Saturday, October 18, 2014

በአፍሪካ የልማት እና የመዋዕለ ንዋይ ፍሰትን ሚስጥር ሀሰትነት ማጋለጥ፣ ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም


October 18,2014
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

በአፍሪካ የአሜሪካ መዋዕለ ንዋይ ፍሰት ሚስጥር፡ “በሚቀጥለው ትውልድ ላይ መዋዕለ ንዋይማፍሰስ“    
ባለፈው ሳምንት በዋሽንግተን ዲሲ በጣም የተጋነነ የዩኤስ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ፌሽታ ነበር፡፡ ሁሉም ነገር “በጣም ፈጣን እድገት እያስመዘገበ ስላለው አህጉር፣ በወጣት ትውልድ ስለተሞላው እና ከፍተኛ የሆነ መዋዕለ ንዋይ እየፈሰሰበት ስላለው“ የአፍሪካ አህጉር ነበር፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ እና ሌሎች ቁንጮ የዩኤስ ባለስልጣናት ይፋ ባልሆነ መልኩ “የአፍሪካ መነሳሳት የሚለውን ተራኪ ሙዚቃ“ ዘምረዋል፡፡ የዩኤስ አሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  የሆኑት ጆን ኬሪም ዉዳሴአቸዉን ዘምረዋል፡፡ እንዲህ የሚል ንግግርም አሰምተዋል፣ “በዓለም ላይ በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ ካሉት 15 አገሮች መካከል 10ሩ የሚገኙት በአፍሪካ ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ2040 አፍሪካ ከህንድ ወይም ከቻይና የበለጠ የሰራተኛ ኃይል ይኖራታል፡፡“ የቀድሞው የኒዮርክ ከተማ ከንቲባ ሚካኤል ብሉምበርግ እና የዩናይትድ ስቴትስ የንግድ ምክር ቤት ጸሐፊ የነበሩት ፔኒ ሪዝገር በፎርበስ ከተማ በመገኘት “የአፍሪካ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት/GDP በሚቀጥሉት አስር ዓመታት በአማካይ በየዓመቱ 6 በመቶ እድገት እንደሚያስመዘግብ ይጠበቃል“ በማለት የብርሀን ሻማቸውን በመለኮስ የፈንጠዝያ መዝሙራቸውን ለማሰማት ፊሽካ ነፍተው ነበር፡፡ በድልአድራጊነት የሚከተለውን አወጁ፣ “የተጣራ ገቢ/Real Income ባለፉት አስር ዓመታት ውስጥ ከ30% በላይ እድገት አሳይቷል፡፡ ብዙዎቹ የአፍሪካ መንግስታት በመሰረተ ልማት፣ በትምህርት እና የብዙዎችን ህይወት በሚያሻሽሉ የጤና አጠባበቅ ልማቶች ላይ ከፍተኛ የሆነ መዋዕለ ንዋይ አፍስሰዋል“ ብለዋል፡፡ በመቀጠልም “የዩኤስ አሜሪካ ኩባንያዎች በአፍሪካ ላይ እያፈሰሱት ያለው መዋዕለ ንዋይ አሁንም በጣም ዝቅተኛ በሆነ ደረጃ ላይ ይገኛል“ በማለት ያደረባቸውን ጸጸት ገልጸዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ኦባማ “በአፍሪካ ያለውን የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት አናሳነት” በማስመልከት እንደመፍተሄ ብለው ያቀረቡት ዩናይትድ ስቴትስ ያፍሪካ ቁርጠኛ የልማት አጋር፣ በእኩልነት መርሆ እና በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ዓላማን እንደምታራምድ እንዲሁም ለአፍሪካ የረዥም ጊዜ ስኬት አጋርነቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል አጽንኦ በመስጠት ንግግር አድርገዋል፡፡ የፕሬዚዳንቱ የልማት አጋርነት ንግግር ትንሽ ግራ የሚያጋባ ሆኖም ግን ግልጽ እና አጭር በሆነ መልኩ እንደሚከተለው ቀርቧል፣
በዚህ ጉባኤ ላይ በመገኘቴ ከፍተኛ የሆነ ደስታ የተሰማኝ መሆኑን አየገለጽኩ በአሜሪካ የሚገኙ ኩባንያዎች ሁሉ በአፍሪካ ውስጥ መዋዕለ ንዋያቸውን በማፍሰስ ለአፍሪካ የልማት ዕድገት ጠንካራ አጋር ለመሆን ቁርጠኝነት ያላቸው መሆናቸውን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ ብለዋል፡፡ ጥቁር ድንጋይ/Blackstone በአፍሪካ የኃይል ፕሮጀክቶች ላይ መዋዕለ ንዋይ ያፈስሳል፡፡ ኮካኮላ የተባለው ኩባንያ ለህብረተሰቡ ንጹህ ውኃ ለማቅረብ ከአፍሪካ ጋር የአጋርነት ስራን ይሰራል፡፡ ጂኢ/ GE የተባለው ኩባንያ የአፍሪካን መሰረተ ልማት በመገንባት ተግባራት ላይ እገዛ ያደርጋል፡፡ ሁሉም በግልጽ ተነግሯል፣ የአሜሪካ ኩባንያዎች አብዛኞቹ ከእኛ የንግድ ድጋፍ በንጹህ የኃይል አቅርቦት፣ በአቬሽን፣ በባንክ ስራ እና በግንባታ ስራዎች ከ14 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ የሚያወጡ የልማት ስራዎች በአፍሪካ ለማፍሰስ እና በርካታ ሸቀጦችን “በአሜሪካ የተሰራ” በማለት ማህተም እያተሙ ሸቀጦቻቸውን መቸብቸብ ነው፡፡
ምናልባትም የፕሬዚዳንቱ ጋዜጣዊ መግለጫ “እውነትን በማስተዋወቅ” እረገድ መጠነኛ ጠቀሜታን አሳይቷል፡፡ ኮካኮላ የተባለው ኩባንያ 5 ቢሊዮን ዶላር በማኑፋክቸሪንግ የምርት መስመሮች እና በመሳሪያዎች ላይ መዋለ ንዋይ በማፍሰስ ላልተገባ ውፍረት የሚዳርገውን በአፍሪካ ብዙ የስኳር ሶዳ እያመረተ ትርፉን በማግበስበስ የዜጎችን ጤንነት የሚጎዳ ምርት ከማምረት ውጭ ለይስሙላ የሚደሰኮረውን የአፍሪካን ህዝብ ንጹህ ውኃ ለማጠጣት አይደለም፡፡ (በተመሳሳይ መልኩ ስለአር/R ለማወቅ በጣም ተስፋ ቆርጫለሁ፡፡ ጀ ሬኖልድ የተባለው የትምባሆ ኩባንያ በአፍሪካ ምንም ዓይነት መዋዕለ ንዋይ እያፈሰሰ አይደለም፡፡ የአንድን አሮጌ የኮኬይን የማስታወቂያ መፈክር አባባል በመውሰድ “ኮኬይን እንደ ዊንስተን ቆንጆ ነው፡፡ (ለጤንነት  ሲጋራና ኮካ ኮላ ትርፋቸው አንድ ነው።) “ ጥቁር ድንጋይ/Blackstone ኤልፒ/LP የተባለው  ቡድን ከዓለም ትልቁ ጠቅላይ የሞኖፖል ወለድ ድርጅት በአፍሪካ የኃይል ፕሮጀክቶች ላይ 3 ሚሊዮን ያህል ዋጋ ያለው መዋዕለ ንዋይ ለማፍሰስ ዕቅድ በማውጣት ለመጀመር በዝግጅት ላይ ነው፡፡ ጀኔራል ኤሌክትሪክ የተባለው ኩባንያ እ.ኤ.አ በ2018 ሁለት ቢሊዮን ዶላር መዋዕለ ንዋይ በተለይ “በልማት ፋሲሊቲ፣ በክህሎት ስልጠና እና ለዘለቄታዊ ተነሳሽነት“ ለማፍሰስ ዕቅድ ይዟል፡፡ ማሪኦት ኢንትርናሽናል ኢንክ/Marriot International, Inc 36 አዲስ ሆቴሎችን ለመክፈት እና 10 ሺህ አዲስ ሰራተኞችን እ.ኤ.አ በ2020 በመቅጠር ስርጭቱን ወደ 16 አገሮች በማድረስ 200 ሚሊዮን ዶላር መዋዕለ ንዋይ ለማፍሰስ ዕቅድ ይዟል፡፡ የጋናን የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት በተለይም በቀጣዮቹ 5 ዓመታት IBM በባንክ 66 ሚሊዮን ዶላር ክፍያ ይፈጸማል፡፡ 
የአፍሪካ “የልማት” ሚስጥር፡ የሚያብረቀርቅ ነገር ሁሉ ወርቅ አይደለም፣
እ.ኤ.አ በ2013 ሪክ ሮውደን “የአፍሪካ መነሳሳት ሚስጥር“ በሚል ርዕስ ታይም እና ዘ ኢኮኖሚስት የተባሉት መጽሔቶች በቀጣዮቹ ዓመታት የአፍሪካ አህጉር ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ኃይል ይሆናል በማለት በውጭ ፖሊሲ ላይ በድረ ገጽ ያቀረቡትን ሰፊ ዘገባ ጠንካር ያለ  ትችት አቅርበውበታል፡፡ ሮውደን በግልጽ እንዳስቀመጡት የአፍሪካ አስደናቂ ልማት የተሳሳተ እንደሆነ እና በዚህ በዓለም አቀፋዊነት ዘመን የአገሮች የኢኮኖሚ ልማት በችግግር የተተበተበ መሆኑ ግንዛቤ ሊወሰድበት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
ሮውደን የአፍሪካ ልማቶች አሳሳች መሆናቸውን እና ልማቶች በምን ዓይነት መልክ እተካሄደ እንዳለ እና የልማት መለኪያዎችን በአሃዛዊ መስፈርት ለማስቀመጥ ባለው ችግር ላይ ሙግት አቅርበዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ያሉትን የአፍሪካን ልማት መለኪያዎች በተለይም የቅርቡ ከፍተኛ የአገር ውስጥ ምርት እድገት መጣኔ፣ እየጨመረ የመጣው የነፍስወከፍ ድርሻ፣ የተንቀሳቃሽ ስልኮች እድገት እና የባንክ ተንቀሳቃሽ ስልክ፣ ቱሪዝም፣ የችርቻሮ ንግድ፣ የአፍሪካ ቢሊዮነሮች ብዛት እና የአፍሪካ አህጉር ከሌላው ዓለም ጋር ያለው የንግድ እንቅስቃሴ በቂ እንዳልሆነ እና ባለፉት ጥቂት ክፍለ ዘመኖች የልማት እንቅስቃሴ ተመጣጣኝም እንዳልሆነ እና ሙሉ በሙሉም ፋይዳየለሽ እንደሆኑ ግንዛቤ ተወስዶባቸዋል፡፡ ሮውደን እንዲህ የሚል ሀሳብ አቅርበዋል፣ “ከ15ኛው ምዕተ ዓመት ሁለተኛ አጋማሽ ጀምሮ ከእንግሊዝ እስከ ታዋቂው የምስራቅ ኤሲያ ነብሮች ድረስ ልማት በአጠቃላይ መልኩ ከኢንዱስትሪ ልማት ጋር የተቆራኘ ሆኖ ይታይ ነበር፡፡“ በአፍሪካ “ያለቀላቸው ስራዎች“ ማለትም እንደ የመጀመሪያ ደረጃ የግብርና ተግባራት እና ወደ ሌላ ዓይነት ሸቀጥ የሚለውጡ ተግባራት እንደ ማዕድን፣ የእንጨት ስንጠቃ ስራ እና ዓሳ ማስገር ከማኑፋቸሪንግ በስተቀር ልማት ሊባሉ አይችልም፡፡
በአፍሪካ ውስጥ ከኢንዱስትሪ ልማት እና ከመልካም አስተዳደር ውጭ ልማት አለ ማለት ይቻላልን? በቀላሉ የሀገር ውስጥ ምርት እድገት እና የንግድ እንቅስቃሴ እየጨመረ መሄድ ለኢኮኖሚ ልማት መረጋገጫ ሊሆኑ ይችላሉን? የነፍስወከፍ ገቢ እየጨመረ መምጣት፣ ቱሪዝም፣ የችርቻሮ ንግድ እና የአፍሪካ ቢሊዮነሮች በእርግጠኝነት መኖር አፍሪካ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገበች ያለች አህጉር ሊያሰኛት ይችላልን? የአፍሪካ ልማት የጥርስ መበስበስ እና ከመጠን ያለፈ ውፍረትን የሚያስከትሉ የስኳርነት ባህሪ ያላቸውን መጠጦችን በገፍ በማምረት ለሽያጭ በሚያቀርቡ ኩባንያዎች አማካይነት እድገት ሊመጣ ይችላልን? የአፍሪካ ልማት በሺዎች ለሚቆጠሩ አገር ጎብኝዎች የሚያገለግሉ ሆቴሎች ወይም ደግሞ አብዛኞቹ የአፍሪካ ዜጎች በቀን ከ2 ዶላር በታች እያገኙ ባለበት ሁኔታ፣ በባንክ ኔትዎርኪንግ መገናኘት እና ለመሰረታዊ ህይወት የሚያስፈልጉት ነገሮች ባልተሟሉበት መንገድ ልማት እንዴት ሊመጣ ይችላል? “በሚቀጥለው ትውልድ ላይ መዋዕ ንዋይ ለማፍሰስ” የዩኤስ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ርዕስ እንዴት ሊሆን ይችላል በማለት ፕሬይ ጥያቄ አቅርቧል፡፡
የኢንዱስትሪ እድገት የአፍሪካን ልማት ለመለካት እንደመስፈርት የሚያዝ ከሆነ በሚል ሮውደን የሚከተለውን መሞገቻ አቅርበዋል፣ “አብዛኞቹ የአፍሪካ አገሮች እንደ ጅብራ ባሉበት ቆመዋል ወይም ደግሞ ወደ ኋላ ተመልሰዋል፡፡“ ይህም ሆኖ የነጻ ገበያ አራማጅ የኢኮኖሚ ጠበብቶች የአፍሪካ አገሮች በአሁኑ ጊዜ ካለው የመጀመሪያ ደረጃ የግብርና ምርቶች እና የሚለውጡ ኢንዱስትሪዎች በአንድ ላያ በመጣመር በአሁኑ ጊዜ እንዳለው የዓለም ኢኮኖሚ መቀጠል እንዳለባቸው የአፍሪካ አገሮች እምነት እንዲያድርባቸው ያደርጋሉ፡፡ አስደንጋጩ እውነታ (የአፍሪካ ተነሳሽነት ሙዚቃ እና ዳንስ ወይ እንዲያንስ ተደርጓል አለያም ደግሞ ተረስቷል) ግን አብዛኞቹ የአፍሪካ አገሮች ጥቂት የማኑፋክቸሪንግ ስራዎችን ወይም ደግሞ ጉልበትን በስፋት በሚጠቀሙ ስራዎች እየታገዙ የመጀመሪያ ደረጃ የግብርና ምርት በማምረት የአፍሪካ መነሳሳት ይመጣል የመባሉ ጉዳይ ነው፡፡ ሮውደን “አፍሪካ እንዴት ባለ ጥሩ ፍጥነት እንደምታድግ ወይም እንደማታድግ የኢኮኖሚ እድገት መለኪያ መስፈርት ሀሳብ አቅርበዋል፡፡“
ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት የማኑፋክቸሪንግ መቶኛ ድርሻ የጨመረ መሆን አለመሆኑን ወይም ደግሞ የማኑክቸሪንግ ኢንዱስትሪው ተጨማሪ እሴት እየመጨመረ የመጣ መሆን እና አለመሆኑን ማየት እንችላለን፡፡ የማኑፋክቸሪንግ ተጨማሪ እሴት  ከአፍሪካ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ሀብት ያለው ድርሻ እ.ኤ.አ በ2000 ከነበረበት 12.8% እ.ኤ.አ በበ2008 ወደ 10.5% የወረደ ሲሆን በመልማት ላያ ያሉት የኤስያ ሀገሮች በተመሳሳይ ጊዜ ከነበረበት ከ22% ወደ 35% እድገት አሳይቷል፡፡ እንደዚሁም ደግሞ ከአፍሪካ ወደ ውጭ የሚወጡ የማኑፋክቸሪንግ ምርቶች በዓለም ገበያ ላይ ያላቸው ጠቀሜታ እየቀነሰ የመጣ ሲሆን የአፍሪካ አጠቃላይ ወደ ውጭ የሚወጡ የማኑፋክቸሪንግ ምርቶች ከጠቅላላው የሀገር ውስጥ ምርት ድርሻ እ.ኤ.አ በ2000 ከነበረበት 43% በ2008 ወደ 39% ወርዷል፡፡ የማኑፋክቸሪንግ ምርቶችን እድገት በተመለከተ የአብዛኞቹ አገሮች እድገት ባለበት ቆሞ የቀረ ሲሆን 21 የአፍሪካ አገሮች እ.ኤ.አ ከ1990 – 2010 ድረስ ባሉት ዓመታት ውስጥ የኔጌተቭ ተጨማሪ እሴት የነፍስ ወከፍ ድርሻ እድገት ያስመዘገበ ሲሆን 5 የአፍሪካ አገሮች ብቻ ከ4% የበለጠ የማኑፋክቸሪንግ ተጨማሪ እሴት አስመዝግበዋል… አፍሪካ በዓለም አቀፍ የማኑፋክቸሪንግ ንግድ ከመጨረሻው ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ማኑፋክቸሪንግ ከጠቅላላው የሀገር ውስጥ ምርት አንጻር ያለው ድርሻ ወይም ደግሞ ከዓለም አቀፍ የማኑፋክቸሪንግ ተጨማሪ እሴት ያለው ድርሻ አ.ኤ.አ በ2000 ከነበረበት 1.2% እ.ኤ.አ በ2008 ወደ 1.1% ያሽቆለቆለ መሆኑን ያመላክታል… ወደ ውጭ የሚወጡ ምርቶችን በሚመለከት ከዓለም አቀፍ የማኑፋክቸሪንግ ምርቶች ግብይት አንጻር የአፍሪካ ድርሻ እ.ኤ.አ በ2000 ከነበረበት ከ1% እ.ኤ.አ በ2008 ወደ 1.3% አሽቆልቁሏል፡፡ ከዘህ በተጨማሪ አፍሪካ በብዛት ጉልበትን በሚጠቀሙ ዝቅተኛ ቴክኖሎጂ የማኑፋክቸሪንግ ፋብሪካዎች ድርሻ እ.ኤ.አ በ2000 ከነበረበት 23% እ.ኤ.አ በ2008 ወደ 20% የወረደ ሲሆን በዝቅተኛ ቴክኖሎጂ ማኑፋክቸሪንግ ተመርተው ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች ድርሻ እ.ኤ.አ በ2000 ከነበረበት 25% እ.ኤ.አ በ2008 ወደ 18% አሽቆልቁሏል…
አሜሪካ በአፍሪካ መልካም አስተዳደር እና የኢንዱስትሪ መስፋፋትን በሚያመጡ የኢኮኖሚ ተግባራት ላይ መሰማራት ይኖርባታል ወይስ ደግሞ የኮካኮላ ሽያጭን እና የጠርሙስ ማምረቻ ፋብሪካዎችን እንዲሁም ለእድገት መሰረታዊ ለውጥ ሊያስመዘግቡ የማይችሉትን ሆቴሎች ማሳደግ ይኖርባታል? የአፍሪካ አገሮች ምርጫ የትኛው ነው?
በአፍሪካ መልካም አስተዳዳር ለእውነተኛ የኢኮኖሚ እድገት ቅድመ ሁኔታ ወሳኝ ነገር እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ሆኖም ግን መልካም አስተዳደር የደበዘዘ እና የነተበ ሀረግ ሆኗል፡፡ ዓለም አቀፍ  ባንኮች እና  አበዳሪ ድርጅቶች የህግ የበላይነትን፣ ተጠያቂነትን፣ ግልጽነትን፣ ሙስናን መዋጋትን እና በቁጥጥር ስር ማዋልን፣ ተሳትፎን…ወዘተ በማስመልከት እውነተኛ እና ተጨባጭነት ያላቸውን እርምጃዎች ሳይወስዱ ለይስሙላ በማነብነብ ብቻ ለእራሳቸው ፍላጎት መጠቀሚያ አድርገዋቸዋል፡፡ ስለምልካም አስተዳደር ደጋግሞ በማውራት ለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች በከፍተኛ የሞራል ስብዕና መሰረት ላያ የተመሰረቱ በመምሰል ስለሰብአዊ መብቶች አጠባበቅ፣ ስለድህነት ቅነሳ እና ስለሰይጣናዊ ማታለያ ዘዲያቸው ይመች ዘንድ ሌት ቀን ይደሰኩራሉ፣ ሰፊ ትንታኔም/lecture ይሰጣሉ፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ በዩኤስ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ በመገኘት እራሳቸውን ከፍ ባደረገ መልኩ እና ምንም ዓይነት ተጨባጭነት በሌለው መልኩ እንዲህ የሚል ዲስኩር አሰምተው ነበር፣ “መልካም አስተዳደርን ባሰፈናችሁ ቁጥር፣ የሚሰራ ዴሞክራሲን በተገበራችሁ ቁጥር፣ የህዝብን ገንዘብ አግባብነት ባለው መልኩ በመያዝ ማስተዳደር በቻላችሁ ቁጥር በመሪዎች ላያ የተጠያቂነት እና ግልጸኝነት ባህልን ባራመዳችሁ እና የስርዓቱ መገለጫ ባደረጋችሁ ቁጥር ያ ድርጊት ለመንግስት እና ስርዓቱን ለሚያሽከረክረው ስርዓት ብቻ አይደለም ጥሩ የሚሆነው ሆኖም ግን ለአኮኖሚ እድገትም ወሳኝ እና ጠቃሚ ነው“ ብለው ነበር፡፡
ከዚህ አንጻር የተከበሩ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ዩኤስ አሜሪካ በአፍሪካ ውስጥ በምን ዓይነት ሁኔታ ነው መልካም አስተዳደርን ልታሰፍን የምትችለው? ማድበስበስ ሳይሆን ግልጹን እና እቅጩን ይንገሩን፡፡ የአሜሪካ ኩባንያዎችን የአፍሪካ ወሮበላ ዘራፊ ገዥዎች አጋር በማድረግ ሙስናን የዝርፊያ መጠቀሚያ መሳሪያ አድርገዋልን? የፖለቲካ ተቀናቃኞቻቸውን፣ ትችት ለሚያቀርቡባቸው ሰላማዊ አመጽ በሚያካሂዱ ሰላማዊ ዜጎች ላይ በተደጋጋሚ ለሚያሰቃዩ ለወሮባላ የአፍሪካ ገዥዎች እርዳታ እና ብድር በመስጠት? የእራሳቸውን ዜጎች አቅም በሚያሳጡ እና ምርጫን በመዝረፍ በስልጣን ላይ የሚጣበቁ አምባገነኖችን ለማጠናከር? ነጻውን ፕሬስ ለሚያፍኑ እና ወጣት ጦማሪያንን በእስር ቤት በማጎር ለሚያማቅቁ ለወሮባላ ዘራፊ አገዛዞች የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ በማለት ዝም ብሎ በማየት? በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሰው ልጆችን መብቶች የሚደፈጥጡ አረመኔ ውንጀለኞችን ከሚገባው በላ በመንከባከብ?
በአፍሪካ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ዩኤስ አሜሪካ ምን ማድረግ እንዳለባት በእርግጠኝነት ታውቃለች፡፡ እነዚህ የአፍሪካ አምባገነን ገዥዎች ለዩኤስ አሜሪካ ጓደኛ መሆን ሲያቆሙ ያኔ ዩኤስ አሜሪካ በእነዚህ አምባገነኖች ላይ አስፋላጊ ነው ብላ የምታንበትን ከማድረግ ወደ ኋላ አትልም፡፡ ዩኤስ አሜሪካ ጓደኛ እና አጋር አይደሉም ብላ በምትጠረጥራቸው ገዥዎች ላይ ዩኤስ  አሜሪካ መጥፎ የሰብአዊ መብት አያያዝ በማለት በዩኤስ እና የዩኤስ አሜሪካ የንግድ ሸሪኮች ባልሆኑ የመዋዕለ ንዋይ በሚፈስስባቸው የኢኮኖሚ ዘርፎችን ኢላማ በማድረግ ቀያጅ ህግን በማውጣት ትተገብራለች፡፡ በእርግጥም ፕሬዚዳንቱ በአምባገነን ገዥዎች እና የሰብአዊ መብት ረግጠዋል ተብለው በሚጠረጠሩ ወይም እየተገበሩ ባሉ ባለስልጣኖች ላይ ተገቢ የሆነ እርምጃ እንዲወስዱ ከኮንግረሱ የሚሰጥ ስልጣን አያስፈልጋቸውም፡፡ በአፍሪካ ውሰጥ የመልካም አስተዳደርን ለማስፈን ፕሬዚዳንቱ ሁሉም የማስፈጸሚያ መሳሪያዎች የኢኮኖሚ ማዕቀብን ጨምሮ ሁሉም በእጆቻቸው ላይ ናቸው፡፡ በብዕራቸው ቅንጣት ጠብታ ከፍተኛ የሆነ ትዕዛዝ እና የተመረጠ የአስተዳደር ዘየን ማዘዝ ይችላሉ፡፡
ዩኤስ አሜሪካ በማትፈልጋቸው ገዥዎች ላይ መርጣ የሚያሽመደምድ ማዕቀብ ትጥላለች፡፡ በዩኤስ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ አንድ ወጣት የዙምምባብዌ የስራ ፈጠራ ባለሙያ/entrepreneur በዝምባብዌ ማዕቀብ መጠል ጉዳይን በማስመልከት ላነሳው ጥያቄ ፕሬዚዳንት ኦባማ የሚከተውን ምላሽ ሰጥተዋል፣ “በዙምባብዌ ያለው ሁኔታ የተለየ ነው፡፡   “በእኛ በዩናይትድ ስቴትስ ያለው ትልቅ ችግር በዙምባብዌ ውስጥ ያለው አገዛዝ መሰረታዊ የሆኑ የዴሞክራሲያዊ አሰራር ተሞክሮዎችን በመደፍጠጥ ላይ በመሆኑ እንዲሁም ይህ አሰራር መስመሩን እንዲይዝ እና ጋብ እንዲል እንዲሁም እኛ በዙምባብዌ ላይ ያለንን ፍላጎት እንዴት ማጣጣም እንደምንችል የተያያዘ ነው፡፡ እናም በአሁኑ ጊዜ በዙምባብዌ ነጻ ምርጫን እንዴት ማካሄድ እንደሚቻል፣ ግልጽ የሆነ መንግስታዊ አሰራርን ለማስፈን እንዲቻል ግልጽ የሆነ መልዕክት ለሮበርት ሙጋቤ ማስተላለፍ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ ይህንን የምናደርግበት ምክንያት ወንጀለኞች በሚፈጽሟቸው እኩይ ምግባሮች ተጠያቂ ሳይሆኑ አብዛኛውን ጊዜ በዚያው የሚቀጥሉ ስለሆነ የእነዚያ አገሮቸች ህዝቦች በተከታታይ ስለሚሰቃዩ ነው…”
በዙምባብዌ ያለው ሁኔታ የተለየ አይደለም፡፡ በአፍሪካ የተለመደ ዘይቤ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል እ.ኤ.አ በ2010 በተካደው ምርጫ 99.6 በመቶ አሸንፊያለሁ ብሎ ሲያውጅ ፕሬዚዳንት ኦባማ “ምርጫው እንዴት እንደተካሄደ የሚጠይቅ ግልጽ መልዕክት ከዩኤስ አሜሪካ አላስተላለፉም፡፡” ይኸው አፋኝ ገዥ አካል በአሁኑ ጊዜም በሺዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞችን በማጎሪያ እስር ቤቱ አስገብቶ እያሰቃየ ባለበት ሁኔታ የዩናይትድ ስቴትስ የመንግስት መመሪያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብት አያያዝን አስመልክቶ ዜጎች በእስር ቤት ህይወታቸው በአደጋ ላይ መሆኑን በመመልከት፣ ወጣት ጦማርያን ተይዘው በእስር ቤት እየማቀቁ መሆናቸውን ተጨባጭ ማስረጃ በመያዝ መምሪያው የሚያወጣቸው ዘገባዎች ገዥውን አካል የሚተቹ ቢሆንም ፕሬዚዳንት ኦባማ ሁለት ምላስ አንደበታቸውን በመጠቀም በስልጣን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ ለሚገኘው ገዥ አካል ግልጽ የሆነ መልዕክት አለማስተላለፍን መርጠዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ በኢትዮጵያ ላለው ገዥ አካል ያላቸው አመለካከት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ፍራንከሊን ዲ ሩዝቬልት በኒኳራጋው አምባገነን እና ገዥ ጋር አንድ ዓይነት ነው፡፡ ሩዝቬልት አምባገነኑን የኒካራጓ ገዥ በሚመለከት እንዲህ ብለው ነበር፣ “ሶሞዛ በጣም የተጠላ እና የተዋረደ ሰው ሊሆን ይችላል፣ ሆኖም ግን የእኛው በጣም የተጠላ እና የተዋረደ ሰው ነው፡፡“ በተቃራኒው መልክ በጣም የሚገርመው ነገር ግን ፕሬዚዳንት ኦባማ በተለያዩ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች ተወንጅሎ በዓለም አቀፉ የወንወጀለኞች ፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶበት የክስ ሂደቱ እየተካሄደ ባለበት ሁኔታ እና ለዙምባብዌው መሪ ለሮበርት ሙጋቤ (በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርደ ቤት አንዲያዙ ግፊት በማድረግ) በዩኤስ-አፍረካ ጉባኤ ላይ እንዳይገኝ የግብዣ ወረቀት በተነፈጉበት ወቅት ከኬንያው እሁሩ ኬንያታ ጋር አጋርነት እና ጓደኝነትን በመመስረት ለጉባኤውም እንዲገኝ አድርገዋል፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በመንግስት ስህተት እና በግለሰቦች መብት ድፍጠጣ ላይ ሳይቀር ጣልቃ ትገባለች፡፡ እ.ኤ.አ በ2012 ፕሬዚዳንት ኦባማ “ሰርጌ ማግኒቲስኪ” የተባለ ጠቃሚ የሆነ ህግን ፈርመዋል እናም ሰርጊ ማግኒቲስኪን በሚያስሩ፣ ሰብአዊ መብታቸውን በሚደፈጥጡ እና ግድያ በሚፈጽሙ ሰዎች ላያ ማዕቀብ ጥለው ነበር፡፡ በቅርቡ የሩሲያ ታሪክ ውስጥ ማግኒቲስኪ የህግ ባለሙያ ሲሆኑ ሙስናን በከፍተኛ ደረጃ የሚዋጉ ዜጋ ነበሩ፡፡ (ዩኤስ አሜሪካ ከጀግና አፍሪካውያን/ት ጎን ትሰለፋለችን? በሚል ርዕስ አዘጋጅቸ ያቀረብኩትን ትችት ይመለከቷል)፡፡ አስር ሩሲያዊ ዜጎች ሀብትን በመያዝ እና እ.ኤ.አ በ2009 ማግኒትስኪ እንዲሞት አስተዋጽ አድርገዋል በሚል ውንጀላ ወደ ዩናይትደ ስቴትስ እንዳይገቡ ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል፡፡ ሆኖም ግን ለሰርጌ ማግኒትስኪ ህግ ተብሎ እንደወጣው ሁሉ ለአፍሪካ ተመሳሳይ ጉዳዮች ግን ጆሮዳባ ይባላል! ይህ የሚሆነው ለምንድን ነው!??
ዋናው ነገር ግን በሺዎች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን/ት በየዓመቱ በአፍሪካ አምባገነን ገዥዎች ይሰቃያሉ፣ ይገደላሉ እናም ፕሬዚዳንቱ አላየሁም፣ አልሰማሁም በማለት ከንፈራቸውን መጥጠዋል፡፡ በእርግጥ ፕሬዚዳንት ኦባማ እነዚህን አምባገነን ገራፊ የአፍሪካ ገዥዎች የእርሳቸው አጋር በማድረግ ለፈጸሙት ወንጀል እና የጥቃት ሰለባዎቹ ለሚያሰሟቸው ጩኸቶች ጆሮዳባ ልበስ ብለዋል፡፡ በመቶዎች የሚቆጠሩ የሰብአዊ መብትን ለመደፍጠጥ የሰለጠኑ የገዥው አካል ወንጀለኞች እና የኢትዮጵያ እና የሌሎች የአፍሪካ አገሮች አምባገነኖች ወንጀሎችን ፈጽመው በየዓመቱ የአሜሪካንን መሬት ይወሩታል
ከተራራ ጎን ባለ ግማሽ ክብ ባዶ ቦታ ላይ ዝናብ ለማዝነብ አትሞክሩ፣
የአፍሪካን የሰርከስ ተውኔት በበዋሽንግተን ዲሲ ለማዝነብ መሞከርን በጣም አድርጌ እጠላዋለሁ፡፡ የአፍሪካን መሪዎች ጠንከር ባለ መልኩ መተቸት የእኔ ዓላማ አይደለም፡፡ ይልቁንም ለእነርሱ ስኬት የማወደስ እና ጥሩንባ መንፋቴን እሻለሁ፡፡ ሆኖም ግን በሰብአዊ መብት የሚደረግ የመብት ረገጣ እንደ ስኬት ተቆጥሮ ሊዘፈንለት የሚገባ አይሆንም፡፡ ከአፍሪካ አምባገነኖች የጠሩ ዴሞክራቶችን ማውጣት ይቻላልን? ጥቅል ጎመንን በመጭመቅ ደም ማውጣት ይቻላልን? ወሮበላ ዘራፊን ለመልካም እና ለጥሩ ነገር ማሰልጠን ይቻላል የሚል እምነት የለኝም፡፡ ማንም ቢሆን በተፈጥሮ ወሮበላ ዘራፊ ሆኖ አይፈጠርም፣ ሆኖም ግን በህይወት ሂደት ዘራፊ ከሆነ እድሜልኩን ዘራፊ እንደሆነ ይኖራል፡፡ ወሮበላ ዘራፊን ከጫካ ውስጥ ማውጣት ይቻላል፣ ሆኖም ግን ከወሮበላ ዘራፊዎች ውስጥ ጫካውን ማውጣት ከቶውንም አይቻልም፡፡ ወሮበላ ዘራፊን የእራሱ መለያ የሚሆን ጥብቆ ልበስ በልኩ ለክቶ በማሰፋት ማልበስ ይቻላል፣ የገንዘብ ማጨቂያ ቦርሳም መስጠት ይቻላል፣ ከቦታ ቦታ እደልቡ እንዲንቀሳቀስ ማድረግ ይቻላል፣ በጣም ውድ በሆኑ ምርጥ ሆቴሎች ማንፈላሰስ ይቻላል እናም ፊቱ ፍም እስኪመስል ድረስ ሰለመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በማዥጎድጎድ መጠየቅ ይቻላል፡፡ በእራስህ ላይ በመሳቅ ጥሎህ ሊሄድ ይችላል፡፡ እነዚህ የአፍሪካ አምባገነን መሪዎች ወደ ሆቴል ክፍሎቻቸው ሲገቡ እና ወደ አገራቸው ለመመለስ ወደ አውሮፕላን ሲገቡ ፕረዜዳንት ኦባማ የተናገሩትን እርባናየለሽ ንግግር ነው እንደሚሉ ጥርጥር የለኝም፡፡
በአፍሪካ ስልጣናቸውን ከህግ አግባብ ውጭ ለሚጠቀሙ አውነትን እስከአፍንጫው ድረስ ለመንገር ከወገቤ ጎንበስ ከእራሴ ቀና በማለት ጥያቄ ላቀርብላቸው እወዳለሁ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የአፍሪካ ወሮበላ ዘራፊዎች ስለእውነት፣ ስለሰብአዊ መብት ወይም ሌላ ማንኛውንም ማለት የምፈልገውን ሁሉ ብናገር ደንታቸው አይደለም፡፡ ሆኖም ግን ሁልጊዜ በተደጋጋሚ እንደምናገረው ሁሉ እውነትን፣ የህግ የበላይነትን፣ ሰብአዊ መብትን እና ሌሎችንም ለአፍሪካ ዘራፊ አምባገነኖች ከመስበክ ለቀንዳሞቹ ሰይጣኖች ከመጽሐፍ ቅዱስ እየጠቀሱ መስበክ ወይም ደግሞ በጣራ ላይ ባለ በጥቁር ባልጩት ድንጋይ ላይ ውኃ ማፍሰስ የቀለለ ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን እንዲህ የሚለው አንድ የቻይናዎቹ አባባል ይመቸኛል፣ “ቀስ በቀስ የሚንጠባጠብ የውኃ ጠብታ ድንጋዩን ሰርስሮ ይገባል“ በእርግጥ ለድንጋይ ልብ ፍጡሮች ግን ይሰራል የሚል እምነት የለኝም፡፡
አፍሪካውያን/ ስለአፍሪካ ልማት እና መዋዕለ ንዋይ ፍሰት የሚነገረውን አፈታሪክ አጥብቀውመዋጋትአለባቸው፣
አፍሪካውያን/ት በተለይም ምሁራን አፍሪካ ቻይና ከ30 ዓመታት በፊት እንዳደረገችው በፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እና በእድገት ጠርዝ ጫፍ ላይ ናት የሚለውን አባባል ተጫባጨነት ያላቸውን አሀዛዊ መረጃዎች በማቅረብ ነጭ ውሸት መሆኑን ማስተባበል እና ህዝቡ ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኝ በማድረግ የጎላ ሚና መጫወት ይኖርባቸዋል፡፡ በ30 እና ከዚያም በላይ በሆኑ ዓመታት የአፍሪካ ህዝብ ቁጥር ከእጥፍ በላይ በመሆን 2.4 ቢሊዮን ይደርሳል፡፡ የአፍሪካ የሰራተኛው ህዝብ ቁጥር ከቻይና ወይም ከህንድ ህዝብ የሰራተኛ ቁጥር የበለጠ ይሆናል፡፡ የአሁኑን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት አፍሪካ ከኦክስፎርድ የድህነት እና የሰብአዊ ልማት ተነሳሽነት የመጨረሻ እረድፍ ላይ የምትገኝ ስትሆን ከወደቁ መንገስታት መለኪያ አንጻር ደግሞ በመጀመሪያው እረድፍ ላይ የምትገኝ ይሆናል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ ፈጣን የእኮኖሚ እድገት ከሚያስመዘግቡ አገሮች ውስጥ 6ቱ በአፍሪካ አህጉር የሚገኙ ሲሆን በመሬት ላይ ከሚወድቁ 25 መንግስታት ውስጥ 18ቱ በዚህቹ የአፍሪካ አህጉር ውስጥ የሚገኙ ይሆናል፡፡ እ.ኤ.አ በ2050 ስንቶቹ የአፍሪካ ሀገሮች ይሆኑ ወደ የወደቁ መንግስታት መለኪያ መስፈርት ላይ በመጨረሻው እርድፍ ላይ የሚደርሱት?
“የአፍሪካ መነሳሳት” እና “የአፍሪካ ልማት” ትረካዎች የአህጉሪቱ መገለጫ የሆነውን ስር የሰደደ ሙስና፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የዕዳ ጫና እና የምዕራቡ ዓለም እርዳታ እና ብድር ሰለባ በሆኑ አስደንጋጭ በሆነ መልክ እየፈጠነ የመጣው የአፍሪካ የወደቁ መንግስታት ቁጥር እና ብዛት በውል ሳይጤን እንደቀነሰ እየተደረገ ዘገባ ይቀርባል፡፡ አፍሪካ የግብርና ምርት ውጠቶችን፣ ጥሬ ዕቃዎችን፣ ብረቶችን እና ማዕድናትን ወደ ውጨ በመላክ የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በመተግበር ስኬታማነትን በማስመዝገብ ከድህነት እና ከኋላቀርነት ትወጣለች እየተባለ ለአፍሪካውያን/ት ባዶ ፕሮፓጋንዳ ይነዛል፡፡ የአፍሪካ ምሁራን በተለይም የአፍሪካ የኢኮኖሚ ጠበብቶች የዚህን የውሸት ፕሮፓጋንዳ በማስተባበል እና እወነተኛውን እና ትክክለኛውን መረጃ በመስጠት ክፍተቱን መዝጋት አለባቸው፡፡
በአፍሪካ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ስራ አጥ ወጣቶችን ለመቅጠር የኮካኮላ እና ጠርሙስ ፋብሪካ በቂ አቅም ሊኖረው ይችላልን? ማሪኦት ሆቴሎች በቂ የሆኑ የስራ እድሎችን በመፍጠር ለአፍሪካ መሰረት የሚሆን የኢኮኖሚ እድገትን ሊያስመዘግቡ ይችላሉን?
የመጀመሪያው የፕሮፓጋንዳ ህግ እንዲህ የሚል ነው፣ “ ሁልጊዜ ውሸትን የምታስተጋባ ከሆነ ህዝብ ሊያምን ይችላል“ ለዚህም ነው ሁልጊዜ እውነትን ወሸት አድርጎ በማውራት ውሸት በእውነት ላይ ስህተት እንደሌለው ተደርጎ እንዲወሰድ የሚፈለገው፡፡ ሰለአፍሪካ እድገት እና የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት እየተደረገ እና እየተነዛ ያለው ሸፍጥ ታላቅ ውሸት በእርግጠኝነት ምን እደሆነ ማጋለጥ አስፈላጊ ነው፡፡ ቤንጃሚን ዲስራኤል እንዲህ ብለው ነበር፣ “ውሸቶች ፍጹም ውሸቶች እና የተዛቡ ለምንም የማይውሉ አሀዛዊ መረጃዎች አሉ“ ስለአፍሪካ ባለሁለት አሀዝ እድገት በአፍሪካ መሪዎች እንደሚነገረው ድፍረት የተሞላበት ነጭ ውሸት ነው፡፡ ይህ ውሸት በበለጋሽ እና አበዳሪ ድርጅቶች ሲደገም ደግሞ የለየለት ነጭ ውሸት ሆናል፡፡ በአዕምሮየለሾች ዓለም አቀፋዊ የዜና መገናኛ ዘዴዎች እንደበቀቀን ሲደጋገሙ በእርገጥ አሃዞች ይሆናሉ፡፡
በዩኤስ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ በመገኘት ድራማውን በመስረቅ የሱዳኑ የቴሌኮሙኒኬሽን ባለሀብት የሆኑት ሞኢብራሂም እንዲህ በማለት ለዘገባ አቅርበውታል፡፡
እኔ በአውሮፕላኑ ላይ ሁሉንም አፍሪካዊ ባገኘሁ ጊዜ… ሁሉም ወደዚህ ወደ አሜሪካ የመጡት በጣም የሚስብ ነገር ለመናገር፣ በሚገባ መረጃ ያላቸው የአሜሪካ የንግድ ግለሰቦችን ለመሳብ እና በአፍሪካ ጥሩ የንግድ እድል እንዳለ ግልጽ ለማደረግ ነበር፣ አንድ የሆነ የቤት ስራ ነገር ይሰራሉ፡፡ በአፍሪካ በየትኛውም ቦታ የቻይና የንግድ ሰዎች እንዲሁም የብራዚል የንግድ ሰዎች አሉ፡፡ ማናችንም ብንሆን ለመናገር፣ ኑ እዩ እና መዋዕለ ንዋያችሁን በአፍርካ አፍስሱ ለማለት ወደ ብራዚል ወይም ወደ ኤስያ እና ቻይና አልሄድንም አልሄድንም፡፡ እራሳቸው ፈልገው አገኙ እናም መጡ እና መዋዕለ ንዋያቸውን አፈሰሱ፡፡ አንደዚህ ነው ዋኛ የንግድ ሰው የሚያደርገው፡፡ ለምንድን ነው ወደዚህ ወደ አሜሪካ በመምጣት  ምንም መረጃ የሌላቸውን የአሜሪካ የንግድ ማህበረሰብ አባላት መረጃ የምንሰጣቸው? እናንተ ሰዎች ታውቃላችሁ ጉግልን የፈጠራችሁት እናንተ ናችሁ፣ አባካችሁ በዚያ ተጠቀሙ፡፡
ለሰው ልጅ ክብር እና ደህንነት የሞኢብራሂምን አቅም እና ተፈጥሯዊ ባህሪ እንዲኖረኝ እመኛለሁ፡፡ ስለአፍሪካ ልማት እና መዋዕለ ንዋይ ፍሰት ጉዳይ ሲነሳ በርካታ የአፍሪካ አገሮች በፍጹም የድህነት አራንቋ ውሰጥ ተዘፍቀው በመሰቃየት ላይ እንዳሉ ሳይ ገሀነም የገባሁ ያህል ይሰማኛል፣ በጣምም እበሳጫለሁ፡፡ ሆኖም ግን ለመበሳጨት ሙሉ መብት አለኝ ምክንያቱም ስለአፍሪካ ሲነሳ ይደክመኛል፣ እና አፍሪካውያን/ት በምዕረብ እና በምስራቅ እንደ ሰሙኒ  ሴተኛ አዳሪ አንድተቀሙባት አልፈለግም፡፡
እውነታዎች እና ማስረጃዎች እንደሚያሳዩት አፍሪካ በፈጣን እድገት ላይ ያለች አህጉር አይደለችም፡፡ ይልቁንም ፈጣን የሆነ የድህነት አቃጣሪዎች በፍጥነት የሚያድጉባት፣ ድህነት እራሱ ያንዣበባት እና ቤቱን የሰራባት አህጉር ናት፡፡ አፍሪካ ለማደግ እና እራሷን ለመቻል ያላት ብቸኛው መንገድ በእራሷ ዜጎች ደም፣ ላብ እና እንባ በመታገዝ የሚመጣ ልማት ነው፡፡ ይህ የማይካድ እና ዘላለማዊ እውነታ ነው!
“የዩኡስ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ” በሚል ርዕስ ባቀረብኩት ሶስት ተካታታይ ትችት የአፍሪካ ተውኔት እንደተጀመረ ጠቁሜ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ የአፍሪካ ተውኔት ተጠናቅቋል ስል ደስታ ይሰማኛል፡፡ ለተውኔቱ ተዋናዮች ጥሩ መጥፎ ነው! የደወል ደዋዩም ተውኔቱ እንደተጠናቀቀ እና አካባቢውን ለቅቀው እንዲሄዱ ደወሉን ደውሏል፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በአንድ ወቅት የመንገድ እና የጫካ አሸባሪዎች እንደምትለው ሁሉ የመንግስት አሸባሪነትንም በተመሳሳይ መልኩ በተመሳሳይ ቦታ ላይ እንደምታስቀምጠው ዘላለማዊ የሆነ ብሩህ ተስፋ አለኝ፡፡ “አሜሪካ አንድ ዓይነት ዩኒፎርም ለብሰው እና የመመንታፊያ ቦርሳቸውን ከአሜሪካ ግብር ከፋይ ህዝብ በልመና በመጣ ገንዘብ አጭቀው ከሚዞሩ የመንግስታት አሸባሪዎች እና ወሮበላ ዘራፊዎች ጋር አጋርነት መመስረት የለባትም፡፡“
“በእርግጠኝነት ለመናገር ስለአፍሪካ ስለሚነገሩ ጉዳዮች ምቾት አይስማኝም፡፡ ከአንድ ጫፍ መጥተናል…በተመሳሳይ መልኩ አፍሪካ በአሁኑ ጊዜ እንደተቆረሰ ዳቦ ቆንጆ ናት፡፡” ሞኢብራሂም በዩኤስ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ የተናገሩት
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ነሐሴ 24 ቀን 2006 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment