Feb.1/2014
የአማራ ክልል ም/ ፕሬዚዳንት እና የብአዴን ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን “የአማራው ህዝብ ሰንፋጭ የሆነ ትምክተኝነት የተጠናወተው በመሆኑ በቤንሻንጉልና በሌሎችም ቦታዎች ለመሰደዱ ምክንያት ሆኖታል” በማለት፣ ለብአዴን ነባርና አዳዲስ ካድሬዎች ተናግረዋል።
ካድሬዎቹ “የአማራው ህዝብ ለምን ይሰደዳል? ለምን በእየክልሉ ጥቃት ይደርስበታል? አማራውን ከጥቃት ለመከላከል ለምን ሙከራ አይደረግም በማለት ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን፣ ም/ል ፕሬዚዳንቱ የአማራው ህዝብ በቅድሚያ እንዳይሰደድ ለማድረግ ስራ እየተሰራ ነው፣ ነገር ግን ከተሰደደ በሁዋላም ቢሆንም ሰንፋጭ የሆነውን ትምክህተኝነቱን በመተው ከሌላው ጋር ለመኖር መልመድ አለበት ብለዋል።
አማራው “በባዶ እግሩ እየሄደ የሚናገረው ንግግር ግን መርዝ ነው” ያሉት ምክትል አስተዳዳሪውና የብአዴን የጽህፈት ቤት ሃላፊው፣ ይሄ መርዝ ንግግሩ አንድ የሚያደርግ አይደለም ሲሉ አክለዋል።
ከኢትዮጵያውያን ጋር አብሮ ለመኖር አማራው የትምክህት ለሃጩን ማራገፍ አለበት ያሉት አቶ አለምነው፣ ይሄ ለሃጭ ሳይራገፍ በጋራ መኖር አይቻልም ሲሉ ድምድመዋል።
ማንኛውም ስም ያወጣ ሙትቻ ፓርቲ ሁሉ መንገሻው አማራ ክልል ነው ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ፣ ምክንያቱንም ሲገልጹ ትምክህትን እንደ ምግብ ስለሚመገበው ነው ብለዋል። ያንን ምግብ እየተመገበ እንደሚያቅራራም ገልጸዋል።
አንዳንድ የብአዴን አባላት የምክትል ፕሬዚዳንቱ ንግግር እጅግ እንዳበሳጫቸው ለኢሳት ተናግረዋል።
የብአዴን ካድሬዎች አንቀጽ 39 ለምን አይወጣም በማለት ላነሱት ጥያቄ፣ እኝሁ ፕሬዚዳንት ሲመልሱ አንቀጽ 39 ባይኖር ኖሮ ኢትዮጵያ ደቡብ ሱዳን እንደሆነቸው ትሆን ነበር በማለት መልሰዋል ። አንቀጽ 39 በህዝቦች ዘንድ መተማመን መፍጠሩን፣ አቶ መለስ ዜናዊ በሞቱበት ጊዜ በገሃድ መታየቱን ም/ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል
የድምጽ ማስረጃውን ቀርጸው ለላኩለን በስብሰባው ላይ የተካፈሉ የህክምና ባለሙያዎችን ለማመስገን እንወዳለን።
<iframe width="640" height="360" src="//www.youtube.com/embed/4EcVDwlZ9tg?feature=player_embedded" frameborder="0" allowfullscreen></iframe>
አቶ አለምነው መኮንን አማራ አይመስሉኝም፡፡ ልክ እንደነ ደመቀ መኮንን እና ኤሌው ጎበዜ የሌላ ብሔረሰብ አባል የሆኑና በአማራ አገር በመኖራቸው ብቻ አማርኛ ስለተናገሩ ወያኔ የብሔር ጀርባቸውን አጣርቶ ያስጠጋቸው አገው መስለውኛል፡፡ ለምሳሌ በ2002 ዓ.ም. ምርጫ አያሌው ጎበዜ የተወዳደረው አንኮበር ከተማ ነበር፡፡ ሕዝቡ ግን አያውቀውም፣ እነድ ዘመድ አንኳን የአንኮበር ተወላጅ የለውም፡፡ ልክ በረከት ስምኦንና አዲሱ ለገሠ በግድ ጎንደሬ ነን ብለው እየሄዱ እንደሚወዳደሩት ማለት ነው፡፡ በጣም የሚያስቀው ደግሞ የተፈራ ዋልዋ ነው፡፡ መንዝ ነው አገሬ፣ ተወልጄ ያደግሁትም እዚያው መንዝ ነው ማቱ ነው፡፡
ReplyDeleteስለዚህ አለምነው መኮንን የአማራ ብሔረሰብን እንዲህ ጨክኖ የተሳደበው ትንሽ ሥጋ እንደ መርፌ ተወጋ እነዲሉ እንጥፍጣፊ እንኳን አማራነት ስለሌለው ነው፡፡ እርግጠኛ ነኝ በሌላው ያሰድባሉ እንጂ ትግሬዎች እንኳን እንዲህ ደፍረው ፀያፍ ስድብ ከአፋቸው አይወጣም፡፡ የሆነ ሆኖ አለምነው መኮንን ለምን እንዲህ ሰደበን ብለው የሚያማቸው እውነተኛ የአማራ ልጆች አጠገቡ ካሉ ዋጋ ያስከፍት ይሆናል፡፡ ቆይተን የምናየው ነው፡፡
አማራ በጣም ጨዋና ስነ ምግባር ያለው ህዝብ ነው፡፡ ዛሬ ማንም ንፍጣም እየተነሳ እንደሚሰድበው አይደለም፡፡ ለማኛውም የጊዜ እንጂ የሰው ጀግና የለውምና አለምነውም ይሁን ወይንም አያሌውና ደመቀ ወደፊት ታሪክ ይፋረዳቸዋል፡፡ ከወያኔ ለሚጣልላቸው ጥቂት ፍርፋሪ ብለው የሚፈጽሙት የአገር ክህደት ወንጀል ልክ እንደ መለስ ዜናዊ ቀድመው ካልሞቱ በስተቀር ለፍርድ ያስቀርባቸዋል፡፡ የደርግ አባላት ውድቀት ጥሩ ምሳሌ ነው፡፡
NO!! NO!! AYALEW IS BY FAR CONCERNED TO AMHARA PEOPLE !!
Delete@Dej Azmach, for true I found you are "dej azmach"!!??? the whole speech made by the vice president of the region may be extremely bad and hot issue, but why do you opt to link it with other ethnic members who stood for Amhara for years and even life time??? Why are you pointing your stupid words to either "Agew" or "Tigray" or what u are passionate at calling "woyane"???? If you think that u are the one who can contribute to the development of our society, you should really feel ashamed of yourself. How can you insult others because you felt being insulted??? Wasn't it wrong at the very beginning?????? I feel sorry about your..bla blas.............
ReplyDelete