ህፃናት በጉዲፈቻ ከሀገር ሲወጡ ቤተሰቦቻቸው በማያውቁበት ሁናቴ በሕገወጥ መልኩ የ20 ሺህ ዶላር ክፍያ ይፈፀምባቸዋል ሲል «ሠንደቅ » ጋዜጣ ባወጣው ዘገባ መከሰሱን ዋና አዘጋጁ ገለፀ።
በቀን በአማካይ 70 ህፃናት በጉዲፈቻ ከሀገር እንደሚወጡም ዋና አዘጋጁ ጠቅሷል። የሴቶች፣ የህፃናትና የወጣቶች ሚንስትር በበኩሉ በወሬ ደረጃ እንጂ ህፃናት በክፍያ ከሀገር ስለመውጣታቸው የማውቀው ነገር የለም ይላል። በቀን በጉዲፈቻ ከሀገር ይወጣሉ ተብሎ በጋዜጣው የተጠቀሰው ቁጥርም ተጋኗል ሲል ገልጿል።
«ሰንደቅ» የተሰኘው ጋዜጣ ታህሳስ 23 ቀን 2006 ዓም ጉዲፈቻን በተመለከተ በጋዜጣው ርዕሰ አንቀፅና የፖለቲካ አምድ ላይ ባወጣው ዘገባው ምክንያት አዘጋጆቹ መከሰሳቸውን የጋዜጣው ዋና አዘጋጅ ፍሬው አበበ ገለፀ። ዋና አዘጋጁ ከፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ዘርፍ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ በስልክ ተጠርቶ ቃላቸውን እንደሰጡም ለዶቼ ቬለ አክሎ ተናግሯል። ክሱን ያቀረበባቸው የሴቶች፣ የህፃናትና የወጣቶች ሚንስትር እንደሆነም ተናግረዋል። የሴቶች፣ የህፃናትና የወጣቶች ሚንስትር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አብይ ኤፍሬም የክስ ሂደቱን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ለመስጠት እንደሚቸገሩ ተናግረዋል። ሙሉ ጥንቅሩን የድምፅ ማጫወቻውን በመጫን ያድምጡ።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሂሩት መለሰ
No comments:
Post a Comment