Sunday, January 26, 2014

የአቶ ጌታቸው ረዳ መልዕክት በስዊድን ለሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት ህዝባዊ ስብሰባ እንዲሁም የጉባኤው አዘጋጆች።

Posted by moreshinfo on December 12, 2013 በአካል በስብስባው ባለመገኘቴ ይቅርታ እየጠየቅኩኝ ፤ በዚህ ደብዳቤ ላስተላልፈው የፈለግኩት መልእክት ጉባኤው ስለተጠራበት ጉዳይ ትንተና ለመስጠት ሳይሆን ማስገንዘብያ ብቻ ነው። በአካል ስለማልገኝ ትንታናውን ለሌሎች ወንድሞቼ እንዲወጡት ትቸዋለሁ።አድማጩ አንዲያውቀው አስፈላጊ ነው ስለምለው ጉዳይ አነጋጋሪ ስለሆነ አጭር መልእክቴ እነሆ። እኔ በተወለድኩበት ትግራይ ክፍለሃገር ውስጥ ወያኔ የትግራይ ሪፑብሊክ ለመመስረት መነሻ አድርጐ ያሰራጫቸው መግለጫዎቹ መሰረት በማድረግ “ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ” ብሎ እራሱን ሰይሞ ወደ ጫካ በመግባት ከደርግ ወታደራዊ መንግሥት ጋር ባካሄደው የትጥቅ ትግል በተለያዩ ምክንያቶች “በለስ ቀንቶት” ደርግን አሸንፎ የመንግሥት መንበር ከተቆጣጠረ ወዲህ ኢትዮጵያን እንደ ደቡብ አፍሪካ ዘረኛው የነጮች መንግሥት በጐሳ/በቋንቋ አስተዳደር አዋቅሮ “ጸረ አማራ” ሕብረተሰብ እና “ጸረ አገር” ዕቅድ ነድፎ ሕዝቧን እና አንድነቷን ለማበጣበጥ የተመሰረተ የፖለቲካ ድርጅት እንደሆነ በተለያዩ ጊዜያት በጽሑፍም በቃለ መጠይቅም በመጽሐፍቶቼም ገልጫለሁ። አሁን በሥልጣን ላይ እየባለገ ያለው “ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ” በታሪካችን ውስጥ ለጆሮ እና ለዓይን የሚከብዱ፤ በሕዝባችን እና በአገራችን ሉአላዊ ክብር ላይ ብዙ አስነዋሪ ወንጀሎች የፈጸመ ቢሆንም፤ ለዓይን እና ለጀሮ ጐልቶ የሚታየው ጥቃት በአማራ ሕብረተሰብ ሕይወት ላይ ፈጽሟል። ይህ የአማራ ጥቃት ከመላ የተለያዩ የአገሪቱ ጐሳዎች ሁሉ በይበልጥ የጥቃት ማሕደሩ የተከመረው በአማራው ላይ ነው። በዚህ ጎሳ (ዘር/ሀረግ) ላይ ያነጣጠረው የወያኔ ጥቃት በምንም መለኪያው በማንኛውም ጎሳ ላይ የደረሰው ጉዳት ሲነጻጸር የት የሌለ ነው። አማራው ለዘመናት ሲኖርባቸው አካባቢዎች ውጣ እየተባለ ከነቤተሰቦቹ ሲባረር፤ኦሮሞው፤ትግሬው፤አደሬው፤ሶማሌው፤አፋሩ፤ጋምቤለው፤ወላይታው፤ወዘተ…ወዘተ… አልተባረረም። ከነ ነብሱ ወደገደል ተገፍትሮ አልተጨፈጨፈም።በዚህ-ከተማመንን፤አማራው ለምን ለብቻው ጥቃቱ አንዲነገርለት ተፈለገ ብለው ለሚጠይቁን ዜጎች ለምን አንድንጮኽለት እንደተፈለገ ግልጽ ይሆንላቸዋል። ከላይ አንደገለጽኩት የዚህ ሕብረተሰብ ጥቃት እና መፍትሔው ምን መሆን እንዳለበት ለመግለጽ በአካል ስላልተገኘሁ በጽሑፍ መዘርዘሩ ቦታ ስለማይበቃ፤ይህንኑ ገለጻ ለወንድሞቼ በመተው አድማጩን ለማስገንዘብ የምፈልገው ነገር አለኝ የምለው ነገር የሚከተለው አጭር ማስገንዘብያ ነው። ይኸውም፤ ይህ ጉባኤ ለምን በአማራ ጥቃት ላይ ማተኮር አንዳለበት ቅሬታቸውን በማሰማት በግል ‘በቴክስት’፤ ‘በኢመይል’ መልእክት እና ‘በስልክ’ በጉባኤው እንዳልሳተፍ ከተሳተፍኩ ደግሞ በሚዲያ ስሜን እንደሚያጠፉት በማስጠንቀቅያ መልክ ያስጠነቀቁኝ ወገኖች እና የአማራው ልዩ ጥቃት ሁኔታው መረዳት የተሳናቸው ግብዝ ወገኖች አንዳሉ ለማስገንዘብ እፈልጋለሁ። እነኚህ ግለሰቦች ያልተረዳቸው ሁኔታ ‘አማራው’ ከማንኛውም ኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ተለይቶ “በሻዕቢያ”፤ “በወያኔ” ፤ “በኦነግ”፤ ዓረባዊ ነኝ በሚለው “ኦብነግ” እና በተቃዋሚው ክፍል የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ የዜና ማሰራጫዎች፤በተለይ በውጭ አገር የተቃዋሚውን መልሕቅ የተቆጣጠረው ከኤርትራ ሻዕቢያው ቡድን ጋር የተቆራኘው ግንቦት 7 ብሎ እራሱን የሚጠራው “ጸረ አማራ” ኤሊቱ ክፍል በአማራ ሕብረተሰብ ላይ የአካል እና የስነ ልቦና ስብራት አድረሰውበታል። ተምረናል ብለው ራሳቸውን የሚያመጻድቁ ግብዝ ኤሊቶች አማራውን ሕብረተሰብ በመጽሐፋቸው “ቀጥቅጠውታል” (የዘረኛውን የአንዳርጋቸው ጽጌ ‘የአማራ ሕዝብ ከየት ወዴት” መጽሐፍ- በጥሞና ማንበብ አለባችሁ)። በጥይት ረሽነውታል። እርጉዝ እናቶች እና እህቶች ከነህይወታቸው ወደ ገደል ተወርውረዋል። ከሚኖሩበት አካባቢ በጉልበት ተገፍተው ንብረታቸው ሳይዙ እና ከቤተሰቦቻቸው እየተነጠሉ ፡ አንዳንዶቹ ከመቅጽበት አንዳንዶቹ ደግሞ በ24 ወይንም በ48 ሰዓት የጊዜ ገደቦች ተሰጥቷቸው አንዲባረሩ ተደርጓል። በጥቂት አመታት ልዩነት የሌሎቹ ጎሳዎች የሕዝብ ቁጥር ሲጨምር አማራው ግን 2 ሚሊዮን አማራ ሕብረተስብ ከምድረገጽ መጥፋቱ በእኛ ጥናት ብቻ ሳይሆን በወያኔ ስታትስቲክ ጭምር ወያኔ በፓርላማው አምኖ ገልፆታል። በወጣት እናቶች እና በአዛውንቶች ክብር ላይ ጥቃት ተፈጽሟል። ‘ዓይነ ስውራን’ ወንዶች አዛውንቶች ‘ብልታቸው’፤እናቶች ደግሞ ‘ጡታቸው’ በቢላዋ ተሰልበዋል። ህፃናት በትምህርት ገበታ ላይ አንዳሉ አንዳይወጡ የየክፍሎቻቸውን መዝግያዎች ተቆልፎባቸው ከነ ነብሳቸው ተቃጥለው እንዲሞቱ እሳት ተለኩሶባቸው አልቀዋል። እናቶች አንዳይወልዱ ማሕጸናቸው አንዲደርቅ መርዝ አንዲወጉ ተደርጓል። አሁንም ጥቃቱ አላባራም። ግብዦቹ ‘ይህንን ጥቃት’ ነው “አታጋልጡ” የሚሉን።በዚህ ጉባኤ ስለ አማራ ጥቃት እና ውረደት ስቃይና መከራ ለሕብረተሰብ መንገር “ጸረ ኢትዮጵያዊነት” ነው እያሉ የአማራው ሕብረተሰብ ጥቃት ተሸፍኖ እንዲቀጥል በማወቅም ባለማወቅም አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ወገኖች አንዳሉ ለመግለጽ እወዳለሁ። በተለይ ለምን አንደዚህ አንደሚሉ ጥቂት ልበል። ስለ አማራ ሕብረተሰብ ጥቃት ማጋለጥ፤መፈትሄ ማፈላለግ ማለት የወያኔ የጐሳ አወቃቀር ፖለቲካ መከተል ነው በማለት “ጐሰኝነት” ነው ይሉታል። ይህ “ጥርቅም” ያለ “ድንቁርና” ለወያኔዎች እና ለመሳሰሉ ለጸረ አማራ ቡድኖች የሚያመቻች ተጨማሪ ጥቃት ነው። እኛ አማራው “ይገንጠል” የራሱ ክልል ይከልል፤በአካባቢው የሚኖሩ ትግሬዎች፤ኦሮሞዎች፤የደቡብ ሕዝብ ጎሳዎች ከአማራ አከባቢ መሬቶች ይባረሩ፤ይገደሉ፤ የሚል ቅስቀሳ እና አጀንዳ የለንም። እኛ እና ወያኔ በጎሰኛነት በመወንጀል የሚያያይዙን “ደንቆሮዎች” የዘር ማጥፋት ወንጀሉና ሰበቡ አላጠኑም ወይንም ሆን ብለው የአማራው ጥቃት አንዲቀጥል የመሰሪ ቡድኖች ተላላኪዎች ናቸው ማለት ነው።ለመሆኑ ከኛ በላይ የጐሳ ፖለቲካ አምርሮ የተቃወመ እና በየሚዲያው የተከራከረ እና መጽሐፍትም የጻፈ ማን ነው? ማን በማን ላይ ነው ስለ ኢትዮያዊነት ለመመጻደቅ የሚሞክረው? ስለ አማራ ጥቃት መናገር እኛ ጐሰኞች፤እነሱ ልዩ “ኢትዮጵያዊያን” የሚሆኑበት በየትኛው መመዘኛቸው ነው? በጣም የሚገርማችሁ ደግሞ፤ በቴክስት እና በስልክ ያስጠነቀቀኝ ግለሰብ “ዶክተር አስፋ፤ ዳኛ ከተማ ደኔ እና አንተ አቶ ጌታቸው ረዳ፤ ስለ አማራ ሕብረተሰብ ጥቃት ስትናገሩ ‘አማራ’ ወክሎናል የምትሉት የምስክር ወረቀት አሳዩን ማለቱ “በጣም አስገራሚ ድንቁርና ከመሆን አልፎ፤ ነገሩ በጣም አስቆኛል። ስለ ትግሬ ወይንም ስለ ኦሮሞ ጥቃት ስንናገር ወይንም “ታሪክ፤ባሕል፤ጦርነት፤ፖለቲካ” አንስተን ስንተነትን ይህ አነጋጋር ‘ወያኔዎች’ አንዲሁም ‘ኦነጐች’ ስለ ጎሳችን ‘እኛ’ እንጂ አንናተ አያገባችሁም፤ስለ እኛ ወክለህ ተናገርልን ብሎ የሰጣችሁ ፈቃድ አሳዩን፤ እያሉ በጠባብ ሕሊና የሚንቀዠቀዡት የጠባብ ቡድኖች ቅጂ ቅስቀሳ ሰለባዎች አንደሆኑ ነው የተረዳሁት። ለነገሩ ወያኔም እኮ “ዲያስፖራ ተቃዋሚ ስለ አገር ውስጥ ላለው ሕዝብ መናገር አይችልም። መበት የለውም፤ ውክልና ወረቀት አምጡ፤ እያለ ድንቁርናውን እያስተጋባብን ነው። ታዲያ የኛ የምንላቸው ተቃዋሚዎች ተመሳሳይ ጥያቄ ሲጠይቁን ከወያኔ ድንቁርና በምን ይሻላሉ? ማን ወከላችሁ? ብሎ ለጠየቀኝ ሰው መልሱ ጥቃት የደረሰበት “አማራ ሕብረተሰብ” ስለ ጥቃቱ እንድንናገርለት በአንደበቱ ጥሪ አድርጎልናል! ይህንን የቴፕ ድምፅ ለማስረጃ አንዲደመጥ ልኬአለሁ። 45 ደቂቃ የፈጀ ዝርዘር በኢትዮጵያን ሰማይ አውድዮ ቪድዮ ክፍል ተለጥፎ ይገኛል። ድረሱልን ያሉንን ጥሪ ግን ባጭሩ ይኼው። እነሆ ከ4 አመት በፊት ጥሪው በጀርመን ራዲዩ ። Active ethnic cleasning in Ethiopia በሚል ርዕስ በዩቱብ እና በኢትዮፕያን ሰማይ ድረገጽ የተለጠፈው ድምፅ እነሆ ያድምጡ። የተጠቂዎቹን የድረሱልን ድምፅ መልእክቱ እንዳዳመጣችሁት፤ መልእክቱ የሚለው “ለሚመለከተው ክፍል እባካችሁ ስለ እኛ ስም ሆናችሁ አነጋግሩልን አደራ! አደራ! አደራ!” የሚለውን የአደራ መልእክት ተንተርሰን ነው እኛም የተጠቂዎቹ አደራ ላለመብላት እዚሁ እየተነጋገርን ያለንበት እና ያስገደደን ምክንያት። ስለዚህ ስለ አማራው ሕብረተሰብ እንደትናገሩ ማን ወከላችሁ? የውክልና የፈቃድ ወረቀት አሳዩን፤ በማለት የሚዘላብዱ እና ስለ አማራ ሕብረተሰብ እናቶች እና አባቶች ጥቃት ‘ትንፍሽ’ አትበሉ የሚሉን ወገኖች የአጥቂዎቹ ተባባሪዎች ከመሆናቸው በፊት ልቦና አንዲገዙ አጋጣሚውን ተጠቅሜ ልመክራቸው እፈልጋለሁ ። በዚህ አጋጣሚ በተጓዝኩበት አካባቢ አመች ሆኖ ካገኘሁት ከናንተው ጋር ለመቀላቀል እሞክራለሁ፡ ካልሆነልኝ ግን ባለመገኘቴ እያዘንኩ፤ የዚህ ሕብረተሰብ ጥቃት ተጠንቶ አጥቂዎቹ ወደ ሕግ የሚቀርቡበት ሁኔታ ማመቻቸት አስፈላጊ መሆኑን ተገንዝበን፤ የተጠቂዎቹ ልሳን ዕርዱን በማለት ያስተላለፉትን “አደራ!” ተግባራዊ ለማድረግ እንበርታ፤ በርቱ። አማራው በዘር ማጽዳት ዘመቻ ሲጠቃ፤ በደፈናው “ስለ ኢትዮጵያ” ጥቃት እንጂ ስለ አማራ ጥቃት አትወያዩ የሚል ስሜት ያሰከራቸው አገራዊ ትርጉም በቅጡ ያልተማሩ ጋላቢዎች፤ የአማራው ሕብረተሰብ ጥቃት ሰሚ ጀሮ አንዳያገኝ የሚጥሩ ወገኖች እየጋለቡበት ካለው ልጓም የበጠሰ ስሜት መቆጠብ ይኖርባቸዋል። በዚህ መሰሪ የወያኔ የጥቃት ዘመቻ የአማራ እናቶች ማህፀን ቢመክንም ከአጥቂዎቹ እጅ ያማለጣችሁ የአማራ ተወላጆች ሁሉ የእናቶቻችሁ እና የእህቶቻችሁ ትኩስ እምባ እንዲቆም ለማገዝ ሐላፊነቱ በናንተው በአማራዎች ብቻ ሳይሆን በሌሎች ኢትዮጵያዊያንም ዘንድ የዜግነት ግዴታቸው አንዲወጡ ጥሬየን አቀርባለሁ። በዚህ አጋጣሚ ከአማራ ሕብረተሰብ የተወለዱ ውጭ አገር እና ውስጥ አገር የሚኖሩ የሕግ ጠበቆች በየድረገጹ የሚያቀርቧቸው ሳምንታዊ/ወርሃዊ “የፖለቲካ ጅላጅል ትንተናቸውን” አቁመው የወላጆቻቸው እና የእህቶቻቸውን የድረሱልን ጥሪ፤ በቅርቡ በዓለም አቀፍ ፍርድ አጣሪ ተቋም በማመልከት “ኢትዮጵያዊያን ኦጋዴን ሶማሌ ተቃዋሚዎች” በወያኔ ላይ እንዳስመዘገቡት ክስ፤ እናንተም የወላጆቻችሁ እና የእህቶቻችሁን እምባ ማድረቅ እና ወንጀለኞቹን ወደ ሕግ የማቅረብ ሐላፊነት ከናንተው ይጠበቃል። ይህ የክህደት ዘመን በመንደላቀቅ እና በምቾት ኑሮ በውጭም በውስጥም አገር ጆሮውን ደፍኖ ሰምቶ አንዳልሰማ ያጠረመመው ‘አማራው ልሂቅም ’ ሆነ በግንቦት 7 ስም ከኤርትራው ቡድን ጋር ትከሻ ለትከሻ እየተሻሸ ያለው አማራው ሊሂቅ እና ተከታየቹ ብቻ ሳይሆኑ ይህንን ጐሳ ያጠቁትና በመጽሀፍቶቻቸው እና በሕዝባዊ ንግግራቸው የዘለፉትና የከዱት፦ የንጉሥ ተፈሪ የልጅ ልጆች ነን የሚሉን ውጭ አገር እና በውስጥ አገር የሚኖሩ መሳፍንቶች ‘አማራን እያጠቃ ካለው የወያኔ ቡድን እና መሪዎች ጋር በመተባባር’ አሳፋሪ የሆኑ የክህድት ተግባሮች ፈጽመዋል። ለመግለጽ የፈለግኩት ጥንቃቄ የጎደለበት በውጭ አገር የስለላ መረቦች እየታገዘ የፖለቲካ ቁማር እየተጫወተ ያለው የምሁሩ ክፍል ብቻ ሳይሆን፤ የንጉሱ የልጅ ልጆች ጭምር ስለ አማራ ጥቃት ከመጤፍ ያለመቁጠራቸው አንዱ አሳዛኝ እና መራራ ያደረገው ገጽታው ስታዘብ ሃዘኔ እጅግ የበረታ ያደረገዋል። ይህ የክህደት ዘመን ስትመለከቱ “ለአማራው” ማን ያልቅስ? ስለ አማራው ጥቃት አንድትነጋገሩ “በስሜ አንድትናገሩልኝ ወክያችሗለሁ ብሎ የሰጣችሁ የምስክር ወረቀት ውክልና አሳዩን” የሚሉ ተቃዋሚ ነን የሚሉን የአማራ ተወላጆችም ሆኑ እንዲሁም “አማራ ብቻ ስለ አማራ ቢናገር ያምርበታል፡ትግሬ የሆናችሁ ተቃዋሚዎች በዚህ ላይ አያምርባችሁም”፡ የሚሉን የወያኔ ሰዎች እና ተቃዋሚዎች የሚሰነዝሩትን አስገራሚ ተቃውሞ ጉባኤው እንዲነጋገርበት አሳስባለሁ። የገረመኝ ነገር፡ ስለ አማራው ጥቃት መነጋጋር ማለት ስለ ኢትዮጵያ ጥቃት መነጋጋር አይደለም ወይ? ስለ አማራው ጥቃት እና እንዴት ይቁም የሚለው መነጋጋር እንዴት “ጐሰኝነት” ነው ያስብላል? ስለ አማራ ጥቃት መቆርቆር በአገር በታኝነት ወይንም በጎሰኛነት አውቀውም ሆነ ባለማስተዋል የሚከሱን ወገኖች፤ ለጸረ አማራ ቡድኖች አመቺ መንገድ አመቻቺዎች እንዳይሆኑ የዕውቀት አድማሳቸው እንዲያሰፉ ከወዲሁ ለማሳሰብ እወዳለሁ። ከዚህ በተጨማሪ፤ በቅርቡ በሳውዲ አረብ በዘረኞቹ አረቦች የተቀነባበረው በኢትዮጵያዊያን ላይ የደረሰው የዘር ጥቃት ባንድነት አንደጮኽን ሁሉ፤ ከዚያ በከፋ መልኩ በወያኔ እና በወያኔ ተላላኪዎች አማካኝነት በአማራው ሕብረተሰብ ላይ የተፈጸመውና አሁንም በመፈጸም ላይ ያለው ጥቃት ተባብረን በመጮኽ ለዓለም ሕብረተሰብ ያላሰወቅንበት እና የሕግ ባለሞያዎች ነን ብለው በሳውዲ ዓረብ የደረሰው ጥቃት ለማጣራት ፈቃደኝነት ያሳዩን ወገኖች፤ ለምን በአማራው ጥቃት ላይ ታከቱ? ወይስ ጥቃቱ በውጭ ሰው ስለተከናወነ ልዩ ጥቃት ሆኖ፤ በውስጥ ጠላት በአማራው የተፈጸመ ጥቃት ግን እንደ ጥቃት ውርደቱ አልተሰማንም? ለምን? አገር ውስጥ ያለው ተቃዋሚም “ሰላማዊ ሰልፍ ሲታገድ” ፊቱን አዙሮ ወደ እየቤቱ ከመመለስ እና በጋዜጦች እሮሮ ከማሰማት ሌላ ምን አድርጓል? እስክንድር እና ጓደኞቹን አንኳ ለማስፈታት “የረሃብ አድማ ሲያደርጉ እና የተጥለቀለቀ እምቢታ፤ የስራ ማቆም አድማ፤ ልገማ ወዘተ.. ለማድረግ የማይችል “ድውይ” ተቃዋሚ ነው። አማራው በዚህ ዳይለማ/ ትንግርት ስቃዩ የሚጮኽለት አጥቷል። የታወቀው የህግ ባለሞያ ደ/ር ያዕቆብም “የተለመደው አፉን ከፍቶ የሕግ አንቀጽ ከመጥቀስ ሌላ” እሱ በደምብ አድርጐ ከሚያውቀው እና ከሰራበት የዓለም አቀፍ መድረክ ፍርድ ቤት እና የመሳሰሉት ተቋማት ወደ ውጭ አገር ተጉዞ መሰል የሕግ ባለሞያዎችን አስተባብሮ ስለ አማራው እልቂት “የመሰረተው” አቤት ያለበት የሕፈግ ክስ የለም። ለምን? አሁንም አንድ ነገር ልጨምር። በሚገርም ሁኔታ ከማንኛውም ተቃዋሚ ጸሐፊዎች ቀድሜ በሳውዲ የደረሰው ጥቃት ስሰማ የጻፍኩት እኔ ነበርኩ። በዛው መልእክቴ ላይ “ኢትዮጵያዊያን የሕግ ባለሞያዎች ከውጭ አገር ባለሙያዎች ጋር በመነጋጋር ” ሳውዲ ድረስ ሄደው ጥቃቱ አንዲያጣሩ የጠየቅኩኝም የመጀመሪያው ሰው እኔ ነበርኩ (የለጠፍኩትን ፋይል እና ቀን ተመለክቱ)። በዛው አንጻር በአማራው ሕብረተሰብ ላይ የደረሰው ጥቃት ከብዙ አመታት በፊት በተደጋጋሚ “የሕግ ባለሞያዎች” ጉዳዩን አጣርተው ወደ አለም ተቋማት አቤት አንዲሉም ተደጋጋሚ ተማጽኖየን አቅርቤላቸው ነበርኩ። በቅርቡ አምናም አንዲሁ ከብዙ አመታት በፊት አማራን በማጥቃት በጥቃቱ የተሳተፉ ግለሰቦች “ፎቶግራፋቸው” እና “አድራሻቸው” “የፈረስ ስሞቻቸው ጭምር” የት አንደሚገኙ ተልኮላቸው፤ “የክስ እና የማጣራቱ ሁኔታ ለመጀመር ዝግጁ አይደለንም ” ብለው መልስ የሰጡኝ አሁን በሳውዲ ሁኔታ ግምባር ቀደም ተዋናይ ሆነው የቀረቡ የሕግ ባለሞያዎች ስታዘብ፤ ይህ አማራ የተባለው ወገን “ተከላካይ ጠበቃ” ለምን አንዳጣ ሳስበው በጣም ይገርመኛል። የሕግ ባለሞያዎች ናቸው የሚባሉት ኢትዮጵያዊያን ምሁራን በአማራው ሕብረተሰብ ፍትሕ ለማስገኘት እንዳይረባረቡ ያገዳቸው “ድልድይ” ምን ይሆን? የጀመሩት አቤቱታ ካለስ ለምን ይፋ አላደረጉትም? ይህ ብቻ አይደለም።ስለ ሳውዲ ጥቃት ማንሳቴ ላልቀረ ለሳወዲ ተጠቂዎች ትብብር አንፈልጋለን በሎ የተመሰረተው ቡድን አንድ ነገር ልበል። ቡዱኑ ትብብራችሁ አንፈልጋለን ብሎ ለመላ ወገኖች ጥሪውን ካስተላለፈ በሗላ፤ “በኮሚቴው ውስጥ ካሉት አንዳንድ ወገኖች የፖለቲካ ልዩነት ቢኖረንም፤ ችግሩ የጋራ በመሆኑ ለተጠቂዎቹ ሲባል ፖለቲካ ልዩነታችንን ለጊዜው ወደ ጐን ገፍቼ እናንተ በምታዋቅሩት እርዳታ የገንዘብም ሆነ የሕሊና ድጋፍ ለማድረግ አቅሜን ለማድረግ ዝግጁ ነኝ፡ በርቱ። መልሳችሁ እጠባበቃለሁ” ብዬ የላኩላቸውን “ኢመይል” ደብዳቤ እስካሁን ድረስ አንድ መስመር የምታክል ‘መልእክትህ ደርሶናል’ እንኳ መልስ አልሰጡኝም። ለምን? በጣም ግልጽ ነው። ይህ በፖሊተካ የነቀዘ ‘የኤሊት ስብስብ’ (ወንዱም ሴቱም) ነገሮችን የሚያዋቅረው ‘በቡድናዊ ትውውቅና የፖለቲካ ጥልፍያ’ የተተበተበ ኤሊት ክፍል ነው (ሚዲያውም ጭምር ያካተተ ‘አዲሱ አዲስ አበባዊ ኤሊት’)። ይህ ስሞታ የኔ ብቻ አይደለም፤ ብዙ ሰዎች ቅሬታ አላቸው። ይህን በተመለከተ ለወደፊቱ የምትመለከቱት ስዕል ይሆናል። የነዚህ ኤሊቶች ‘ደወል’ የሆነው “ኢሳት ቲቪ ስለ አማራው ጥቃት የጮኸ የመጀመሪያ የዜና ማሰራጫ ነው እያለ በውሸት ከንቱ የምጐሳ ንጥቂያ ሲያደረግ በጋዜጠኖቻቸው እና በተወካዮቻቸው አንደበት ሰምቻለሁ። ኢሳት የኦነግ፤ የሻዕቢያ፤ የኦብነግ ባንዴራ አሸብራቂ፤ የወያኔ ኢትዮጵያ የቆዳ ስፋት ካርታ ‘ለጣፊ’ ቀስቃሽ ሚዲያ መሆኑ “የመጀመሪያው ቲቪ” ነኝ ቢል ያምርበታል። ኢሳት አሁን ነው የተመሰረተው። የጀርመን ራዲዩ፤ የቪኦኤ፤ የኢሕአፓው “ፍኖተ ራዲዮ”፤ የካናዳው የሃዋርያ ጋዜጣ፤ ኢትዮጵያን ረጅሰተር፤ መኢዐድ፤ ጦቢያ ጋዜጣ፤ በግል ደግሞ እነ ዶክተር አሰፋ ነጋሽ እና እኔው እራሴ እና የመሳሰሉ ዜጎች እና ሚዲያዎች ኢሳት የሚባለው የግንቦት 7 አቀንቃኝ ሚዲያ ከመመስረቱ በፊት ስለ አማራው ሕብረተሰብ ጥቃት በሚገባ ለመላው ዓለም እያጋለጡ ከ1991 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን የዘለቁት ተቋማት እንዳልነበሩ በማድረግ “ኢሳት” የመጀመሪያው የአማራውን ጥቃት ያጋለጠ ሚዲያ ነው ሲል ታማኝ በየነ በለመደው ዘባራቂነት ባሕሪው ሲዋሽ ሰምቻለሁ። ይህ ውሸቱ “ያረመው” ሰውም ሆነ ሚዲያ የለም። የነቀዘው ሕብረሰተሰብም ከነጠቃው ባሕሪ ጋር አብሮ ኖግዷል። ይህ ነጠቃ ባንዳንድ የነቀዙ ኤሊት ጸሓፊዎች እየተደገመ ነው። ይህ ማሳሰቢያ ባጭሩ ጉባኤው እንዲነጋገርበት ይህ መልእክት እያሳለፍኩ ፡ ጉባኤው አንዲሳካ ምኞቴ ነው።ትግሉ ረዢም እና መራራ ቢሆንም፤ በመጨረሻ ግን የተጠቃው ሕዝብ ባሸናፊነት በድል ተራራ ላይ ቆሞ የተነጠቀው ክብሩን እና ሰንደቃላማው እንደገና ያውለበልባል። Read In PDF አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ (ኢትዮፕያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ) አሜሪካ ካሊፎርኒያ ስቴት – ሳንሆዘ ከተማ (2006) getachre@aol.com

No comments:

Post a Comment