በየቦታዉ የሚታየዉ ደካማ የትምህርት አሰጣጥ መሃይምነትን ቀደም ሲል ከተገመተዉ በላይ እንዳስፋፋም UNESCO ትምህርትን በተመለከዉ 11ኛዉ ዓመታዊ ዘገባዉ አስታዉቋል። የትምህርት ፖሊሲም በርካታ ልጆች ወደትምህርት ቤት እንዲሄዱ ብቻ ሳይሆን እኩል እድልና የተሻለ ትምህርት እንዲያገኙ በሚለዉ ላይ እንዲያተኩርም ድርጅቱ ጠይቋል።
በድርጅቱ የትምህርት ለሁሉም ፕሮጀክት ዳይሬክተር ፓዉሊን ሮዝ ዘገባዉ በጥቅሉ በመላዉ ዓለም በመማር ማስተማር ሂደት ያለዉን ቀዉስ እንደሚያሳይ ገልጸዋል፤ «ዘገባዉ በመላዉ ዓለም በሚታየዉ የመማር ማስተማር ቀዉስ ላይ ያተኮረ ሲሆን 250 ሚሊዮን ልጆች መሠረታዊ የሚባለዉን ትምህርት እንዳላገኙ ያመለክታል። እናም ዘገባዉ መምህራንን ማፍራት ላይ ተጨማሪ ገንዘብ እንዲዉል እና ምርጥ መምህራን እነዚህን ልጆች እንዲያስተምሩ መደረጉን ማረጋገጥና የመማር ነገር እንደዋዛ እንዳይታይ ያሳስባል።»
የወደፊት ትዉልድ እጣፈንታ በመምህራን እጅ ላይ መሆኑን ያመለከቱት የUNESCO ዋና ዳይሬክተር ኢሪና ቦኮቫ በበኩላቸዉ በመጪዉ የጎርጎሪዮሳዊ ዓመት 2015 ከአምስት ሚሊዮን በላይ መምህራን እንደሚያስፈልጉ ገልጸዋል።
Source/http://www.dw.de/
No comments:
Post a Comment