Tuesday, October 14, 2014

13 የ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች በነፃ ተለቀዋል።

የወሎ ዩኒቨርስቲውን ሙሃመድ ሰዒድን ጨምሮ 12ቱ ሙስሊም የዩኒቨርስቲ ተማሪዎቻችን ‹‹በ 196 ዓ.ም ተደንግጎ የወጣውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ፣ 38/1/ እና 257/ሀ/ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ›› መንግስት ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓትንና አለባበስን በሚመለከት ያወጣውን የሥነ ምግባር ደንብ በመቃወም በሃይማኖት ሽፋን ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሒደትን ማስተጓጎላቸውን ፣ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በትምህርት ላይ የሚገኙ ሙስሊም ተማሪዎችን ሕዝበ ሙስሊሙ በአመፅ ውስጥ እንዲሳተፍ በማድረግ የሥነ ምግባር ደንቡ በተግባር ላይ እንዳይው እንዲሁም በህግ ተይዞ በመታየት ላይ ያለውን ራሳቸውን የሙስሊሙ ማህበረሰብ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ በማለት የሚጠሩትን ተከሳሾች ለማስፈታት በመንግሥት ላይ በሕገወጥ መንገድ ተፅዕኖ በማድረጋቸው ፣ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን የህገ መንግሥታዊ ሥልጣንን ተግባራዊነት ለማሰናከል በመገፋፋት፣ ግዙፍ ያልሆነ የማስተላለፍ ወንጀል በሚል በፌደራሉ አቃቤ ህግ በሃሰት እንደተወነጀሉና ካለፉት 1 አመት ከ6 ወር በላይ በእስር ላይ እየማቀቁ እንደሆነ ይታወሳል።
እንደሚታወቀው የፌዴራሉ ከ/ፍ/ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት ሐምሌ 18/2005፣ ሐምሌ 19/2005 እና ህዳር 2006 በዋለው ችሎት በክስ ማመልከቻው ላይ ከተመለከቱት 28 ምስክሮች የ17ቱን በክፍት እና የ2ቱን በዝግ ችሎት በድምሩ 19 የሐሰት ምስክሮችን ሰምቷል። ከእነዚህ ‹‹የሰለጠኑ›› ምስክሮች
አንዳንዱ በብጣሽ ወረቀት የያዘውን የሚያነብ የነበረ ሲሆን ሌላው ደግሞ የሰለጠነው (የሸመደደው) ጠፍቶት ያልተከሰሰ ሰው ስም ሲጠራ ተደምጧል። ሌላው ደግሞ ‹‹ይህም ተማሪ በአካል አላውቀውም›› እያለ ፍ/ቤቱ ‹‹በማታውቀው ሰው ላይ መመስከር አትችልም›› ማለት ሲገባው ምስክሩን የተቀበለው ሲሆን ሌላው ደሞ ሃሰተኛ ምስክሩ አውቀዋለሁ ያለውን ሰው እንኳ ከተከሳሾች ለይቶ ማሳየት አልቻለም። አላህን ፈርቶ ‹‹እኔ እገሌን የማውቀው ተቃውሞችንን በሰላማዊ መንገድ ለመንግስት ማሳወቅ አለብን ሲል ነው›› ብሎ የመሰከረው ደግሞ በሐሰት
ስላልመሰከረ ‹‹አንተ ስነ-ስርአት አድርገህ መስክር! በህግ ትጠየቃለህ!›› የሚል ማስፈራሪያ ከአቃቤ ህግ ሲደርስበት እንደነበር መስተዋሉ ትዝታችን ነው።
ንፁሃን ወንድሞቻችንና በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የምትገኝው ጀግናዋ እህታችን ፈትህያ ሙሃመድ ግንቦት 26/2006 ዓ.ል በዋለው ችሎት የፌደራል አቃቤ ህግ ባቀረበው ክስ እና ሐሰተኛ ምስክር ዙሪያ የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ንፁሃን ተከሳሾችን ጥፋተኛ ናቸው ማለቱንና ይህን ተከትሎም 12ቱ ብርቅዬ ሙስሊም የዩኒቨርስቲ ተማሪዎቻችንና አሁን ጨለማ ክፍል የተከረቸመበት የወሎ ዩኒቨርስቲው መምህር ኢንጂነር ሙሃመድ ሰዒድ ባለፉት ወራቶች መከላከያቸውን ያቀረቡ ሲሆን የመከላከያ ምስክሮቹም ተከሳሾቹ ቃላቸውን በግዳጅና በድብደባ እንደሰጡ ገልፀዋል።
በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የምትገኝው የቤቴል ሜዲካል ኮሌጅ ተማሪ የነበረችው እህታችን ፈትህያ ሙሃመድ እድሪስ እና ንፁሃን ወንድሞቻችን መስከረም 23-01-2007 እለተ ዐርብ የፍርድ ቤቱን የመጨረሻ ብይን ለማድመጥ በፌደራሉ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 14ተኛ ምድብ ችሎት የተገኙ ሲሆን ወትሮውንም በመንግስት የደህንነት አካላትና በፀጥታ ሃይሎች ብሎም በሹመኛ ባለስልጣናት የሚመራው የካንጋሮው ፍርድ ቤትም ተከሳሾቹ የዓቃቤ ህግን ክስ ማስተባበል ባለመቻላቸው በጅምላ ጥፋተኛ ናቸው በማለት የተዘናበለ ውሳኔ ማስተላለፉንና የተከሳሾች ጠበቆችም የቅጣት ማቅለያ ለፍርድ ቤት የሰጡ ሲሆን ዓቃቤ ህግ በፅህፈት ቤት በኩል እንዲያቀርብ ታዟል፡፡
በዚያው እለትም መስከረም 4 በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የምትገኝዋ ሁለተኛ ተከሳሽ ፈትህያ ኒቃብ (ዓይነ-ርግብ) በማረሚያ ቤት ማድረግ እንደተከለከለች፣ ምክንያቱ ደግሞ የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር መመርያ እንደሚከለክል በማስረዳት፣ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው የማረሚያ ቤቱ ተወካይ አመልክተው ነበር፡፡ ተከሳሿ ተጠይቃ የሃይማኖት ጉዳይ በመሆኑ በማረሚያ ቤቱ እንድታወልቅ በመታዘዟ ለ15 ቀናት ቤተሰቦቿን ጭምር ሳታገኝ መቆየቷን በማስረዳት ተቃውማለች፡፡ ፍርድ ቤቱም ጉዳዩ የማረሚያ ቤት መሆኑንና ጣልቃ እንደማይገባ በመግለፅ አሳዛኝ ውሳኔ በይኗል።
የፌደራሉ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 14ተኛ ምድብ ችሎትም በሰጠው የጥፋተኝነት ውሳኔ ላይ የቅጣት ብይን ለመስጠት ለዛሬ ጥቅምት 4-2007 በሰጠው ቀነ ቀጠሮ መሰረት የቤቴል ሜዲካል ኮሌጅ ተማሪ የሆነችውን ፈትህያ ሙሃመድን ጨምሮ ሌሎች ተከሳሽ ጀግኖች ወንድሞቻችን በፍርፍ ቤቱ እንደተገኙ የቂሊንጦ ልሳን ምንጮች ዘግበዋል።
ዛሬ ጥቅምት 4-2007 በተሰየመው ችሎት
ተማሪዎቻችንና መምህራችን በፍርድ ቤቱ የተገኙ ሲሆን የዩኒቨርሥቲ ተማሪ በመሆናቸውና እሥካአሁን የታሠሩበት ጊዜ በቂ ሆነው በመገኝቱ የልደታው ፍርድ ቤት እንዲፈቱ ወስኗል።

No comments:

Post a Comment