ትናንት አመሻሽ ላይ ከሞያሌ ወደ ሻሸመኔ ሲጓዝ በነበረ ሀገር አቋራጭ አውቶብስ ላይ በደረሰ የመገልበጥ አደጋ የ16 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ32 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደረሰ።
ከሟቾቹ ውስጥ ዘጠኙ ወንዶች ሲሆኑ ሰባቱ ደግሞ ሴቶች ናቸው።
ከተሳፋሪዎቹ ውስጥ የ2 አመት ህጻን ያለ ምንም ጉዳት ተርፏል።
ከዚህ በፊትም በዚህ ቦታ ላይ የተለያዩ የትራፊክ አደጋዎች ይደርሱ እንደነበርም አስተባባሪው ገልጸዋል።
ተጎጂዎቹ በዲላ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝና የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችልም ተናግረዋል
No comments:
Post a Comment