Sunday, January 19, 2014

‹ዶክመንተሪው የመንግስትን የንቃት ጉድለት ያሳያል››

ዘመኑ ተቀይሯል ፣ ማህበረሰቡ ከየትኛውም በላይ ነቅቷል ከመንቃትም አልፎም መጥቋል ፣ ውሸት እና ሐሰትን መለየት የሚችል ትውልድ ተፈጥሯል፣ ያልተማረ የለም ሁሉም ተምሯል፡፡ ተምሮም ተመራምሯል፡፡ ይህ የንቃት አውድማ አውሮፓ እና አሜሪካ አሊያም ህንድና አውትራሊያ ላይ አልተገደበም፡፡ ይሀው ሐበሻዊቷ ሐገራችን ላይ በገሐድ እያየነው ያለነው ተጨባጭ እውነታ ነው፡፡
ሰዉ በዚህ መልኩ በጣም ነጥቆና ተመንጥቆ ባለበት የስልጣኔ ዘመን ህውሀት/ኢህአዲግ ድራማዊ ዶክመንተሪ ሰርቶ ህዝቡን ለማስበርገግ መመከሩ እራሱ የንቃት ጉድለት እንደተጠናወተው በግልፅ ያሳብቅበታል፡፡ ይህ የንቃት ጉድለት ያለበት መንግስት የንቃት ጉድለቱን እንደጨቀየ እንድናውቅለት ስለፈለገ በተደጋጋሚ የተራቆቱ ዶክመንተሪ በመስራት እያሳየን ይገኛል፡፡ መንግስት በገሐድ ህግ አታክቡሩ ብሎ ቢነግረን እንኳ እኛ እንደ ህዝብ ህገመንግስቱን በማክበር እና በማስከበር ለዚ መንግስት መሐይም እንደሆነ እና የንቃት ጉድለት እንዳለበት በግልፅ እያሳየን እንደሆነ ይሀው ለሁለት አመት ያደረግነው ሰላማዊ ትግል ምስክር ነው፡፡
አስቡት እስኪ ህውሐት/ኢህአዲግ ጂሐዳዊ ሐረካት የሚበለውን ዶክመተሪ ሰርቶ እነ ያሲን ኑሩን ፣ እነ አቡኬን ፣ እነ ካሚል ሸምሱን እና እነ አህመዲን ጀበልን በሽብር መወንጀሉ ነገር በህዝብ ዘንድ እንደተነቃበት እያወቀ ህዝብ ነቃን ማለቱ እንዳልገባው ለመመሰል ሚሞክረው ሙከራና ድጋሚ የተባነነበትን ዶክመንተሪ መልሶ ለነቃ ህዝብ ማሳየቱ ሆን ብሎ ነገር ፍለጋን ከማሳየት ውጪ ምን ሚያስተላልፈው መልእክት አለ፡፡ ይህ ነው በህዝብ እና በመንግስት መካከል ያለው ልዩነት !
ዛሬ በታየው ዶክመንተሪ ህዝብ እና መንግስትን ያስተዛዘበው ነገር መንግስት በህዝብ ላይ ጭቆና ደርሷል ብለው እውነቱን ሲያጋልጡ የነበሩ አካላትን በተለይ የአሜሪካን መንግስትን በጓብታናሞቤ በግልፅ በኢቲቪ ሲያማ እንዳልነበር ዛሬ ደሞ ሐሳቡን ቀይሮ የአሜሪካን መንግስትን በ ዲሞክራሲ ማሞገሱ ከህዝብ ጋር በድጋሚ ያስተዛዝበዋል፡፡ ሌላው ሚጎረብጥ ነገር ደግሞ ዛሬ በዶክመንተሪው ላይ በዴሞክራሲ እድገት የኢህአዴግ መንግስት የአሜሪካን እና የኢንግሊዝ መንግስት መብለጡን መንገሩ ነው፡፡ ልብ ካልን በዛሬው ዶክመንተሪ የአሜሪካ እና የኢንግሊዝ መንግስታት የፀረ ሽብር ህጋቸው ህዝብን ያላማከለ እንደነበር በመግለፅ የኢህአዴግ ደግሞ ህዝብ እና ፓርላማ እንደተወያየበት በይፋ ገልጾልናል፡፡ ከዚህ በላይ እሺ በህዝብ ላይ መቀለድ አለ?
ሳጠቃለው መንግስት በህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለው ሹፈት ደደብነቱን እና የህሊና ንቃት ጉድለቱን ሲያንፀባርቅበት ህዝብ ግን እያሳየ ባለው ሰላማዊ ትግል ምን ያህል እንደነቃና እንደመጠቀ እያረጋገጠት ይገኛል ፡፡ ህዝብ እያሳየ ያለው ንቃትም አጠናክሮ ሊቀጥልበት ገባዋል፡፡
ፍትህ ለኢትዮጵያ ሙስሊም፡፡
Image

No comments:

Post a Comment