Friday, October 31, 2014

Ethiopia: Amnesty International’s Report: Sensationalism Gone Wild

America's War in the Horn of  Africa:  “Drone Alley” – a Harbinger of Western Power across the African Continent
Amnesty International made waves this week with its report alleging ”patterns of human rights violations” on the Oromos – a community to which the President of Ethiopia belongs.
The London-based rights group claimed:
“at least 5,000 Oromos have been arrested based on their actual or suspected peaceful opposition to the government” and presented troubling accounts of individuals who allegedly had been subjected ”to treatment amounting to torture and other cruel, inhuman or degrading treatment.”
Inadequacy of the human rights practices in Ethiopia is not a much disputed matter. Even the authorities in Addis Ababa felt the need to launched an inter-ministerial National Human Rights Action Plan (NHRAP) so as to “review the  present  human  rights  situation  of  the country, identifies potential problems, and sets feasible solutions.”
But the similarity ends there. What the NHRAP acknowledges is “occasional human rights violations are committed by some police officers due to lack of awareness,” while Amnesty International  alleges “patterns of human rights violations” in which “a multiplicity of both regional and federal actors are involved.”
While NHRAP aims:
“to develop a  comprehensive  and structured  mechanism  to  advance  the  respect,  protection  and  fulfillment  of  human  and  democratic  rights”;  western rights-groups want “the establishment of an independent commission of inquiry,   fact – finding mission or comparable  procedure, comprised of independent international experts.”
For a cautious observer, the essential lies in the western rights-groups’ demand and Addis Ababa’s refusal of a “confession”  and an international intervention. Demands that Addis Ababa deems paternalistic, while Amnesty decries ”the repeated failure to acknowledge the existence of  torture  demonstrates a concerning lack of political will.”
Thus, in an apparent bid to pressure Ethiopia and her developmental partners, Amnesty  picked a sensational title on the reports. With an alarmist title ”Because I Am Oromo: Sweeping Repression In The Oromia Region Of Ethiopia”, Amnesty International’s report led to sensational headlines:Ethiopia ‘targets’ Oromo ethnic group (BBC); Ethiopia ‘ruthlessly targeting’ and torturing Oromo people, says Amnesty (The Guardian); Ethiopia Systematically Repressing Oromo (VOA ) and others.
The media outlets were not entirely unjustified, as that is what the report appears to have been aiming for. Though buried in the report, a disclaimer-styled note reads:
“many of the human rights violations documented in this report…affected other ethnic groups as well as Oromo s  over the  same time period. However, this reports focuses  specifically on Oromia and Oromo s due to  the  large  scale of the targeting of actual or perceived dissent in the region.  This research did  not, however,   compare the treatment of the Oromo to treatment of other ethnic groups, so the  report does not seek to establish discriminatory treatment, but to specifically document  patterns of violations in Oromia.”
Yet, the report consisted several contentions impressing up on the reader that the government targeted the Oromos – a community to which the President, the Dep. Prime Minister and the Hose Speaker as well as a third of the population  belongs.
Two illustrations suffice: In its introductory note, it shouts ”Oromos make up  a high proportion of the prison population in federal prisons …. [the numerical size of the group] alone does not account for the high  proportion of Oromos in the country’s prisons”
Nonetheless, the report indicates elsewhere that ”a large proportion of former detainees interviewed by Amnesty International” were detained in region”. Though two remarks were quoted in the report to corroborate the claim, both are about decade-old and made in a political campaign gathering context – not to Amnesty’s interviewers. In fact, since the number of inmates at Federal prisons was about 18,000 – or a fifth – of the total prison population , any plausible estimate of disproportionate incarceration would not change the math by significant margin. Taking into consideration that prison density in Oromia region was 87:100,000 in 2010, while the national average was 108.
Perhaps even more bewildering is the report’s claim that ”the government has exhibited hostility to displays of Oromo cultural heritage” adding that ”participating  in societies to discuss and promote Oromo culture and history  also causes harassment and in some cases, arrest”. Quite to the contrary, the recent debate was on the regional government’s insistence that business owners should give the Oromo language prominence on their roadside billboards.
But there is a giveaway.  Describing an arrest made during a celebration of the  traditional festival of Irreecha , the report indicates ”Reported reasons for arrests included  wearing clothes in colours considered as symbols of Oromo resistance  –   red   and   green  –   or  alleged chanting of political slogans during the festival”.
The “symbols of Oromo resistance” was an euphemism the report writers chose to use for the flag/symbols of OLF (Oromo Liberation Front) – a group with a troubling track-record and recently proscribed as terrorist by Ethiopian parliament.  Whether a ban on wearing flag/symbols a terrorist group is advised was an issue on which Amnesty could have cast light on.
This is not a rebuttal of the report, as that requires further analyses. Again, as noted earlier, the rights group may be tempted to use sensational headings and catchy-phrases which may be excusable approach if a single-minded focus on saving others is presumed.
Yet, employing hyperbolic  statements that stir emotions in an entire community does a disservice to the primary objective of the report and leads the conversation astray.

source Global Research, October 31, 2014

Wednesday, October 29, 2014

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የእስር ቅጣቱን በመቃወም ይግባኝ ሊጠየቅ ነው


  • 415
     
    Share
በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 16ኛ ወንጀል ችሎት ህዝብን ለአመፅ በማነሳሳትና ሀሰተኛ መረጃን በመስጠት በሚል ዐቃቤ ሕግ ክስ መስርቶበት የ3 ዓመት ፅኑ እስራት የተፈረደበት በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ይግባኝ እንደሚጠይቁ ጠበቃው አቶ አመሀ መኮንን አስታወቁ። ጠበቃው አክለውም፤ ውጤቱ ምንም ይሁን ምን ሕጉ እስከፈቀደው ድረስ ማንኛውንም መድረክ አሟጠን እንጠቀማለን ሲሉ ተናግረዋል። ይግባኝ እንደሚጠይቁ ጠቁመው ያም ሆኖ የተለየ ውጤት ካልተገኘ እስከሰበር ችሎት እንደርሳለን ብለዋል።
በተከሳሹ ላይ ፍርድ ቤቱ የጥፋተኝነት ብይን ከሰጠ በኋላ ስለምን የቅጣት ማቅለያ አላቀረባችሁም ተብሎ ከሰንደቅ ጋዜጣ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱም፤ በመርህ ደረጃ ጥፋተኛ መባል አልነበረበትም፤ አሁን ጉዳዩ ብዙ ዓመት የመታሰርና ትንሽ ዓመት 
የመታሰር ብቻ ሳይሆን በዋናነት ለቅጣት ቅነሳ መከራከሪያችን ለህግ ጥፋቱን የማመን ምልክት ስላለው አልፈለግንም።

Temesghen Desalegn (CPJ)cropped
አመፅን ለመቀስቀስ በመሰናዳት ወንጀል ተሳትፎ፤ ሕገ-መንግስቱንና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ የሚያነሳሱ ፅሁፎችን በቀድሞዋ ፍትህ ጋዜጣ ላይ ሲያሰፍር ነበር በሚል የፌዴራሉ ዐቃቤ ሕግ ክስ የመሰረተበት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፤ ጥፋተኛ የተባለበት ግዙፍ ያልሆነ የማሰናዳት ወንጀል ሥር በ3 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ሲል ፍርድ ቤት ባሳለፍነው ሰኞ ጥቅምት 12 ቀን 2007 ዓ.ም የቅጣት ውሳኔውን አስተላልፏል።
ዐቃቤ ሕግ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 16ኛ ወንጀል ችሎት ሶስት ክሶችን በጋዜጠኛው ላይ አቅርቦ በሰውና በሰነድ ማስረጃዎች 
አስረድቷል። ተከሳሹም ከተከሰሰባቸው ወንጀሎች ነፃ ያወጡኛል ያላቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች ለፍርድ ቤቱ አቅርቦ የተከራከረ ቢሆንም፤ ችሎቱ የግራ ቀኙን መረጃ መርምሮ ጥቅምት 3 ቀን 2007 ዓ.ም ጥፋተኛ ነህ ብሎት እንደነበር ይታወሳል።
በዐቃቤ ሕግ የክስ ዝርዝር የተጠቀሱት ፍሬ ሀሳቦች መካከል በአንደኛው ክስ ሥር “ሞትን የማይፈሩ ወጣቶች” በሚል ርዕስ ነሐሴ 23 ቀን 2003 ዓ.ም ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፃፈው ሀተታ ውስጥ ወጣቶች ለአብዮትና ለለውጥ እንዲነሳሱ በማድረግ፤ በአረቡ አለም ወጣቶች የነበራቸውን ሚና በመጥቀስ አሁን ያለውን ስርዓት ለመቀየር ወጣቶች ለአመፅ እንዲነሳሱ አድርጓል የሚል ነው።
በ2ኛ ክስ ስር የተዘረዘረው ሀሳብ ደግሞ “የሁለተኛ ዜግነት ህይወት በኢትዮጵያ እስከመቼ?” በሚል ርዕስ ሐምሌ 22 ቀን 2003 ዓ.ም በፍትህ ጋዜጣ ባወጣው ሀተታ ስር መንግስት በተለያዩ ክልሎች የጅምላ ጭፍጨፋ ፈፅሟል በማለት የአገሪቱን መንግስት ስም በማጥፋትና በሀሰት ወንጅሏል የሚል ክስ ተመስርቶበታል።
ዐቃቤ ሕግ 3ኛ ክስ አድርጎ ያቀረበው ደግሞ በመጋቢት 7 ቀን 2004 ዓ.ም በታተመችው ፍትህ ጋዜጣ ላይ “ሲኖዶሱና መጅሊሱ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ማጥመቂያ” ሲል ባሰፈረው ፅሁፍ መንግስት የሃይማኖት ተቋማቱን ለፖለቲካዊ ዓላማ እየተጠቀመባቸው ስለመሆኑ በማተት የህዝብን እምነት እንዲሸረሸር አድርጓል ሲል ይከሰዋል።
ተከሳሹ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፤ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧቸው በነበሩ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች አማካኝነት በጥቅሉ፤ የጋዜጠኝነት ተግባሩን እየተወጣ በመሆኑንና በዚህም ህገ መንግስቱ የሰጠውን ኀሰብን የመግለፅ ነፃነት ተጠቅሞ ሥራውን ማከናወኑን ባቀረባቸው የመከላከያ ምስክሮች ጭምር አስረድቷል።
ሆኖም የግራ ቀኙን ክርክር ሲመረምር የቆየው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 16ኛ ወንጀል ችሎት ጥቅምት 3 ቀን 2007 ዓ.ም ጥፋተኛ ማለቱን ተከትሎ ባሳለፍነው ሰኞ የቅጣት ውሳኔውን አስተላልፏል። በዚህም የውሳኔ ንባብ ወቅት ፍርድ ቤቱ እንዳለው፤ ምንም እንኳን ተከሳሹ ጥፋተኛ ቢባልም የቀረቡበት 3 ክሶች በአንድ ሃሳብ ሊጠየቅ የሚገባው ነው በሚል፤ በወንጀል ህጉ የመገፋፋትና ግዙፍ ያልሆነ የማሰናዳት ተግባር ወንጀል ብቻ ይቀጣ ማለቱን ተከትሎ ምንም አይነት የቅጣት ማቅለያ ባላቀረበው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ የ3 ዓመት ፅኑ እስራት ፈርዶበታል።
በተያያዘም አሳታሚው ማስተዋል የህትመትና ማስታወቂያ ኃ/የተ/የግ ማህበር ላይ ዐቃቤ ሕግ አቅርቦት የነበረው የንብረት ይወርስልኝ ጥያቄን ፍርድ ቤቱ ወደጎን በመተው የ10ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ጥሎበታል።

ምንጭ፦ ሰንደቅ ጋዜጣ

- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/35812#sthash.Ryk2P5za.HSP249Ld.dpuf

ሃብታሙ አያሌው ቶርቸር እየተደረገ ነው !

ክስ ሳይመሰረትበት ለአራት ወራት በማእከላዊ እስር ቤት የሚገኘው የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ ወጣት ሃብታሙ አያሌው፣ ከፍተኛ ኢሰብአዊ ግፍ እየተፈጸመበት እንደሆነ ታወቀ። ሃብታሙ አያሌው ለአንድ ሳምንት ወደ መጸዳጃ ቤት እንድዳይሄድ በመከልከሉ በፌስትታል ይጠቀም እንደነበረ፣ ለሶስት ሳምንታትም ቁጥር ስምንት በምትባል የጨለማ ቤት ዉስጥ ለብቻው እንዲቀመጥ መደረጉንም አረጋግጠናል። “ወደ ፖለቲካው የማትመለስ ከሆነ ትወጣለህ። አለበለዚያ እዚሁ ነው የምትሞተው” በማለት አማራጭ ቢያቀርቡለትም፣ ሃብታሙ መሞትን እመርጣለሁ የሚል መልስ የሰጣቸው ሲሆን፣ እየደረሰበት ባለው ስቃይ በጣም እየታመመ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። “እስኪ ትግሉን እናስቀጥላለን የሚሉ ሰዎች ያድኑህ ? “ ሲሉ አሳሪዎቹ በስቃዩ የሚደሰቱ ሲሆን፣ ከባለቤቱ በስትቀር ጠበቃዉም ሁሉ ሳይቀር እንዳያየው ተደርጓል። በተመሳሳይ ሁኔታ ዳንኤል ሺበሺ፣ የአንድነት የድርጅት ጉዳይ ም/ሃላፊ ፣ በታፈነና አየር በማያስወጣ ክፍል ዉስጥ እንዲታሰር በመደረጉ በተደጋጋሚ ለተቅማጥና ተያያዥ በሽታ መጋለጡን፣ እንዲሁም የመተንፈስ ችግር እንዳለበት ለማወቅ ችለናል። “የፓርቲያችሁ የገንዘብ ምንጭ ምንድን ነው ? አንድነት ዉስጥ ያሉ ጠንካራ አባላት እነማን ናቸው ? “ በሚል ጥያቄ የቀረበለት ዳንኤል ሺበሺ፣ ክብሩን በሚነካ መልኩ እንደሚሰደብም የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ሃብታሙ አያሌው ፣ በእርሱ ላይ እይደረሰ ያለው ግፍ በማንም ዜጋ ላይ መድረስ እንደሌለበት በመግልጽ “የግፈኛው አገዛዝ እንዲያበቃ የኢትዮጵያ ሕዝብ መነሳት አለበት” ሲልም ለህዝቡ የትግል ጥሪ አስተላልፏል። የአንድነት ራዲዮ የዘገበዉን እንደሚከተለው ያድምጡ ! http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/16060#more-16060

“ሂድና ከአባዱላ ተማር የአንተ አቅም ግንባታ እንኳን አቅም ሊገነባ ያለውንም ሊያስቀጥል አልቻለም” ተብለው በአቶ መለስ የተገመገሙት አቶ ተፈራ ዋልዋ

“ተፌ!”

tefera w

ታጋይ፣ ከንቲባ፣ መከላከያ ሚ/ር፣ ምክትል ጠ/ሚ/ር፣ አቅም ገንቢ፣ አቅም ተገንቢ … ከዚህ ሁሉ አልፈው አሁን አቅማቸው ተገንብቶ የስፔስ (ሕዋ) ሳይንስ “አቅም ግንባታ” ለመሆን የበቁት ጡረተኛው ተፈራ ዋልዋ “የኢትዮጵያን የሕዋ (ስፔስ) ሳይንስ ሶሳይቲን” ገንብተው በሪፖርተር በኩል ብቅ ብለዋል፡፡
“አቅም ገንቢ ሚ/ር” በነበሩበት ወቅት “ሂድና ከአባዱላ ተማር የአንተ አቅም ግንባታ እንኳን አቅም ሊገነባ ያለውንም ሊያስቀጥል አልቻለም” ተብለው በአቶ መለስ የተገመገሙት አቶ ተፈራ አቅማቸው ተገንብቶ ለስፔስ መድረሱን “ባለራዕዩ መሪ” ሳያዩና ሪፖርተር ላይ ሳያነቡ መሰዋታቸው አቶ ተፈራን እጀ ሰባራ አድርጓቸዋል፡፡
የአላሙዲን “ወዳጅ” ሪፖርተር የአቶ ተፈራን አንደበት ገድቦት ነው እንጂ ተፈራ “ሼኸ፣ ዶ/ር፣ አቅም አስገንቢ … አላሙዲንን” ባነሱበት አንደበታቸው በግል ጄታቸው ገስግሰን ሁለተኛውን ሙት ዓመት “ነፍስ ይማር” በማለት አክብረን “በባለራዕዩ መሪያችን ስም በዚያውም ዛፍ ተክለን እና ፓርክ አቋቁመን እንዲሁም አንድ ፕላኔት በስማቸው አሰይመን” ተመልሰናል እንዳሉ ይገመታል – የሕዋው “አቅም ገንቢ” ተፌ! (ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®)

አዲስ አበባ ውስጥ ሌሊት የሚለጠፉ ወረቀቶችን ተከትሎ ውጥረት ነግሷል


“መረጃ ለአንድ ለአምስት ማቀበል አለባችሁ” ፖሊስና ካድሬዎች

addis p

  • የበር መብራት ማጥፋት ክልክል ነው፤ በሕግ ያስቀጣል
  • “መውጫና መግቢያ ሰዓታችሁ መመዝገብ ይጀመራል ተብለናል” ነዋሪዎቹ
ከትናንት በስቲያ በጨርቆስ አካባቢ አንድ ሰው በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድሎ መገኘቱን እና ሌሊት ላይ በቦሌ አካባቢ የተለያዩ የመብት ጥያቄዎችን የሚያስተጋቡ ወረቀቶች በየግድግዳውና የኤሌክትሪክ ምሶሶ ላይ ተለጥፈው መገኘታቸውን ተከትሎ በከተማዋ ውጥረት መንገሱን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

“አንድ የጨርቆስ አካባቢ ነዋሪ ተገድሎ መገኘቱን ተከትሎ ‹የጨርቆስ ወጣቶች› ተሰባስበው ይህን ድርጊት ይፈጽሙ ይሆናል ብለው በገመቱት ላይ ቁጣቸውን ገልጸው ነበር፡፡ በተለምዶ ካታንጋ ወደሚባል ስፍራ ሄደው ገዳዩን አውጡ ብለዋል፡፡ መኪኖችን ሰባብረዋል፡፡ ካታንጋ ምንም ፍንጭ ሲያጡ ወደ ፊላሚንጎ አምርተዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ፖሊስ የተወሰኑትን ይዟል፤ ያመለጡም አሉ፡፡ እስካሁንም ውጥረቱ አለ” ስትል አንዲት የአካባቢው ነዋሪ ለነገረ ኢትዮጵያ ተናግራለች፡፡
ቀደም ብሎ ተለጥፎ በተገኘው ወረቀትና በሟቹ ምክንያትም ፖሊስና የኢህአዴግ ካድሬዎች የተለያዩ ጫናዎችን በነዋሪዎች ላይ ማሳደር መጀመራቸው ታውቋል፡፡ “ለስድስት ወራት ችላ ብለውት የነበረው የአንድ ለአምስት አደረጃጀት ስብሰባ አሁን እንደገና ጀምረውታል፡፡ አደረጃጀቱ ስራውን ካቆመና ስብሰባ ካደረግን 6 ወራት አልፈውት ነበር፡፡ ከትላንት ጀምሮ ግን በግዳጅ ጀምረውታል” ሲሉ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
ምንጮች አክለው እንዳስታወቁት ነዋሪዎችን ፖሊስና ካድሬዎች በስብሰባ በመያዝ የተለያዩ የማሳመኛ ሰበቦችን እንደሚያነሱ ተገልጾአል፡፡ “ምርጫ ደርሷልና አብረን እንስራ፡፡ 97 የሆነውን ታውቃላችሁ፡፡ ያ እንዲሆን አንፈልግም፡፡ ስለሆነም ሙሉ ሌሊቱን በራችሁ ላይ መብራት ማብራት አለባችሁ፤ የተከራይ መታወቂያ ማየት አለባችሁ፡፡ እያንዳንዷን መረጃ ለፖሊስና ለአንድ ለአምስት አደረጃጀቱ ማቀበል አለባችሁ” እንዳሏቸውም ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
በየስብሰባዎቹ በአብዛኛው የሚገኙት ሴቶች መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ነዋሪዎች በግዳጅ በተፈጠሩት የአንድ ለአምስቱ አደረጃጀቶች መሪ ለመሆን የሚፈልግ አለመኖሩንም ምንጮች ተናግረዋል፡፡
“እያንዳንዱ ሰው የሚወጣ የሚገባበትን ሰዓት መመዝገብ ይጀመራል ተብለናል” የሚሉት ነዋሪዎቹ፣ “አከራዮች ተከራዮቻችሁ የሚገቡበትን ሰዓት ገደብ ማስቀመጥ አለባችሁ፤ የበር መብራቱንም ማጥፋት ክልክል ነው፡፡ ሌሊቱን ሙሉ መብራት ያላበራ ይቀጣል፤ ፍርድ ቤት ሁሉ ሊቀርብ ይችላል” ተብሎ በየስብሰባዎቹ እንደተነገራቸው የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ጨምረው አስረድተዋል፡፡ (ምንጭ፡ ነገረ ኢትዮጵያ

ባለፉት 23 ዓመታት ውስጥ በልጆቻቸው መታሰር በፅኑ ሃዘን የተወጉትን እናቶች ማሳያ የሆኑት 70 ዓመታት ያለፋቸው የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እናት ተመስገን በተፈረደበት ዕለት የነበሩበትን ሁኔታ የተመስገን ወንድም እንደፃፈው (ኦድዮ) ያድምጡት

Monday, October 27, 2014

ወያኔ ሲያስር አሜን….ሲገድልም አሜን በኤፍሬም ማዴቦ October 8th, 2014


ብዕር የያዘ ማንም ሰዉ በዘመናችን ደግሞ የኮምፒተር መክተቢያ ፊቱ ላይ የደቀነ ሁሉ ከሱ ዉጭ ያለዉን ማንንም ሰዉ “ሌባ”፤ “ባንዳ” ወይም “ከሃዲ” እያለ እንዳሰኘዉ መጻፍ ይችላል። በተለይ በእንደኛ አይነቱ ሀላፊነትም ተጠያቂነትም በሌለበት ህብረተሰብ ዉስጥ ደግሞ የጓደኛዉ ሀሳብ ያልተስማማዉ ሁሉ እየተነሳ የገዛ ጓደኛዉን ባንዳና ከሃዲ አድርጎ ስለሚስለዉ የላይ የላዩን ብቻ ለሚመለከት ሰዉ አገራችን በባንዳና በአገር ወዳድ መሳ ለመሳ ለሁለት የተከፈለች ትመስላለች። እግዝአብሄር ይመሰገን እዉነቱ ግን ከዚህ እጅግ በጣም የተለየ ነዉ። ርዕሴን የጀመርኩት አሜን ብዬ ነዉና እስኪ አንባቢዉ አንተም አሜን በል። ባንዳነትና ከሃዲነት ኃብታምና በእድገት ወደፊት የገፉ አገሮችን እየዘለለ ደሃና ኋላ ቀር አገሮችን ብቻ የሚጠናወት ተራ በሽታ አይደለም። ብዙዎቻችን አምባገነን መሪዎቻችንን ሸሽተን የተጠለልንባት አገር አሜሪካ እነ ሄንሪ ቤስትንና ጆን ብራዉንን የመሳሰሉ ከሃዲዎችን እንዳበቀለች ሁሉ ኢትዮጵያችንም ትናንት እነ ኃ/ሥላሤ ጉግሳን ዛሬ ደግሞ የኃ/ሥላሤ ጉግሳ የልጅ ልጆች የሆኑትን እነ መለስ ዜናዊን፤ አባይ ፀሐዬንና ሰብሃት ነጋን የመሳሰሉ የለየላቸዉ ከሀዲዎችን አፍርታለች። በነገራችን ላይ ሙስሊሙ በዱአዉ፤ ክርስቲያኑ በፀሎት፤ ጠቢብ በጥበቡ ፤ፀሐፊ በምናቡ የባንዳዉንና የከሃዲዉን ብዛት ለመቀነስ ካልተባበሩ በቀር “ወላድ በድባብ ትሂድ” ብለን ባንመርቃቸዉም የባንዳ አባትና አናት አስካሉ ድረስ ባንዳም መወለዱ አይቀርም።
ደጅአዝማች ኃ/ሥላሤ ጉግሳ ማንም ሳያስገድደዉ ወድዶና ፈቅዶ ለወራሪዉ የጣሊያን ጦር ካደረ በኋላ ከጄኔራል ደቦኖ ጋር ሆኖ እናት አገሩን ኢትዮጵያን ወግቷል። ጣሊያኖች ኃ/ሥላሤ ጉግሳ ከነተከታዮቹ ከጎናቸዉ ተሰልፎ አገሩን ሲወጋ ያደረጉት የመጀመሪያዉ ነገር ይህ ከሃዲ ሰዉ ከጎናቸዉ መሰለፉን የሚያሳዩ ፎቶግራፎች ለዓለም ህዝብ ማሰራጨት ነበር። ታሪክ እራሱን ይደግማል ሲባል አይኑ አላይ እያለዉ በጆሮዉ ብቻ ለሰማ ሰዉ ዛሬ ማረጋገጫዉ እነሆ በግልጽ ቀርቦለታል። ትናንት ማክሰኞ መሰከረም 27 ቀን የወያኔ ቴሌቭዥንና ሬድዮ ኢትዮጵያ ዉስጥ በጋዜጠኞች ላይ የሚፈፀመዉን እስርና ስደት፤ ወያኔ በወገኖቻቸን ላይ የሚፈጽመዉን የዕለት ከዕለት ሰቆቃና እንዲሁም በቅርቡ አምቦና ኦጋዴን ዉስጥ የተካሄዱትን የጅምላ ግድያዎች የሚደግፉ የዚህ ዘመን ኃ/ሥላሤ ጉግሳዎች ዋሺንግተን ዲሲ ዉስጥ ያካሄዱትን የክህደት ሰለማዊ ሠልፍ በተደጋጋሚ ለህዝብ አቅርበዋል። እነዚህ ትናንት ክቡር ባንዲራችን በአለባሌ ሰዉ አንደበት “ጨርቅ” ተብላ ስትሰደብ ከተሳዳቢዉ ሰዉ ጎን ቆመዉ የሳቁና የተሳለቁ ከሃዲ ሆድ አምላኪዎች ዛሬ “ባንዲራችን ተደፈረ” ብለዉ የአዞ እምባ ያነቡብናል። የትኛዉ ባንዲራ? ለመሆኑ እነዚህ “እናቴን ያገባ ሁሉ አባቴ ነዉ” ባዮች ጀግናዉ ዘርዐይ ደረስ ጣሊያኖችን በራሳቸዉ አደባባዮች አንገታቸዉን በጎራዴ የቀላዉ ለዬትኛዉ ባንዲራ እንደሆነ ያዉቃሉ? እነ አብዲሳ አጋ፤ በላይ ዘለቀ፤ ባልቻ አባ ነብሶና እልፍ አዕላፋት የኢትዮጵያ ልጆች ምትክ የሌላትን ህይወታቸዉን የሰጡት ለዬትኛዉ ባንዲራ አንደሆነ ያዉቃሉ?
እነዚህ ወያኔ አዲስ አበባ ዉስጥ የገዛ ወገኖቻዉን ሲያስርና ሲገድል አሜን ብለዉ ዋሺንግተን ዲሲ ዉስጥ ሠላማዊ ሠልፍ የሚወጡ የለየላቸዉ ከሃዲዎች ባንዲራ አዲስ መንግስት በመጣ ቁጥር እንደ ፖሊሲና እንደ ካቢኔ ሚኒስቴር የማይቀያየር ቋሚ የአገር ማንነትና የትዉልድ ትስስር መታወቂያ መሆኑን ሊገነዙ ይገባል። ባንዲራ ምክንያታዊ በሆነ መልኩ ሊቀየር ይችላል ብለን ብናስብ እንኳን ምን አይነት ሰዎች ብንሆን ነዉ ባንዲራን የመሰለ ህዝብና አገር ማስተሳሰሪያ ማተብ ኢትዮጵያንና ታሪኳን ከልቡ ለሚጠላዉ መለስ ዜናዊና የትግራይ ሪፓብሊክ ካላቋቋምኩ ብሎ ይታገል ለነበረዉ ለከሃዲዉ ስብሀት ነጋ የምንተዉላቸዉ? ደግሞም እነዚህ ምናምንቴዎች አንደሚሉት ባንዲራችን ላይ ባዕድ አካል ሆኖ የተለጠፈዉና የኢትዮጵያ ህዝብ በተለምዶ “ባላ አምባሻዉ” እያለ የሚጠራዉ የወያኔ ጨርቅ እዉነትም ኢትዮጵያ ዉስጥ የብሄር ብሄረሰቦችን እኩልነት አረጋግጦ ቢሆን ኖሮ ዛሬ አገራችን በየቀኑ ብሄር ብሄረሰቦች ዉጣልኝ አልወጣም እየተባባሉ የሚተላለቁባት አገር አትሆንም ነበር። አባቶቻችን የሞቱት ለአረንጓዴ፤ ብጫና ቀይ ባንዲራ ነዉ፤ እኛም ዛሬ በየተሰደድንበት አገር አገሬን እያሰኘ የሚያስጮኸን ይሄዉ አረንጓዴ፤ ብጫ ቀይ ባንዲራችን ነዉ። አገር ቤት ያለዉ ኢትዮጵያዊም አንዱን “ባላአምባሻዉ” ሌላዉን ደግሞ ባንድራዬ እያለ የሚጠራዉ ይህንኑ አረንጓዴ፤ ብጫና ቀይ ባንዲራዉን ነዉ። በአንዲት አገራችን ኢትዮጵያ ዉስጥ እነሱም እኛም ለየቅላችን የኛ የምንለዉ ባንዲራ ሊኖር በፍጹም አይችልም። ይልቅ ወያኔዎች ሲጠፉ እነሱ ይዘዉብን የመጡት ኮተቶ ሁሉ አብሯቸዉ መጥፋቱ አይቀርምና ዛሬ “ባንዲራችን ተደፈረ” ብላችሁ የምታቅራሩ እዉሮች ነገ ከወያኔ በጸዳችዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ጭራሽ ባንዲራ ላይኖራችሁ ይችላልና መጀመሪያ ከራሳችሁ ጋር ቀጥሎም ከአገራችሁ ከኢትዮጵያ ጋር እንድትታረቁ አጥብቄ እማጸናችኋለሁ።
የወያኔን ቂልነትና ባዶነት በሰብኩ ቁጥር ትዝ የምትለኝ አንዲት ቀልድ ብጤ አለችና እስኪ ለፈገግታ ትሆናለችና አዳምጡኝ። ሁለት አመት የፈጀዉ የኤርትራና የኢትዮጵያ አላስፈላጊ ጦርነት እንዳለቀ በጦርነቱ ወቅት ስንቅና ትጥቅ በማመላለስ ትልቅ ዉለታ የዋለች ኣንዲት አህያ ጦርነቱ አብቅቶ የድል በዐል ሲከበር መስቀል አደባባይ ተጋብዛ መለስ ዜናዊ ፊት ትቀርባለች፤ በቋንቋ ይግባቡ ነበርና መለስ ጎንበስ ብሎ በጆሮዋ አንድ ነገር ሹክ ሲላት አህይት በደስታ እየፈነጠዘች አደባባዩን መዞር ጀመረች። በልማታዊ አህይት ዝላይና ፍንጠዛ ግራ የተጋቡት የወያኔ ጋዜጠኞች ዜና ያገኙ መስሏቸዉ “ታላቁ መሪ” ምን አለሽ ብለዉ አህይትን ጠየቋት። የዕድሜ ልክ የህወሓት አባል ሆነሻል ተብያለሁ ብላ አህይት ዝላይዋንና ፍንጠዛዋን ቀጠለች።
ትናንት እዚህ ዋሺንግተን ዲሲ ዉስጥ የወያኔን ጭፍጨፋ፤ እስርና በዘር መድሎ የተጨማለቀ ስርዐት አበጀህ ቀጥልበት ብለዉ አደባባይ የወጡ ጥቂት ህሊና ቢሶችና እነሱን አመስግኖ የነጻነት አርበኞችን “ዱሪዬዎች” ብሎ የዘለፈዉ የአድር ባዮች ሁሉ አድርባይ የሆነዉ ግርማ ብሩ ከዚያች ባድመ ላይ ብዙ ስንቅና ትጥቅ ካመላለሰችዉ ጎበዝ አህያ የሚለዩበት መንገድ ቢኖር አህያዋ ማሰብ ስለማትችል አለማሰቧ እነሱ ግን ማሰብ እየቻሉ አለማሰባቸዉ ብቻ ነዉ። በተረፈ እነሱም አህያዋም የወያኔ አባልነታቸዉ ያስደስታቸዋል፤ ምክንያቱም ሁለቱም አያስቡም። መቼም የገዛ ወንድሙና እህቱ ሲታሰሩ፤ ሲደበደቡና ሲገደሉ አሜን ብሎ ተቀብሎ ነብሰ ገዳዮችን ደግፎ ሰላማዊ ሠልፍ የሚሰለፍ የሰዉ ዘር ያለዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ብቻ መሆን አለበት። ለዚያዉም በወያኔ ዘመን ብቻ!
እነዚህን ሆዳሞች ደግሜ ደጋግሜ እዉሮች እያልኩ የምጠራቸዉ አለምክንያት አይደለም። በእርግጥም ስለማያዩ ነዉ። ባለፈዉ ወር አዚህ አሜሪካ ሚዙሪ ግዛት ፈርግሰን የሚባል ከተማ ዉስጥ ከባድ መሳሪያ የታጠቁ ፖሊሶች መሳሪያቸዉን ሰላማዊ ሰልፈኛዉ ላይ ስላዞሩ (ልብ በሉ ስላዞሩ ነዉ ያልኩት እንጂ ስለተኮሱ አላለኩም እነሱም አላደረጉትም) የአሜሪካ ህዝብ፤ መሪዎችና የህዝብ ተወካዮች ምን ያህል እንደተንጫጩ ሁላችንም ተመልክተናል። እነዚያ እዉሮች ያልኳቸዉ ወንድሞቻችንም እኛ የተመለከትነዉን ተመልክተዉት ይሆናል፤ ግን እነሱ የአዕምሮ እዉራን ናቸዉና ስዕሉን ብቻ ነዉ እንጂ ቁም ነገሩን አላዩትም። ስለዚህም ነዉ የነሱ ድፕሎማት ተብዬዉ ድንጋይ ራስ (ርዕስ እምኒ) አዲስ አበባ ዉስጥ ያለ መስሎት ሠላማዊ ሠልፈኛ ለመግደል ደጋግሞ ሲተኩስ አበጀህ ብለዉ ሠላማዊ ሠልፍ የወጡለት። እግዚአብሄር ከዚህ አይነቱ የአዕምሮ እዉርነት ያድነን! እባካችሁ አሁንም አሜን በሉ። እኔ እያረረ የሚስቅ ማሽላ ብቻ ይመስለኝ ነበር . . . . ለካስ የገዛ ወገኖቹ ሲገደሉ ደስ ብሎት የሚስቅ ሰዉም አለ። አቤት እግዚኦ!!!!
ሌላዉ የገረመኝ ነገር ቢኖር እነዚህ የአዕምሮ እዉራን ትናንት ረፋዱ ላይ ለአሜሪካዉ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጆን ኬሪ በጻፉት ደብዳቤ ግንቦት 7 ያ እንቅልፋም ፓርላማቸዉ “ሽብርተኛ” ብሎ የፈረጀዉ ድርጀት ነዉና ምነዉ ዝም ብላችሁ ታያላችሁ ብለዉ ኬሪን መወትወታቸዉ ነዉ። ኬሪ እንደነሱ ጨካኝና አምባገነን መሪዎች የማይወደዉንና የሚጠላዉን ሁሉ አይንህ አላማረኝም እያለ ማሰር የሚችል መስሏቸዋል። እነዚህ ሆዳቸዉ ልባቸዉን የሸፈነ ከሃዲዎች አይገባቸዉም አንጂ የነሱን “ግንቦት ሰባቶችን” እሰሩልን ብሎ ጥያቄ እንኳን ኬሪ የአለማችን ሀይለኛዉ መሪ አባማም ማስተናገድ አይችልም። እኛስ ብንሆን የምንታገላቸዉ ለዚሁ ነዉኮ – ኢትዮጵያን የሚመራ ሁሉ ሀሳባችን ከሀሳቡ በተጋጨ ቁጥር አንዳያስረንና እንዳይደገድለን። እኔኮ ምን ይሻለኛል . . . . በአንድ በኩል ኢትዮጵያዉያን የወገኖቻቸዉን መገደል ተቃዉመዉ ሠላማዊ ሠልፍ ሲወጡ የወያኔዉ ተላላኪ ግርማ ብሩ የኤርትራን መንግስት ይከስሳል፤ የአይጥ ምስክር ድንቢጥ እንዲሉ የግርማ ብሩ ተላላኪዎች ደግሞ (የተላላኪ ተላላኪ ማለት ነዉ) ግንቦት ሰባት የሚረዳዉ በኤርትራ መንግስት ነዉና ስጋታችንን እዩልን እያሉ ኬሪን ይለማመጡታል። መቼም አዉቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይነቃም ነዉና የወያኔ ደጋፊዎች አይገባቸዉም አንጂ ለሻዕቢያ ጎንበስ ቀና እያሉና የሻዕቢያን መሪዎች እንደ ታቦት እየተሳለሙ ለዚህ ዛሬ ላሉበት ደረጃ የበቁት የወያኔ መሪዎች ናቸዉኮ። ዛሬ በባነኑ ቁጥር አንዴ ግንቦት ሰባት አንዴ ሻዕቢያ እያሉ ዛር እንደያዘዉ ሰዉ የሚያጓሩትም ተደምስሰዉ ከታሪክ ምዕራፍ የሚፋቁት በዚሁ እንደ ህጻን ልጅ እጃቸዉን ይዞ ለታሪክ ባበቃቸዉ በሻዕቢያ በኩል መሆኑን በሚገባ ስለሚያዉቁት ብቻ ነዉ። ምድረ የወያኔ አጎብጋቢዎች ዛሬ እቅጩን ልንገራችሁ፤ ወደዳችሁም ጠላችሁ ይህ “ልማታዊ” ብላችሁ የምትጠሩት ነብሰ ገዳይ አገዛዝ ይደመሰሳል- ስጋታችሁ ትክክለኛ ስጋት ነዉ። ግን ከዚህ ስጋት የሚያድናችሁ ኬሪ ሳይሆን የራሳችሁ ሂሊና ብቻ ነዉና ሳይዉል ሳያድር ዛሬዉኑ ኑና ከህዝብ ጎን ተሰለፉ፤ አለዚያ ዕድላችሁ ከኑግ የተገኘህ ሰሊጥ አብረህ ተወቀጥ ይሆናል። መቼም እንደኔዉ የዚያች ምስኪን አገር ልጆች ናችሁና በተረት ብነግራችሁ ይገባችኋል ብዬ ነዉ እንጂ በእናንተና መወቀጥ በሚገባዉ ኑግ መካከል ምንም ልዩነት የለም።
የዘረኞቹ የወያኔ መሪዎችና እንደ ችግኝ ኮትኩተዉ ያሳደጓቸዉ ቡችሎቻቸዉ አስቂኝ ታሪክ በዚህ ብቻ አያበቃም፤ እነዚህ ጣምራ ጉደኞች ብዙ ተነግሮ የማያልቅ ጉድ አላቸዉ። ወያኔዎች ጋዜጠኛ እያሰሩና ከአገር እንዲሰደድ እያደረጉ ተዉ ያላቸዉን ፀረ አገርና ፀረ ልማት ይሉታል፤ በየሰላማዊ ሠልፉ ላይ ንጹህ ዜጎችን በጅምላ ሲጨፈጭፉ ምነዉ ያላቸዉን ደግሞ ሽብርተኛ ብለዉ ያስሩታል። እነዚህ አረመኔዎች ይህንን የመሰለ ለጆሮ የሚቀፍ ወንጀል በህዝብና በአገር ላይ ፈጽመዉ ሰዎች በነጻነት ወደሚኖሩበት አገር ሰዉ መስለዉ ሲመጡና ስንቃወማቸዉ ደግሞ እዚህ ዉጭ አገር ያስቀመጧቸዉ ተናካሽ ዉሾቻቸዉ “ኢትዮጵያዊ ጨዋነት” የጎደላቸዉ ብለዉ ይዘልፉናል። ለመሆኑ ለእነዚህ እንደ ዉሻ ቁራሽ ስጋ በተወረወረላቸዉ ቁጥር ለሚያላዝኑ ምናምንቴዎች ማነዉ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት እንደነሱ ነዉርን አሜን ብሎ መቀበል ብሎ የነገራቸዉ? ዜጎችን አንደ እንስሳ አየጎተቱ ገድለዉ አስከሬኑን በሟቹ ወንድም እያስጎቱና ይህንን ነዉር በቪድዮ እየቀረጹ መሳቅና መሳለቅ ነዉ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ወይስ ይህንን ኔሮና ሂትለር ምን አደረጉ የሚያሰኝ ጭካኔና አረመኔነት መቃወም ነዉ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት? አዲስ አበባ ዉስጥና እዚህ ዋሺንግተን ዲሲ ዉስጥ ተቃዋሚ ኃይሎችን “ኢትዮጵያዊ ጨዋነት” የጎደላቸዉ ብለዉ የዘለፉት ሬድዋን ሁሴንና ግርማ ብሩ የዉኃ ጠብታን ያክል ኢትዮጵያዊ ጨዋነት በደማቸዉ ዉስጥ ቢኖር ኖሮ “ኢትዮጵያዊ ጨዋነት” የኢትዮጵያዉያንን ህይወት በየአደባባዩ መቀማት አይደለምና እናከብራቸዉ ነበር እንጂ በወጡና በገቡ ቁጥር ስማቸዉን እየጠራን ሌባና ከሃዲ እያልን አናሸማቅቃቸዉም ነበር። ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ስንታሰርና ስንዋረድ እልል፤ ስንገደል ደግሞ አሜን ብለን እንደ በሬ አንገታችንን ለቢለዋ መስጠት ማለት አይደለም። ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ለወገን ማዘን ነዉ፤ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ወገን ሲጎዳና ሲጠቃ ከለላ መሆን ነዉ። ከሁሉም በላይ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ዜጎች ሰቆቃ ሲፈጸምባቸዉና ሲገደሉ ቆሞ ከመመልከት ይልቅ ወይም የገዳዮች ጠበቃ ከመሆን ባጭር ታጥቆ ነብሰ ገዳዮችንና የጭካኔ ምልክቶችን ከአገር አናትና ከህዝብ ጀርባ ላይ ማስወገድ ነዉ – ወላድ በድባብ ትሂድ – ይህንን የሚያደርጉ የቁርጥ ቀን ልጆች እናት ኢትዮጵያ ትናንንት ነበሯት፤ ዛሬ አሏት ነገም ይኖሯታል።

Thursday, October 23, 2014

ሰበር ዜና – በምዕ. ወለጋ በቤተ ክርስቲያን ላይ በሚፈጸመው ግፍ ፓትርያርኩ መንግሥትን አሳሰቡ


  • የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ጉዳዩን በጥብቅ ይነጋገርበታል
  • በመንግሥት ባለሥልጣናት ስለሚፈጸሙ በደሎች ከአህጉረ ስብከት የሚቀርቡ አቤቱታዎች የፍትሕ አካሉን አፋጣኝ ውሳኔ ያገኙ ዘንድ ቅ/ሲኖዶሱ ግፊት እንዲያደርግ አጠቃላይ ጉባኤው ዐደራ ጥሎበታል
  • አህጉረ ስብከት ያቀረቧቸውን የአስተዳደር፣ የፍትሕና የጸጥታ አካላት በደሎችና ተጽዕኖዎች አጣርቶ መፍትሔ የሚሰጥ÷ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት፣ ከሃይማኖት ተቋማት ጉባኤና ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የተውጣጣ ኮሚቴ እንዲዋቀር አጠቃላይ ጉባኤው በአቋም መግለጫው ጠይቋል
  • ‹‹ይህ ዐይነቱ ጊዜ የማይሰጠው ችግር ወደ ሌላ ከመዛመቱ በፊት አፋጣኝ መፍትሔ ማግኘት አለበት፡፡›› /የ፴፪ው አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የአቋም መግለጫና የውሳኔ ሐሳብ/
  • ‹‹ድርጊቱ የመቻቻልን ሕግ እያፈረሰ ነው፤ በአካባቢው ያለው መንግሥታዊ አስተዳደር ሊያስብበት ይገባል፡፡›› /ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ/
  • የምዕ/ወለጋ ሀ/ስብከት በሪፖርቱ የዘረዘራቸውን ችግሮች ከዘገባው በታች ይመልከቱ
His Holiness Abune Mathias0000በምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት በቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰ ባለው ፈታኝ ችግር በአካባቢው ያለው መንግሥታዊ አስተዳደር ሊያስብበት እንደሚገባ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አስጠነቀቁ፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ማሳሰቢያውን የሰጡት የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌል አዳራሽ ከጥቅምት ፬ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ጀምሮ ለሰባት ቀናት ሲያካሂድ የሰነበተውን ፴፪ ዓመታዊ ስብሰባውን ዛሬ፣ ጥቅምት ፲ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ቀትር ላይ ባጠናቀቀበት ወቅት ባሰሙት የመዝጊያ ንግግር ነው፡፡
‹‹በምዕራብ ወለጋ ዐይን ያወጣ፣ ይሉኝታ የሌለው ግፍ እየተፈጸመ ነው፤›› ያሉት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በካህናትና ምእመናን ላይ፣ በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚፈጸመው ግፍ ‹‹በዚያ አካባቢ መንግሥት አለ ወይ ያሰኛል?›› በማለት ነው በአስተዳደር፣ የፍትሕና የጸጥታ አካላት የሚፈጸመውን በደልና ተጽዕኖ የገለጹት፡፡
‹‹ድርጊቱ የመቻቻልን ሕግ እያፈረሰ ነው፤›› ያሉት ፓትርያርኩ በአካባቢው ያለው የመንግሥት አስተዳደር ሊያስብበት እንደሚገባ በቃለ ምዕዳናቸው አስጠንቅቀዋል፤ በጉዳዩ ላይ ከጥቅምት ፲፪ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ጀምሮ የሚካሄደው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በአጀንዳነት ይዞ በጥብቅ እንደሚነጋገርበትም አመልክተዋል፡፡
በሌላ በኩል ባለ36 ነጥቦች የአቋም መግለጫና የውሳኔ ሐሳብ በማውጣት ዓመታዊ ስብሰባውን ያጠናቀቀው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ፣ እንደ ምዕራብ ወለጋ ባሉ አህጉረ ስብከት በቤተ ክርስቲያን ላይ እየተከሠቱ ያሉ ችግሮች ፈታኝ መኾናቸውንና በቤተ ክርስቲያን ልማትና በሐዋርያዋ አገልግሎቷ የመጠናከር ጥረት ላይ ተጽዕኖ ማድረሳቸውን በአቋም መግለጫው ላይ በአጽንዖት አስፍሯል፡፡ የምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከትን ሪፖርት በአብነት የጠቀሰው መግለጫው፣ በሀገረ ስብከቱ፡-
  • በየትምህርት ቤቱ የሚማሩ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ የኾኑ ወጣቶች እምነታቸውን የሚያስለውጥ ዘዴ በመጠቀም ቅስቀሳ የማካሄድ፤
  • በጠመንጃ አፈ ሙዝ እያስፈራሩ የድብደባ ወንጀል የመፈጸም፤
  • በቤተ ክርስቲያን ስም የተተከለውን የዕጣን አዙርና የዓመታውያን በዓላት ማክበርያ ቦታዎችን እየነጠቁ ለሌላ እምነት ተከታዮች አሳልፎ የመስጠት፤
  • የተሠራውን ቤተ ክርስቲያን ለማፍረስ ሙከራ የማድረግ፤
  • ባልተጠበቀ የትንኮሳ መንገድ እየተጓዙ እስከ ነፍስ ግድያ የሚያደርስ ከባድ የወንጀል ድርጊት በእምነታችን ተከታዮች ላይ እንዲደርስ የማድረግ፤
ከባድ የወንጀል ድርጊት በሕገ ቤተ ክርስቲያን በቃለ ዐዋዲው የቤተ ክርስቲያናችን መተዳደርያ ደንብ የተቀመጠውን ድንጋጌ ይልቁንም ሕገ መንግሥቱን እንደሚጥስ አመልክቷል፡፡ የሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት በጉዳዩ ላይ የሕግ ክትትል እያደረገ መኾኑ ቢታወቅም፣ ይህ ዐይነቱ ጊዜ የማይሰጠው ችግር ወደ ሌላ ከመዛመቱ በፊት አፋጣኝ መፍትሔ ማግኘት እንዳለበት አሳስቧል፡፡ በመኾኑም ቅዱስ ሲኖዶስ በምልአተ ጉባኤው፣ በምዕራብ ወለጋ ሀ/ስብከት የተከሠተውንም ኾነ ከሌሎች ተመሳሳይ ችግር ካለባቸው አህጉረ ስብከት የሚቀርቡለትን አቤቱታዎች በመቀበል በሚመለከተው የፍትሕ አካል እንዲያስወስን አጠቃላይ ጉባኤው ታላቅ ዐደራ ጥሎበታል፡፡SGGA wound up
የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ‹‹የሃይማኖት መቻቻል›› በሚለው የአጠቃላይ ጉባኤው መርሐ ግብር ላይ ‹‹የብዝኃነት አያያዝ፣ አክራሪነት/ጽንፈኝነት ዝንባሌዎቹና መፍትሔዎቹ›› በሚል ርእስ በሦስት ተወካዮቹ አማካይነት ሰፊ ገለጻ ማቅረቡን ያስታወሰው የአቋም መግለጫው፣‹‹በሃይማኖት መቻቻል ዙሪያ የደረሰውና እየደረሰ ያለው ጥፋትና ጉዳት በማስረጃ የተደገፈ ኾኖ ሲቀርብ ጉዳዩ በሚመለከተው የፍትሕ አካል እየተመረመረ እንደሚወሰን፣ በሌላም በኩል እንደ አሁኑ የቤተ ክርስቲያኒቱን ህልውና የሚፈታተን ችግር ሲያጋጥም በኢትዮጵያ የሃይማኖትተቋማት ጉባኤ በኩል እየቀረበ መፍትሔን ማግኘት እንደሚችል›› በተወካዮቹ መገለጹን አትቷል፡፡
በዚሁም መሠረት ክትትሉ እንዲቀጥልና ለችግሮቹ እልባት እንዲደረግላቸው÷ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት፣ ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የተውጣጣ ኮሚቴተዋቅሮ ጉዳዮቹ እንዲጣሩና የመጨረሻ መፍትሔ በአስቸኳይ እንዲሰጣቸው ይደረግ ዘንድ ቅዱስ ሲኖዶስ የአፈጻጸም ውሳኔ እንዲሰጥ ጉባኤው በከፍተኛ ድምፅ ጠይቋል፡፡
*                         *                     *
የምዕራብ ወለጋ ሀ/ስብከት ለአጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው ዓመታዊ ስብሰባ ባቀረበው ሪፖርት በሀ/ስብከቱ መንግሥታዊ የአስተዳደር፣ የፍትሕና የጸጥታ አካላት ስለሚፈጸሙ በደሎችና ተጽዕኖዎች የዘረዘራቸው ችግሮች፤
1)  መናፍቃን ባላቸው የገንዘብ ድጋፍ እንዲሁም በፖሊቲካና የመናፍቃን አባላት በኾኑ ባለሥልጣናት በመደገፍ በሥነ ልቡና ጦርነት ሕዝቡን መንጠቅ፤
2)  የቤተ ክርስቲያን የዕጣን አዙር መሬት ክልል በመናፍቃን መደፈር፣ በክሥ ለከፍተኛ ወጪ መዳረግ፤
3)  መናፍቃን መምህራን በትምህርት ቤት ከሕፃናት አንገት ማዕተብ መበጠስ፣ ማሰር አይቻልም የሚል የሌለ መመሪያ ማውጣት፤
4)  በባቦ ገምቤል ወረዳ ሓላፊነት በማይሰማቸው የፖሊስ ሠራዊት ምእመናን ተደብድበው ከአንገታቸው ማዕተብ መበጠስ፣ ወጣቱ በቅድስቲቷ እምነት እንዲያፍር ማድረግ፣ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደር፤
5)  ካህናት በጸሎተ ቅዳሴ አገልግሎት ላይ ሳሉ በወረዳው ባለሥልጣናት ተይዘው እስር ቤት መወሰድ፣ ቤተ ክርስቲያኑ ያለቊልፍ ውሎና አድሮ በሕዝብ መጠበቅ፤
6)  የካህናት በባለሥልጣናት ትእዛዝ መንበርከክ፣ መቀጥቀጥ፣ ለከፍተኛ ኢ-ሰብአዊ አደጋና ሥቃይ መዳረግ፤
7)  በዕለተ ሰንበት ካህናት አገልግሎት ላይ እያሉ ምእመናንን ‹‹ውጡና ወደ ስብሰባ ሂዱ፤ ለቅዳሴ ቄሶች ይበቃሉ›› ከማለት አልፎ ጥዋት ከኪዳን መልስ መኪና መንገድ ላይ አቁመው የ10 ዓመት ዕድሜ ካላቸው የሰንበት ት/ቤት አዳጊዎች ጀምሮ በመኪና ጭነው ወደ ቀበሌው እስር ቤት መውሰድ፤
8)  በቅዱስ ሚካኤል የወርኃዊ መታሰቢያ በዓል ከቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ጎን የእርሻ ቀን አድርገው በማመቻቸት ‹‹በአማራ አገር ቄሶች ጥላ ይዘው ገበሬ ማኅበር እርሻ ላይ ተገኝተው ያሳርሳሉ›› በማለት ቅዳሴ እየተቀደሰ አንድን ቄስ በማስገደድ ጥላ ይዘው እንዲወጡ አስገድደዋል፡፡ በዚህም የቤተ ክርስቲያኑ አገልግሎት እንዲስተጓጎል፣ በቤተ ክርስቲያኑ አካባቢ የመናፍቃንና የሙስሊም አባላት በልማት አስመስለው በሆታና በጫጫታ በመረበሽ ካህናቱ ተደማምጠው ቃለ እግዚአብሔሩን እንዳያደርሱ ማወክ፤
9)  ‹‹የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሰፊ ቦታ ይዛ ሌላው በጠባብ መቸገር የለበትም›› በማለት የቤተ ክርስቲያኑን አጥር አስፈርሰው መስጊድ እንዲሠራ መፍቀድ፤
10)   አንድ ሙስሊም ሚልሻ የካህኑን ሚስት ከማሳ ላይ ይዞ ‹‹ባልሽ ያለበትን ቦታ አሳይኝ›› ብሎ በማስገደድ ካህኑ በዐቢይ ጾም በቤተ መቅደስ በውሎ ቅዳሴ በማገልገል ላይ እያሉ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብቶ ካህኑን በመስኮት በኩል ባለቤታቸውን እያሳየ ማሣቀቅ፤
11)   በወረዳ አስተዳደሩ መምሪያ የቀበሌ ሥራ አመራር አባላት፣ በዐቢይ ጾም ወቅት ካህኑን አስገድደው ለስብሰባ ወስደው በቅዳሴ ሰዓት አትሄድም ብለው ከቅዳሴ ማስቀረትና አገልግሎቱን ማስታጎል፤
12)   ምእመናን አባቶች በእርሻ ላይ እያሉ ፖሊሶች፣ ‹‹እዚህ አካባቢ የኦርቶዶክስ ቤተ እምነት የት ነው፤ አሳየን?›› ሲሉ ‹‹እኔ አላውቅም›› ሲሏቸው እርሻቸው ከመኖርያ ቤታቸው አጠገብ ነበርና  አንበርክከው በዱላ ደብድበዋቸዋል፡፡ ለኻያ ደቂቃ ወደ ፀሐይ አንጋጥጠው እንዲያዩ አድርገዋቸዋል፡፡ ይህን አይተው የተደናገጡት ባለቤታቸው ምርር ብለው እያለቀሱ ወዲያውኑ ታመው ሰውዬው በተደበደቡ በሦስተኛው ቀን ሕይወታቸው አልፏል፡፡
13)   የቀበሌ ገበሬ ማኅበር ሚልሻዎች፣ በመጋቢት ፳፯ ቀን ክብረ በዓል ወደ ቤተ ክርስቲያኑ በመግባት፣ ‹‹ታቦት ለማክበርና ለማንገሥ ቄሶች ይበቃሉ፤ ሕዝቡ ግን ወደ ስብሰባ ይሂድ›› በማለት ሕዝቡን አስገድደው ወስደው ክብረ በዓሉ በካህናት ብቻ ውሏል፡፡
14)   በጊምቢ ከተማ ውስጥ በአራት ዓመት ውስጥ ሦስት መስጊዶች ያለፈቃድ ሲሠሩ፣ የሕዝብና የመንግሥት ጎተራ ላይ የፕሮቴስታንት አዳራሽ ሲሠራ በዝምታ ያለፉ የመንግሥት አካላት በከተማው ውስጥ የግለሰብ ቦታ አግኝተን ቤተ ክርስቲያን ለማነጽ ስንጠይቅ ‹‹ቤተ ክርስቲያናችኹ በመንግሥት ለመታወቋ በዘንድሮው ዓመት ያሳደሰችውን የዕውቅና ወረቀት/ደብዳቤ አምጡ›› በማለት የ3000 ዓመት ባለታሪኳን ቤተ ክርስቲያን መድፈር፤
15)   ጊምቢ ደብረ ፀሐይ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ለልማት ሠርቶ ከሚያከራያቸው ሕንጻዎች የመንግሥት ግብር ክፈሉ ማለት፤ ይህ ሁሉ በተለያዩ የእምነት ድርጅቶች ተከታይ የመንግሥት አመራር አባላት መመሪያ ሰጭነት በቤተ ክርስቲያኗ ላይ የሚፈጸም የግፍ ግፍ ነው፤ በዚህም ሀገረ ስብከቱ በሐሳብ፣ በጉልበት፣ በኢኮኖሚ ከፍተኛ እንግልት እየደረሰበት መኾኑ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በአንክሮ እንዲገነዘብልን እንጠይቃለን፡፡
16)   የቃለ ዐዋዲው ሕግ ይሻሻል፤ እኛ በራሳችን በጀት ስለምንሠራ ሀ/ስብከትና ጠቅላይ ቤተ ክህነት ምን ያደርጉልናል በሚል ሕዝብ ማሳመፅና የሀ/ስብከት ዕቅድ ተግባራዊ እንዳይኾን ዕንቅፋት መኾን
የተወሰዱ ርምጃዎች
1)  የሀገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ ጨምሮ መላው የሀ/ስብከታችን ሠራተኞች ሁሉ በኦሮምኛ ቋንቋ ማስተማር ስለሚችሉ ስብከተ ወንጌልን ማስፋፋትና በበዓላት ላይ ሁሉም ሠራተኛ ወደ ወረዳ ወርዶ እንዲያስተምር ተደርጓል፤
2)  በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በደረሰው ከአንገት ላይ ማዕተብ የመበጠስ ድፍረት በፍርድ ቤት ክሥ መመሥረት፤
3)  በባቦ ገምቤል፣ በቤጊ እና ነጆ ወረዳዎች ለደረሰው ከፍተኛ የሕገ ቤተ ክርስቲያን ጥሰትና ሥርዐተ አልበኝነት በብፁዕ አባታችን መሪነት ልኡካንን አስከትሎ ካህኑ የተደበደበበበት ቦታ ድረስ በእግር የሁለት ሰዓት መንገድ በመሄድ መንግሥት አካላትን ይዘን ነገሩን አጣርተን ከወረዳ አስተዳደሮች ጋራ በጠረጴዛ ዙሪያ በመነጋገር የችግሩን ፈጣሪዎች ለይተን በማውጣት ለሕግ አቅርበናል፡፡West Wollega Hagere Sibket annual report01

“አንዳርጋቸውን አስገድደው በማናገር ሌላ የፊልም ቅንብር ለመስራት ተፍ! ተፍ! እያሉ እንደሆነ መረጃ ደርሶናል” – ታማኝ በየነ





“አንዳርጋቸውን አስገድደው በማናገር ሌላ የፊልም ቅንብር ለመስራት ተፍ! ተፍ! እያሉ እንደሆነ መረጃ ደርሶናል”
ታማኝ በየነ
October 21, 2014
አሻራ፦ ጤና ይስጥልኝ አርቲስና አክቲቪስት ታማኝ በየነ፤ በቅድሚያ ስለ ጊዜህ በአንባቢያን ስም ከፍ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ። አቶ አንዳርጋቸውን ለምን ያህል ጊዜ ታውቃቸዋለህ ? እንዴትስ ትገልጻቸዋለህ?
andargacew ashara magazine cover page
ታማኝ፦ አንዳርጋቸውን የማውቀው ከምርጫ 97 ጀምሮ ነው።በምርጫ 97 ቅንጅትን ተቀላቅሎ በሚንቀሳቀስበት ወቅት ማለት ነው። ያኔ መቼም ሁላችንም ልባችን የምርጫው እንቅስቃሴ ላይ ስለ ነበር በየእለቱ እየደወልን ሁኔታውን እንከታተል ነበር። እኔም ራሴ ሃገሬ ገብቼ እንደልቤ በነጻነት ለመኖር የምችልበት ጊዜ አሁን ነው ከሚል እምነት የመግባት እቅድ ነበረኝ። አንዳርጋቸውን የማውቀው እንግዲህ በዛ ግዜ በነበረን የስልክ ግንኙነት ነው። እስኪታሰር ድረስ ማለት ነው። በነገራችን ላይ ከመታሰሩ በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ያናገረኝ እኔን ነበር። ከኔ ጋር አውርተን ስልክ እንደዘጋ ነው የታሰረው።
ከንግግራችን የማስታውሰው እኔ እዚህ ሆኜ በስልክ ብቻ ከምከታተል ልምጣ እያልኩት ነበር። እሱ ደግሞ በዚህ ደረጃ መምጣት የለብህም እዛው ብትሆን ነው የምትጠቅመን እያለኝ ተነጋግረን እንደጨረስን ታሰረ። ከዚያም ተፈቶ ወደ እንግሊዝ አገር ተመለሰ። በኋላም በቅንጅት ኢንተርናሽናል ተመርጦ ሲሰራ በስልክም በአካልም እንገናኝ ነበር። ከአንዳርጋቸው ጋር የነበረን ትውውቅ ይህን ይመስል ነበር፡፡
እንዴት ትገልጸዋለህ? ላልከኝ፦በጣም አስቸጋሪ በሆነበት ጊዜና መንገድ ህልሙን ሊያሳካ የደከመ ሰው ነው!። በተማሪዎች እንቅስቃሴ ወቅት የውጭውን ዓለም ዘመናዊ ህይወት የለመዱ ከአውሮፓና ከአሜሪካ እየሄዱ የኢህአፓን ትግል ተቀላቅለው በርሃ የቀሩ ወጣቶች እንደነበሩ አንብቢያለሁ። በንባብ የምታውቀውን ታሪክ በአካል የምታውቀው ሰው ሲያደርግ ስታይ ደግሞ በጣም ከባድ ነው። በአውሮፓና አሜሪካ ህይወት ፤ ምግብ፤ አልባሳት፤መኝታ፤ መዝናኛ፤
ብቻ እያንዳንዷን ነገር በምርጫና በፍላጎት የምታደርግበትን ህይወት ለምደህ በርሃ ገብተህ፤ ድንጋይ ለመንተራስ፤ አሸዋ ለመልበስ፤ ላለመታጠብና ያልታጠበ ለመልበስ መወሰን እጅግ በጣም ከባድ ነው። አስበው ከእንግሊዝ አገር ከንግስቲቷ ከተማ ሄዶ አሸዋ ላይ መተኛት ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆነ!።
ባጠቃላይ አንዳርጋቸው ከልጅነቱ ጀምሮ ከራሱ ህይወት አልፎ ቤተሰቡ የከፈለውን መስዋዕትነት ሳይ የሚሰማኝ ስሜት ሃዘን ሳይሆን ይህን ሥርዓት በተለያየ መልኩ እንታገላለን ለምንል ወገኖች ትልቅ ምሳሌና አርአያ የሆነ ሰው መሆኑን ነው።
አሻራ፦ የወያኔ መንግስት አንድን ግለሰብ ለመያዝ ይህን ያህል ተጨንቆና ተጠቦ፤ ቀደም ሲል የግድያ ሙከራ ማድረጉ አሁን ደግሞ ከፍተኛ ወጪ አፍስሶ፤ ሁለተኛ አገር(የመን) የተሳተፈችበት ድንበር ዘለል አፈና መፈጸሙ ምን የፖለቲካ ፋይዳ አገኝበታለሁ ብሎ ይመስልሃል?
ታማኝ፦ በመጀመሪያ የአንዳርጋቸውን የዓላማ ጽናት (ኮሚትመንት) አብሯቸው በሰራ ጊዜ አይተውታል። ያውቁታል። ከወጣትነት ዕድሜው ጀምሮ በኢ.ህ.አ.ፓ በኋላም ከነሱ ጋር ሲሰራ ለራሴ የሚል ሰው እንዳልሆነ፤ ስልጣን ይዞ ለመንደላቀቅ፤ ቤት ለመስራት፤ መኪና … የመሳሰሉት ቁሳዊ ፍላጎት የሌለው ሰው እንደሆነ ጠንቅቀው ያውቁታል። የአንዳርጋቸው የዘወትር ቁጭት ኢትዮጵያ እንደ ሃገር ብዙ ያልተሟሉ ጉዳዮች ስላሏት እነሱን ለማሟላት መሆኑንም ያውቃሉ። ከቅርብ ጊዜው ብናይ እንኳ በምርጫ 97 ቅንጅትን ተቀላቅሎ በአጭር ግዜ ውስጥ ምን ያህል ህዝብን የማሰባሰብና የማደራጀት ስራ እንደሰራ እናስታውሳለን።
ባለፈው አስመራ ድረስ ቅጥር ነፈሰ ገዳይ ልከው ሊያስገድሉት መሞከራቸውን ኢሳት በዘገበበት ጊዜ እንዴት ሊሆን ይችላል?ይሄ የኢሳት ወሬ ነው ያሉኝ ሰዎች ነበሩ። እነሱ(ወያኔዎች) ግን በየት በኩል ጉዳት ሊመጣ እንደሚችል በደንብ ገብቷቸዋል።በኔ ግንዛ አንዳርጋቸው የማስተባበሩን ስራ ጥሩ አድርጎ እንደሚሰራ ስላወቁ ይመስለኛል ይህን ያህል ክትትል አድርገው ሊይዙት የቻሉት።
አሻራ፦ እንዳልከው አቶ አንዳርጋቸውን መያዝ ማለት የተቃዋሚውን አከርካሪ እንደመስበር ሳይቆጥሩት የቀሩ አይመስልም።ይሁንና አቶ አንዳርጋቸውን የመን ላይ ይዘው መውሰዳቸው ለግዜው ጮቤ ቢያስረግጣቸውም፤ ውጤቱ ግን “ አሳ ጎርጓሪ….” ሆኖባቸዋል የሚሉ ብዙ ናቸው፡፡ አንተስ በዚህ ሃሳብ ትስማማለህ?
ታማኝ፦ በጣም እንጂ የምስማማው።እኔ እንግዲህ ህወሃት አገሪቷን ከተቆጣጠረበት ጊዜ አንስቶ በተቃዋሚነት አብሬ ኖርያለሁ። በውጭው ዓለምም አውሮፓ ፤ አውስትራሊያ ፤ አሜሪካ …ያለውን የተቃዋሚውን ወገን እንቅስቃሴ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን አውቃለሁ እላለሁ። እናም ከቅንጅት በኋላ “የምን ፖለቲካ?…ፖለቲካ በቃኝ!” እያለ የሸሸው ሰው ሁሉ በፈቃደኝነት “ምን እናድርግ?” ብሎ የመጣበት ወቅት ነው አሁን።
የአንዳርጋቸውን ነገር የተለየ የሚያደርገው ደግሞ፦ አንዳርጋቸው በየመድረኩ የሚታይ ሰው አይደለም። ከሱ በበለጠ እኔ በብዙ መድረክ እታያለሁ።
እሱ ግን የሚሰራ እንጂ የሚታይ ሰው አልነበረም፡፡ ይሁንና ህውሃት ይህን ያህል ሊያጠፋው የፈለገው አንዳርጋቸው ምን አይነት ሰው ቢሆን ነው? የሚለውን ነገር እንድት ጠይቅና እንድታገናዝብ ያደርግሃል። ለዚህም ይመስለኛል በውጭም በሃገር ቤትም የሚገኘው ህዝብ በሚያስደንቅ መልክ የተንቀሳቀሰው።
በዚሁ ጉዳይ ላይ ከአንድ ኢትዮጵያዊ ምሁር ጋር ስንወያይ “በታሪክ ውስጥ አንዳንድ ሰዎች ለለውጥ ምክንያት ይሆናሉ” ነበር ያለኝ። እኔም አንዳርጋቸው የለውጥ ምክንያት እንደሆነ ነው የሚሰማኝ። በርግጥ በዚህ መልክ መሆኑና እየደረሰበት ያለውን ስቃይ ስታስብ ቢያምህም በህዝብ ውስጥ የፈጠረው የመተሳሰብና የአብሮነት ስሜት ግን ቀላል አይደለም። ፊት ለፊት የማይተያዩና መነጋገር የማይፈልጉ ተቃዋሚዎች ያወጡትን ተመሳሳይ ቁጭት፤ እልህና ንዴት የተንጸባረቀበትን መግለጫ ስታየው ህወሃቶች እራሳቸው ምነው በቀረብን ሳይሉ የሚቀሩ አይመስለኝም። አንዳርጋቸውን መያዛቸው በርግጥም “አሳ ጎርጓሪ..” ሆኖባቸዋል በሚለው ሃሳብ እስማማለሁ።
አሻራ፦ አሁን ደግሞ በቅርቡ ለእይታ ወዳቀረብከው “ተላላኪው ማነው?” ወደሚለው የምስል ዘገባ ልመልስህ፦ ይህን ስራ ለማቅረብ ምክንያት የሆነህ ወይም መነሻ ሃሳቡን ያጫረብህ ጉዳይ ምንድነው?
ታማኝ፦ እእ …! ሁሌም በአይምሮዬ የሚመላለሱ ጥያቄዎች አሉ፦ የህወሃት መሪዎች ከሟቹ ጠ/ሚንስትራቸው ጀምሮ “እነዚህ የሻቢያ ተላላኪዎች” የሚሉት ነገር አለ። እናም ሁሌ እነኝህ ሰዎች እውነት ሰው አያውቅብንም ብለው ያስባሉ? እያልኩ እራሴን እጠይቃለሁ። አንድ ነገር ኮሽ ባለ ቁጥር “እነኚህ የሻቢያ ….” ሲሉ እየቀለዱ ነው? እላለሁ።
አሁን ደግሞ አንዳርጋቸውን ከያዙ በኋላ ይህንኑ አባባላቸውን ደጋግመው ሲጠቀሙበት …. አልበዛም? የሚል ስሜትና የነሱ መሬት የለቀቀ ውሸት ነው ለሥራው ያነሳሳኝ።
አሻራ፦ አቶ አንዳርጋቸውን ለሁለተኛ ጊዜ በቴሌቪዥን መስኮ ያቀረቧቸው “ተላላኪው ማነው?” የሚለው የታማኝ የምስል-ዘገባ በኢሳት እንደሚቀርብ ከማስታወቂያው በማወቃቸው ሳይቀደሙ ለመቅደም አስበው ነው ሲሉ ብዙዎች አስተያየት ሰንዝረዋል። በተለይ ያቀረቡት የፊልም ዘገባ የሚጀምረው “የሻቢያ ተላላኪዎች” በሚሉ ቃላት መሆኑ የአስተያየቱን ትክክለኝነት ያጎላዋል ይላሉ…በዚህ መልክ ታይቶሃል?
ታማኝ፦ እንዳልከው የተሰነዘሩ አስተያየቶችን ሰምቻለሁ። ምንድነው ከባዱ ነገር መሰለህ ? የኔ ስራ ከመውጣቱ በፊት ለመቅደም ሲሉ አዘጋጁት ብል የኔ ከፍታ ሊጨምር ነው፤ መንጠራራት ሊሆንብኝ ነው። ከኔጋ እየተከራከሩ ነው ማለት በጣም በጣም ይከብዳል። ከተለያዩ ሰዎች የተሰነዘሩ አስተያየቶችን ስትመለከት፤ የቪዲዮው ያለ ጥንቃቄ ተከታትፎ (በአግባቡ ኤዲት ሳይደረግ) በችኮላ መቅረብ፤ የተጠቀሙበት ቃልና ከኔ ሥራ ጋር በአንድ ቀን መልቀቃቸው እነኚህን ነገሮች እንድታስብ ያደርግሃል። ጥድፊያቸው ደግሞ ከአንዳርጋቸው ቃል ጀርባ ያለውን የጣር ድምጽ እንድንሰማ እስከማድረግ ያደረሳቸው ነው። ይህን ይህን ደማምረህ ስታይ አንተ ከምትለው ጋር ይቀራረባል ። እኔ ግን ለኔ መልስ ሰጡ ብዬ ማለት ይከብደኛል።
አሻራ፦ እንደ መንግስት አስበሃቸው ይሆን ለኔ መልስ እየሰጡኝ ነው ማለት ይከብደኛል ያልከው?
ታማኝ፦ በጭራሽ!! እንደ መንግስት ቢያስቡና እኔም እንደ መንግስት ባስባቸውማ በወደድኩ ነበር። ዋናው ችግር እንደ መንግስት አለማሰባቸው ፤ እንደ መንግስት አለመስራታቸው አይደል እንዴ?እንዴት አድርጌ ነው እንደ መንግስት የማስባቸው? እኔ ይህን የምለው ሕዝብን ከማክበር ነው። በግለሰብ ደረጃ የሰጠሁት አስተያየት ወይም ያቀረብኩት ስራ ሊታይ የሚገባው በዛው ደረጃ መሆኑን ስለማምንበትና ከዛ በራቀ እንዳይታይብኝ ነው።
Fezralizm – By Tamagn Beyene Part 2
አሻራ፦ በቅርቡ በጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና አወያይነት አንተ፤ አቶ ኤርሚያስ ለገሰና የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ወንድማገኝ ጋሹ በኢሳት ቀርባችሁ ባደረጋችሁት ውይይት ብዙዎችን ያስገረመ ነገር አስደምጠሃል። ያስደመጥከው ነገር፦ ጥቂት የወያኔ ባለስልጣናት በተገኙበት ውይይት ላይ አቶ በረከትና አቶ አዲሱ የተናገሩትን ነው። ይህ ውይይት በኢሳት መደመጡ ተቃዋሚው ወያኔ ጉያ ውስጥ ለመግባቱ አመላካች ሆኗል የሚሉ ብዙዎች ናቸው። ትግሉ የደረሰበትን ደረጃም ያሳያል የሚሉም አሉ፡፡ እንደ ጥያቄ ማንሳት የምሻው ይህን አይነት ጥብቅ ሚስጥር ኢሳት እጅ ሊገባ መቻሉ የተቃዋሚው የመረጃ ክፍል ጥንካሬ ወይስ ወያኔ ውስጡ ከመቦርቦሩ ጋር በተገናኘ እየሆነ ያለ …?
ታማኝ፦ ህዝቡ እኮ ታፍኖ የመጨረሻ ግፍ እየተቀበለ ነው ያለው። ደርግ ክፉ ነገሮችን ሁሉ ጨርሶ አድርጓቸው ሄዷል፤ ከደርግ በላይ ማንም ምንም አይነት ግፍ ሊፈጽም አይችልም የሚል እምነት ነበርን፡፡ እነዚህ ግን እኮ ሁሌም የሚሰሩት ግፍና ክፋት እያስደነቀን ነው።
ክፋታቸውን ቢያሳይ አንድ ምሳሌ ልንገርህ፦ የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ፍርድ ቤት ቀርበው በነበረበት ጊዜ፤ በርሃብ ምክንያት መናገር እንኳ አቅቷቸው፤ ለዳኛው ምግብ በልተን አናውቅም ብለው ሲናገሩ፤ ዳኛው ደንግጦ ምግብ አምጡላቸው ብሎ ፍርድ ቤት ውስጥ እኮ ምግብ ተበላ! እነኚህ ሰዎች እኮ ያሰሩትን ሰው በርሃብ የሚቀጡ ናቸው ! እረ ስንቱን…… ዘርዝሬ እችለዋለሁ?
የህዝብን ስሜት በጥቂቱም ሊያሳይ ከቻለ አንድ ነገር ልንገርህ፦ በቅርቡ ለኢሳት አራተኛ አመት ወደ ጀርመን ሄጄ ነበር፡፡ በዝግጅቱ ላይ አንድ ሰው እጁን አውጥቶ እንዲህ ሲል ተናገረ፦ “ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ሄጄ ነበር፡፡ በክፍለ ሃገር ቤተሰቤ በሚገኝበት አካባቢ ለሚኖሩ አንድ አዛውንት ለቡና መግዣ ብዬ 50 ዩሮ ሰጠኋቸው። ተቀብለው ካመሰገኑኝ በኋላ፤ ሰማህ ወይ ልጄ ከዚህች 50 ብር ላይ ዘርዝርና 10 ብሩን ለዛ ለታማኝ በእጁ ስጥልኝ፤ ለኢሳት ገቢ እንዲያረግልኝ ብለው ሰጥተውኛል።” ነበር ያለው፡፡ ተመልከት በዚህ አይነት የኑሮ ደረጃ ያሉ ኢትዮጵያዊ እንኳ ከተሰጣቸው 50 ዩሮ 10 ለኢሳት ይሰጥልኝ አሉ።ይሄ እኮ ሌላ ምንም ማለት አይደለም። ህዝቡ ምን ያህል ነጻነት እንደናፈቀ የሚያሳይ ነው። የሰውን ፍላጎት ነው የምነግርህ፡፡
በመረጃ በኩልም ህዝቡ ለትግሉ የሚጠቅም መረጃ ለመላክ በሚገርም መልኩ ፍቃዱና ፍላጎቱ አለው። ባገኘው ቀዳዳ ሁሉ ሳይፈራና መስዋዕትነት ከፍሎም ቢሆን መረጃዎችን ለመላክ ይፈልጋል።
ኢሳት አሁን አብዛኛውን መረጃ የሚያገኘው ከህዝብ ነው። እኔ በግለሰብ ደረጃ ነው መረጃዎቹ የሚደርሱኝ፡፡ አንድ ጠንካራ ድርጅት ተፈጥሮ በዚህ ረገድ ስራ ቢሰራ ደግሞ ምን ያህል እንደሚተባበር መገመት ከባድ አይሆንም።
አሻራ፦ ወደ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ልመልስህ፦ አቶ አንዳርጋቸው ላይ አፈናው በተፈጸመበት ሰሞን በለንደን በተደረገ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ተገኝተህ በነበረበት ወቅት አቶ አንዳርጋቸው የአንበሳ ምስል በልዩ ሽልማት መልክ ሲሰጡህ ከሚያሳይ ክሊፕ ጋርአዳብለህ “ አንዳርጋቸው አንበሳውን መልሰህ ተቀበለኝ፤ ለኔ አይገባኝም!” የሚል መልዕክት አስተላልፈሃል። ይህን ያዩ ሰዎች ለአንድ ሃገር አንድ አንበሳ ብቻ ነው የሚያስፈልጋት እስካልተባለ ድረስ ታማኝም አንዳርጋቸውም ለሃገራችን አንበሶች ናቸውና ታማኝ ለምን ያንን አደረገ? ሲሉ ይጠይቃሉ። በርግጥ ለአቶ አንዳርጋቸው ያለህን ክብር ለመግለጽ የተጠቀምክበትን አገላለጽ ብዙዎች ወደውታል ። እስቲ ይህን ልትል ያስቻለህን …. ግለጽልን፡፡
ታማኝ፦ ያንን ያልኩት በስሜታዊነት ወይም በግብታዊነት አይደለም። ከልቤ የተሰማኝንና የሚሰማኝን ነው የተናገርኩት። አንዳርጋቸው አንበሳውን ለኔ ሲሸልም ስለኔ የተናገረው ራሱ በጊዜውም ከብዶኛል። እኔ ቀደም ሲል እንደ ገለጽኩልህ ራሴን የማየው እንደ አንድ ለህዝብ ነጻነትና ለሃገሩ ሰላም ፤ ….የሚናፍቅ ዜጋ ነው። አንዳርጋቸው በዚህ እድሜው ለህዝቡና ለሃገሩ ሲል የወሰደው እርምጃ በጣም ያስደንቀኛል። ሊከፍል የተዘጋጀው መስዋእትነት ሳያንስ እንደገና አፈናው ሲፈጸምበት ልንላቸው ይገባል፡፡
እነሱ (ገዢው ፓርቲ) በፍርሃት ዓለም ውስጥ ስለሆኑ ሁሉንም ነገር ለመቆጣጠር ነው ሩጫቸው፡፡ ወደፊት መቼም ቻይና የማትሰራው ነገር የለምና አገር ስትገባ ኤርፖርት ላይ ለመንግስት ክፉ -ልብ ያለውን ስካን የሚያደርግ መሳሪያ ሁሉ ሊያሰሩ ይችላሉ ….(ሳቅ)። ምርጫውንም ቢሆን ከዚህ በተለየ አይደለም የማየው። ፍርሃት ውስጥ ያለ አካል እውር ድንብሩን ብዙ ነገር ሊያደርግ ይችላል።
አሻራ፦ አንዳንድ ሰዎች ታማኝ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝን የራራላቸው ይመስላል። አቶ መለስን የተነፈሷትን ቃል ተከትሎ ወዲህ ወዲያ ያደርጋቸው እንዳልነበር ለአቶ ሃይለማሪያም ምነው ዝም አለ ይላሉ?
ታማኝ፦ ሳቅ…………! ይህን የሚሉ ሰዎች እውነት ከልባቸው እኔ በአቶ ኃይለማሪያም ላይ ግዜ እንዳጠፋ ፈልገው ነው? አይመስለኝም፡፡ አቶ መለስ እኮ የራሳቸው ተረት ፤የራሳቸው ስድብ ፤የራሳቸው፤ ውሸት የራሳቸው ምናምን…የነበራችው ሰው ነበሩ። አቶ ኃይለማሪያም ደግሞ ሳይዛቸው አልሆን ብሎ እንጂ የአቶ መለስን ልብስ ሊለብሱ የሚፈልጉ ነው የሚመስለኝ።
የአገር መሪዎች ከስራ ውጭ መጽሄት ማገለባበጥ፤ የአለም ዜና መከታተል …. እንዲህ እንዲህ አይነት ነገር እደሚያደርጉ ነው የማስበው፡፡ አቶ ኃይለማሪያም ግን ሌሊት ሁሉ ቁጭ ብለው የአቶ መለስን ቪዲዮ የሚያዩ ነው የሚመስለኝ፡፡ “ እስኪ የ 94ቱን አምጪልኝ የ93ቱን ጨርሻለሁ እያሉ…” እና በእኝህ ሰው ላይ ነው ግዜ እንዳጠፋ የሚፈለገው? ለሳቸው የሚሆን ግዜ እንኳ የለኝም፡፡ በቁምነገር ልወስዳቸው አለመፈለጌ እንጂ አቶ ኃይለማሪያም እንዴት ያለ ኮሜዲ ሊሰራባቸው የሚችሉ መሰሉህ?
አንተ ኮ! ስትኮርጅ የሰውን ሃሳብ፤ ወይም ሻል ያለ ነገር ትኮርጃለህ ። ማዛጋት ትኮርጃለህ?…..(ሳቅ) እሳቸው እኮ የአቶ መለስን ማዛጋት ሁሉ እየኮረጁ ነው! (ሳቅ)……! እኔ እንደ መዝናኛና ኮሜዲ ሾው ነው የማያቸው። ከዚህ ባለፈ አላያቸውም። አይ የግድ ይሰራባቸው ከተባለም ለቁምነገር ሳይሆን ለትርፍ ግዜ መዝናኛ ሊሰራባቸው ይችላል፡፡ከዚያ ውጭ ግን በሳቸው ላይ ግዜ ማጥፋት ያለብኝም ያለብንም አይመስለኝም።
ደግሞ ምን መሰለህ..? እኔ ጠ/ሚ/ር ስትለኝ የሚመጣብኝ ምስል እንደ አክሊሉ ሃብተወልድ አይነት ሰው ነው፡፡ ….እና በዚህ ስም ኃይለማሪያም ደሳለኝ ሲጠራበት ……(ፋታ) ልክ አይሆንም፡፡
አሻራ፦ የወያኔን ከፍተኛ ባለስልጣናት በስልክም ቢሆን ለማግኘት ሞክረህ አታውቅም? ሞክረህ ከሆነ ውጤቱ ምን ነበር?
ታማኝ፦ እምምም.. አዎ! አንድ ሶስት ግዜ ሞክርያለሁ፡፡ አንዴ የቤንሻንጉል መፈናቀል ጊዜ …ሌላው ደግሞ አርሲ ውስጥ ሙስሊሞች የተገደሉ ጊዜ ይመስለኛል…አንዱን ዘነጋሁት። ብቻ ለ3 ጊዜ ያህል አቶ በረከት ጋ ደውዬ ነበር።መጀመሪያ የደወልኩ ጊዜ አነሳ፤ ጤና ይስጥልኝ ከአሜሪካ ነው የምደውለው አልኩት። “ማን ልበል? ” አለኝ። አይ እኔ የመንግስትዎ ተቃዋሚ ነኝ፤ ነገር ግን አሁን እየሆነ ባለው ጉዳይ መረጃ ይሰጡኝ እንደሁ ብዬ ነው የደወልኩት አልኩት።
እሱም “ማንነትክን ካልገለጽክልኝ ምንም መረጃ መስጠትም ሆነ ማውራት አልችልም” አለኝ።
መልሼም፦ማንነቴን ከነገርኩዎት አያናግሩኝም አልኩት። “ግዴለህም አናግርሃለሁ!” አለኝ።
ታማኝ በየነ ብዬ ሳልጨርስ ስልኩ ላዬ ላይ ተዘጋ፡፡በሌላም ጊዜ የሆነው እንዲሁ ነው፡፡ ታማኝ በየነ ነኝ ስለው ስልኬን ይዘጋዋል።
አሻራ፦ ለማነጋገር ፈቃደኛ ቢሆን ኖሮ በምን አይነት ስሜት ነበር የምታናግረው? ምንስ ነበር የምታናግረው?
ታማኝ፦ ለነገሩ በተለይ በመጀመሪያ የደወልኩለት ጊዜ አልተዘጋጀሁም ነበር፡፡ አሁን ስልኩን ሲያነሳ እንዴት ብዬ ነው የማናግረው? ንዴትም ቁጣም ፤ እልህም ይኖራል እና እንዴት እንደማናግረው አላውቅም ነበር፡፡ ሰዎችም አብረውኝ ነበሩ። ለማንኛውም የምለውን ሳልል እሱም ስልኩን ዘጋው። ሁለተኛ ስደውል ግን አስቤበት ነበር፡፡ ግን ምን ዋጋ አለው ስልኩ ይነሳና ራሴን ሳስተዋውቅ ይዘጋል።
አሻራ፦ ምን ትለው ነበር ?
ታማኝ፦ሁሌ ራሴን የምጠይቀውን ነገር ነበር ልጠይቀው የፈለኩት። እንደው መጨረሻችሁ ምንድነው? እውነት እናንተ ሰዎች የምታደርጉትን ነገር ሁሉ የምታደርጉት የምር!! ለሃገርና ለህዝብ ጥሩ እየሰራን ነው ብላችሁ አምናችሁበት ነው? ልጆቻችሁን ትወዳላችሁ? ልጆቻችሁ ከሌሎች ልጆች ጋር በፍቅር እዲኖሩ አስባችሁ ታውቃላችሁ? ብዬ ጠይቄ ከራሳቸው አንደበት ብሰማው ፈልጌ ነበር አልሆነም ዘጋብኝ፡፡
አሻራ፦ ወደ ወቅቱ ጉዳይ ልመልስህ፦ የአቶ አንዳርጋቸው መያዝ ኢትዮጵያዊውን ሁሉ አስቆጥቷል፡፡ በወያኔ መንግስት ላይ ያለው ተቃውሞና ለለውጥ ያለው ተነሳሽነት ከመቼው ጊዜ በተለየ ጠንክሯል። ይህን ተነሳሽነት ወደ ውጤት ለመለወጥ ምን መደረግ አለበት ትላለህ?
ታማኝ፡- አንድ ነገር አለ! በአሁኑ ሰአት በሃገራችን እየሆነ ያለው ነገር በጣም የሚያስፈራ ነው፡፡ እኛ የምንቃወማቸው ስለምንጠላቸው አይደለም፡፡ የምንቃወማቸው እያደረጉ ያሉት ነገር በጣም የሚያስፈራ፤ ሃገራችን እንደ ሃገር ህልውና እንዳይኖራት፤ ህዝባችንም አብሮ መኖር እንዳይችል የሚያደርጉ ሥራዎችን እየሰሩ በመሆኑ ነው። በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በተደጋጋሚ የዘር ቅራኔዎችን እያየን ነው። እገሌ ከዚህ ክልል እገሌ ከዚህ ክልል ውጣ እየተባለ ህዝብና ህዝብ እየተቂያቂያመ እንዲሄድ እየተደረገ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በጣም ያስፈራል፡፡
የህክምና ባለሙያ ባልሆንም አንድ ዶክተር ወደ ካንሰር ሊለወጥ የሚችል በጣም ከባድ የጤና ችግር ያለበትን በሽተኛ ፡ በአግባቡ መርምሮ ዘለቄታዊ መፍትሄ ይፈልግለታል እንጂ ህመም አስታጋሽ (ፔይን ኪለር) የሚሰጠው አይመስለኝም፡፡ የሃገራችን ወቅታዊ ጉዳይም ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ነው። ዛሬ አንድ ዘላቂ መፍትሄ ነገር ካላደረግን ችግሩ ሊድን ወደማይችል ካንሰርነት መለወጡ አይቀርም።
ኢትዮጵያን ሃገሬ የምንላት ሁሉ አትሌቶቻችን ባንዲራዋን ለብሰው ትራክ ላይ ሲያሟሙቁ፤ ማን በ10 ሺህ ተሰለፈ ? ማን ለወርቅ ተስፋ አለው? …. እያልን እንጨነቃለን ። በውጤቱም እንደሰታለን። አሁን ደግሞ አትሌቶቿ ወርቅ ሲያስገኙላት የምንቦርቅላት ሃገር እንደ ሃገር መቀጠሏ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው። ይህ ደግሞ በኛና በኛ ትከሻ ላይ ብቻ ያረፈ ችግር ነው። ስለሆነም ከዚህ በፊት በተቃዋሚነት ሲንቀሳቀስ የቆየውም ሆነ ያልተንቀሳቀሰው ዜጋ፤ ብቻ ሁሉም ሁሉም ባመነበትና ታግሎ ያታግለኛል ባለው በአንዱ መስመር ገብቶ መታገል አለበት እላለሁ፡፡ ዛሬ አንዱ ተመልካች አንዱ ሯጭ የሚሆንበት ጊዜ አይደለም። ማንም ለምንም ጥሪ የሚያደርግበት ጊዜም አይደለም። ዛሬ አንድ ነገር ካላደረግን ለልጆቻችን የምናስተላልፈው “ነገ” የለም፡፡በዚህ ደረጃ ነው መታየት ያለበት የሚመስለኝ።
አሻራ፦ በተነሳንበት እንቋጭና አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለህዝብ ነጻነት በጽናት ሲታገሉ ጠላት እጅ ወድቀዋል ፤ ህዝብስ ለሳቸውም ሆነ ለሃገር ነጻነት በመታገል ረገድ ምን ይጠበቅበታል ትላለህ?
Andargachew Tsige
ታማኝ፡- አንዳርጋቸው በወያኔ እጅ እስከወደቀበት ጊዜ ድረስ የራሱንና የቤተሰቡን ህይወት ሰውቶ፤ በርሃ ገብቶ የቻለውን ሁሉ አድርጓል። የአንዳርጋቸው የትግል ጉዞ እዛ ጋ አብቅቷል። ዓለም ላይ ያሉ ሰውን የማስቃያ ቴክኒኮችን ሁሉ በእጁ ያስገባው የወያኔ መንግስት ደህንነት ባለፉት ሁለት ወራት አንዳርጋቸው ላይ ምን ሲፈጽምበት እንደቆየ ለመገመት የካፒቴን ተሾመ ተንኮሉን ቃለ ምልልስ ማድመጡ በቂ ይመስለኛል፡፡ አንዳርጋቸው ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍሏል። እየከፈለም ነው።
የወያኔ መንግስትን ባህሪ መለስ ብለን ብናይ ሕዝብ የሚያከ ብራቸውን ሰዎች አዋርዶና አቅልሎ ለማሳየት የማይፈነቅለው ድንጋይ እንደሌለ እንረዳለን፡፡
በአቶ አንዳርጋቸው መታፈን የተቆጣውን ህዝብ ተስፋ ለማስቆረጥ በተለመደው መልክ አቶ አንዳርጋቸውን አስገድደው በማናገር ሌላ የፊልም ቅንብር ለመስራት ተፍ! ተፍ! እያሉ እንደሆነ መረጃ ደርሶናል። ዋናው ቁምነገር ግን ህዝባችን ለዚህ መሰሉ የወያኔ ተደጋጋሚና አሰልቺ ህዝብን የማሳሳት፤ ጉምቱ የህዝብ ወኪሎችን የማዋረድ ሴራ አዲስ ስላልሆነ ምንም ይበሉ ምንም ይስሩ ፕሮፓጋንዳው ውጤት እንደማይኖረው አልጠራጠርም፡፡
ዋናው ቁም ነገር የነሱን ፕሮፓጋንዳ ማክሸፍ ብቻ ሳይሆን ለዘመናት ስንታገልለት የቆየነው ዘረኛውን መንግስት ከሕዝብ ጭንቃ ላይ የማውረድ ዓላማ በውጤት እንዲቋጭ ሁላችንም አንድ ሆነን መነሳት ነው!!!።
አሻራ፡ ስለ ጊዜህ በድጋሚ እናመስግናለን! ታማኝ፡ እኔም ስለተሰጠኝ እድል አመሰግናለሁ::
በአውስትራሊያ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለማስታወስ ከታተመችው አሻራ መጽሄት የተወሰደ::