(ዘ-ሐበሻ) በቅርቡ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ባደረገው ምርጫ ስልጣናቸውን ለኢንጂነር ግዛቸው ያስረከቡት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ፓርቲያቸው አንድነት የመስራች ጉባኤውን በአዲስ ቪው ሆቴል እያደረገ ባለበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ቀጣይ የፖለቲካ ህይወታቸውን አስመልክቶ የደረሱበትን ውሳኔ አሳወቁ።
የፓርቲውን የመመስረቻ ጉባዬ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቀድሞው የአንድነት ሊቀመንበር ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ‹‹ከአሁን በኋላ ከየትኛውም የፓርቲ ፖለቲካ ራሴን አግልያለሁ፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ዕድሜዬ 70 መድረሱ ነው፡፡ትግሉን ወጣቶች መምራት እንዳለባቸው አምናለሁ፡፡ስለዚህ በቀሪው ህይወቴ ገለልተኛ በመሆን አገሪን ለማገልገል እሰራለሁ፡፡በአንድነት አዲሱ ብሄራዊ ምክር ቤት ከ65ቱ ውስጥ 47 ወጣቶች መሆናቸው አስደሳች ነገር ነው፡፡አዲሱ ፕሬዘዳንት ስራ አስፈጻሚ ውስጥ ከ65% በላይ ወጣቶች እንደሚሆኑ መናገራቸውም ያስደስተኛል፡፡›› ማለታቸውን የአንድነት ፓርቲ ሚድያዎች ዘግበዋል።
ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ኢሕአዴግን ሲለቁ አቶ መለስ ዜናዊን “አሁንስ መንግስቱ ኃይለማርያም መሰልከኝ” በሚል በቃኝ ያሉ ሲሆን አሁን ደግሞ ከማንኛውም የፓርቲ ፖለቲካ በቃኝ ያሉት በእድሜ መግፋት ነው።
ዛሬ በአዲስ ቪው ሆቴል ኢንጂነር ግዛቸው በአብዛኛው በወጣት የተያዘውን ካቢኔያቸውን ይፋ አድርገዋል። ዝርዝራቸውም የሚከተሉት ናቸው፦
1) አቶ ተክሌ በቀለ ——- ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዘዳንት
2) አቶ በላይ ፈቃዱ ——– ምክትል ፕሬዘዳንት
3) አቶ ስዩም መንገሻ ——– ዋና ጸሀፊ
4) አቶ ዳንኤል ተፈራ ——– የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ
5)አቶ ሃብታሙ አያሌው ——- የህዝብ ግኑኝነት ሀላፊ
6)አቶ ዘለቀ ረዲ ——— የውጪ ጉዳይ ሀላፊ
7) አቶ አስቻለው ከተማ ——- የፋይናንስ ጉዳይ ሃላፊ
8)አቶ ሰለሞን ስዮም ——– የፖለቲካ ጉዳይ ሃላፊ
9) አቶ ዳዊት አስራደ ——– የኢኮኖሚ ጉዳይ ሃላፊ
10)አቶ አለነ ማህጸንቱ ——- የማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊ
11) ወ/ሮ የትናየት ቱጂ ——- የህግና ሰብአዊ መብት ጉዳይ ሃላፊ
12) አቶ ትእግስቱ አወሉ ——- (የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሃላፊ በመሆናቸው በቀጥታ የካቢኔ አባል ሆነዋል)
Ze-Habesha2) አቶ በላይ ፈቃዱ ——– ምክትል ፕሬዘዳንት
3) አቶ ስዩም መንገሻ ——– ዋና ጸሀፊ
4) አቶ ዳንኤል ተፈራ ——– የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ
5)አቶ ሃብታሙ አያሌው ——- የህዝብ ግኑኝነት ሀላፊ
6)አቶ ዘለቀ ረዲ ——— የውጪ ጉዳይ ሀላፊ
7) አቶ አስቻለው ከተማ ——- የፋይናንስ ጉዳይ ሃላፊ
8)አቶ ሰለሞን ስዮም ——– የፖለቲካ ጉዳይ ሃላፊ
9) አቶ ዳዊት አስራደ ——– የኢኮኖሚ ጉዳይ ሃላፊ
10)አቶ አለነ ማህጸንቱ ——- የማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊ
11) ወ/ሮ የትናየት ቱጂ ——- የህግና ሰብአዊ መብት ጉዳይ ሃላፊ
12) አቶ ትእግስቱ አወሉ ——- (የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሃላፊ በመሆናቸው በቀጥታ የካቢኔ አባል ሆነዋል)
No comments:
Post a Comment