ትላንት ህይወቱን ከባእዳን ጥቃት ለመታደግ ሰንደቃላማው ወደ ተሰቀለበት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ የኮንቴነር መጠለያ በገቡ እህቶቻችን ላይ ግፍ እና በደል ሲፈጽሙ የኖሩት በሪያድ የኢትዮጵያ መንግስት ዲፕሎማቶች በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ወገኖቻችንን መርጃ በሚል ሽፋን ዶላርና ሪያል መሰብሰባቸውን አጠናክረው መቀጠላቸውን ማረጋገጥ ተችሎሏል።
በሪያድ እና አካባቢው ማህበረሰብ የሚወገዙ እነዚህ የኢትዮጵያ መንግስት ዲፕሎማቶች ዛሬ መፉሃ ውስጥ ለተከሰተው እና ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ላለው ግፍ እና ስቃይ በቀጥታ መጠየቅ የሚገባቸው እና ከወገኖቻችን ስቃይ ይልቅ በወገኖቻችን ህይወት ለከበሩ የሰራተኛ እና ሰሪ አገናኝ ኤጀንሲ ባለቤት ለሆኑ የአረብ ደላላዎች ጥብቅና የቆሙ ወንጀለኞች መሆናቸውን የሚገልጹ ምንጮች ቀደም ሲል ወደ ኮሚኒትው መጠለያ ገብተው ከነብሩ እህቶቻችን መሃከል ለ3ቱ ሞት ተጠያቂ መሆናቸውን በማስረጃ አስደግፈው ምሬታቸውን ይገልጻሉ ።
በሳዲ አረቢያ የኢትዮጵያው ሰም አንባሳደር መሃመድ ሃሰን እና ዲፕሎማቱ ለእህቶቻችን ስቃይ እና መከራ ዴንታ የሌላቸው ከመሆናቸውም በላይ በተለያዩ ወቅቶች በአሰሪዎቻችን ተበድለናል ድረሱልን አጋር ሁኑንን ብለው ብሶውታቸውን ሊያሰሙ ወደ ኤንባሲ የመጡ እቶቻችን ሰበአዊ ክብር በሚንኩ ቃላቶች ሲሳድቡ ሲያዋርዱ የነብሩ መሆናቸውን በማስታወስ እንዚህ ዲፕሎማቶች ዛሬ ለህዝብ አዛኝ እና ተቅርቋሪ መስለው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ት/ቤት በሚገኙ ተላላኪዎቻቸው አማካኝነት ባዋቀሩት ኮሚቴ ከእስት ወደ ረመጥ። በተዘፈቁ ወገኖቻችንን ስም ህዝብን ለመመዝበር እያደረጉ ያለው እሩጫ በምንም ማመዛኛ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ይናገራሉ።
በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች እንደተቋቋመ የሚነገርለት ይህ የእርዳታ አሰባሳቢ ኮሚቴ ቀደም ሲል በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ ውስጥ የሚገኙ የነበሩ 12 ነስፈስ ጡሮችን ጨምሮ ከ 200 የሚበልጡ ወገኖቻችን ከስቃይ እና መከራ በማዳን በሚል ሽፋን « የአይሮፕላን » ትኬት መግዣ ቀደም ብሎ 1 መቶሺህ ሪያል አሊያም ግማሽ ሚልዮን ብር መሰብሰቡን በማውሳት የገበያ ግርግር ለምን ያመቻል እንዲሉ የመንፉሃውን ሁከት ተከትሎ ዲፕሎማቱ እህቶቻችን ከኮሚኒተ ግቢ በአውቶብስ አስጭነው እስካሁን በውል ወዳልታወቀ የሳውዲ መግስት ወዳ ዘጋጀው ጊዘያዊ መጠለያ ጣቢያ ወስደወ በመጣል የተጠቀሰውን ግንዘብ ዲፕሎማቱ የት እንዳደርሱት እንደማይታወቅ የሚናገሩ ምንጮች በወገኖቻችን ስም የሚደረግውን የማጭበርበር ተግባር ህዝቡ ከወዲሁ መቃወም ማክሸፍ እንድሚገባው አብክረው ገልጸዋል።
Ethiopian Hagere ሳውዲ አረቢያ ጅዳ በዋዲ