Saturday, January 4, 2014

ደላላው የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስን “ካሳ ካልከፈሉኝ እከሳለሁ” አለ


- የፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤት፣ የቀድሞው ፕሬዚዳንት እና ሴት ልጃቸው በፍርድ ቤት ክስ ቀረበባቸው

- የፕሬዝዳንቱ ጽ/ቤት የህግ ባለሙያ የለውም
- ” የ2.4 ሚሊየን ብር ካሳ ይከፈለኝ” የሚል ደብዳቤ ለፕሬዝዳንቱ ጽ/ቤት ገብቷል
ከምኒልክ ሳልሳዊ
girma weldegirogis
ለቀድሞው ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ አሁን የሚኖሩበትን ቤት አፈላልጎ ያከራያቸው ግለሰብ 360,000 ብር የአገልግሎት ክፍያ አልተከፈለኝም ሲል የቀድሞው ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስን፣ ሴት ልጃቸውን መና ግርማ ጨምሮ የፕሬዝዳንት ጽ/ቤትን ከፕሬዚዳንቱ ቢሮ የጽ/ቤቱን ኦፊሰሮች ወይዘሮ አማረች በቃሎን እና ወይዘሮ አምሳል ፋንታሁንን ከስሷል፡፡
ከሳሹ የአገልግሎት ክፍያውን ከማን ማግኘት እንዳለበት እንዳላወቀና ፍርድ ቤት አጣርቶ እንዲያሳውቀውም ጠይቋል፡፡ የፕሬዝዳንቱ ጽ/ቤት በበኩሉ ክፍያው የመንግስትን ጥቅም ስለሚጎዳና ክሱን ለመከራከርም ጽ/ቤቱ የህግ ባለሙያ ስለሌለው ፍትህ ሚንስትር ወክሎ እንዲከራከርለት የሚጠይቅ ደብዳቤ ለፍትህ ሚንስትር ጽፏል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም፣ ከዚህ በፊት ለቀድሞው ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ቤት ለማከራየት ውል ተዋውዬ፣ ቤቴን አሳድሼና ሌሎችንም በርካታ ወጪዎችን አውጥቼ ውሉ ፈርሶብኛል ያሉት ግለሰብ በዚሁ ሳቢያ ለደረሰብኝ ጉዳት የ2.4 ሚሊየን ብር ካሳ ይከፈለኝ የሚል ደብዳቤ ለፕሬዝዳንቱ ጽ/ቤት አስገብቷል፡፡
ይህ ካልሆነ ግን ወደ ፍርድ ቤት እንደሚያመራ አስታውቋል፡፡
Ze-Habesha

No comments:

Post a Comment