – ዳዊት ዳባ።

ze-habesha

  • 248
     
    Share
ፖሊስ የደብረ ማርቆስ ተማሪዎችን እየደበደበ ነው፡፡ የትናንትናው ተቃውሞ በኢሳትና በሌሎች ሚዲያዎች መተላለፉን ተከትሎ ‹‹ማን ነው ከኢሳትና ከሌሎች ሚዲያዎች ጋር እየተደዋወለ መረጃ የሚሰጠው?›› እንዲሁም ‹‹የተቃዋሚ ፓርቲ አባል ካለ ተናገሩ›› በሚል ተማሪዎቹን አሳልፈው እንዲሰጡ ከፍተኛ ደብደባ እየፈጸመ መሆኑን ከቦታው የደረሰን መረጃ ይጠቁማል፡፡ ፖሊስ አሁንም ተማሪዎችን እየፈለገ እያሰረ መሆኑም ተገልጾአል ይላል የዛሬ ዋና ዜና።
deberemarcos-7ለምን ለሚልና ላልሰማ። ወያኔዎች አንድ ቀን ቀደም ብሎ ‹‹የአብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠና በደብረማርቆስ የመለስተኛ ሁለተኛ እና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ (መሰናዶ) ተማሪዎች መስጠት ጀመሩ። ክርክሩን በኢሳት ራዲዬ የሰማን በሙሉ ምስክር ልንሆን በምንችልበት  ህፃናቱ  በሀሳብ  ሞግተው ግልፅ ሆኖ በሚታይ ሁኔታ የስርአቱን ካድሬዎች አሸነፏቸው። ያነሷቸው ጥያቄዎችና መከራከሪያዎች ፍፁም እውነትነት ያላቸው፤ ብስለት የተሞላባቸውና ስክን ባለ ሁኔታ የሚቀርቡ ነበሩ። አይደለም ተራ ካድሬዎች አውራዎቹም ቢመጡም የሚቋቋሟቸው እንዳልሆነ ላዳመጠው ሁሉ ግልፅ ነበረ።  ካድሬዎቹ  ለጊዜው   እንደ መፍትሄ አድርገው በተለመደው የመከፋፈል ዘይቤ ህፃናቱ ይሰለጥኑበት ከነበረው ሰፊ አዳራሽ ወጥተው 20፣ 20 ሆነው በጠባብ ክፍል እንዲሰለጥኑ በማድረግና ጥያቄ የሚያነሱትን በማስፈራራት ሊወጡት ሞከሩ። ህፃናቱ  በዚህም የሚሸነፉ አልሆኑም ማለት ነው። ይህው በሚቀጥለው ቀን ወያኔዎች ወደሀይል እርምጃ መግባታቸውን የሚያሳይ ከላይ የተቀመጠውን አሳፈሪም አሳፋሪም ዜና ሰማን።
እነዚህ ልጆች ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ታዳጊ ህጻናት ናቸው። ወዲያም አደረግነው ወዲህ ደህንነታቸው በዋናነት በቤተሰብና በማህበረሰቡ ሀላፊነት ላይ ነው ገና ያለው። ጥቃት እየፈፀመባቸው ያለው አካል ስራው ደህንነታቸውን መጠበቅ ይገባቸው ከነበሩት አንዱ  “መንግስት” ተብዬው ነው። ይህ አካል ሁላችንንም እየቀጠቀጠ እየገዛ ያለና አሁንም ቤተሰብ ለምን ቢል ጥቃት ከመሰንዘር የማይመለስ መሆኑ ቢታወቅም።  በአጠቃላይ እጅግ ግዙፍ የሆነ ባላንጣ  ቢሆንም። እነዚህ ልጆች ለብቻቸው መተው ግን በጭራሽ የለባቸውም።ቤተሰብም ማህበረሰቡም ዝም ብሎ ይህንን ህፃናት ልጆቹ ላይ የሚፈፀም ወንጀል መመልከት የለበትም።  እጅጉኑ  ዝም ልንለው ከሚገባው በላይ ያለፈም ነው።
ህፃናቱን ምን አድርጉ ነው የሚላቸው። 90%የሚሆኑት ለመምረጥ ገና እድሜያቸው አልደረሰም። ምረጡኝን ምን አመጣው። በጣም ከጥቂቶች በቀር አስራ ስምንት አመት ገና ያልሞላቸው አማካኝ እድሜያቸው አስራ ስድስት አመት አካባቢ የሆኑ ታዳጊ ህፃናት ናቸው። የትኛውንስ ርእዬት አለም  ለማጥመቅም ሆነ ተከታዬ ሁኑ ለማለት ቤተሰቦቻቸውን አስፈቅዷል ወይ?። ተጠይቀንስ ፈቅደናል ወይ?። ይህም ሆኖ መታወቅ ያለበት ለአቅመ አዳም ለደረስነውም   ማስገደድ ከባድ  ወንጀል ነው።  ህፃናትን አስገድዶ ተከታዬ ሁኑ፤ አስገድዶ ምረጡኝ ማለት አስገድዶ ከመድፈር በምንድን ነው የሚለየው?። ይህ አላንስ ብሎ መደብደብ፤ ማሰር፤ ትምህርታቸውን ማስተጓጎል፤ ማሸበርንስ ምን የሚሉት?፤ ማን አለብኝነትስ ነው?። እንዴትስ ነው ይህ ዝም ተብሎ የሚታየው?። ለልጆቹስ ይወጡት ተብሎ የሚተወው።
ልጅ እያለው የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ሲለቀቁ እየጠበቅን ቾክ እንለምን ነበር። ልጅ ስለነበርኩም ይሆናል ተማሪዎቹ ጠብደል ጠብደል ያሉ፤ በስርአቱ የለበሱና ጥንድ ጥንድ ሆነው የሚሄዱ ጎልማሶች ነበሩ።  እኔ ሁለተኛ ደረጃ ስደርስ እንደጠበኩት አልነበረም። ገና ፔፕሲ፤ ሱዚና ሌባና ፖሊስ እረፍት ላይ ቅልጥ አድርገው የሚጫወቱ ነበሩ። አሁን ደግሞ ልጆቼ ናቸው። አውቃለው በእርግጠኛነት በጣም በለጋ እድሜ ያሉ ታዳጊ ህፃናት ናቸው። በዛ ላይ ገና አስረኛ ክፍል ያልደረሱ።

No comments:

Post a Comment