ናትናኤል ካብቲመር (ኦስሎ)
“እናንት ከእስር ቤት ፍርግርግ ጀርባ ያላችሁ የእውነት ሐዋርያዎች የቆማችሁለትን ፣ የተሰቃያችሁለትን እውነት የኢትዮጲያ ህዝብ ብቻ ሳይሆን አለምያውቀዋል አካላች ሁ እስር ቤት ሆኖ በህመም በግርፋት ቢሰቃይም ስብዕናችሁ ግን ውብ ሆኖ ይኖራል”
አምባገነኑ የወያኔ መንግስት እንደተራ ወንጀለኞች በየእስር ቤቱ የሚያንገላታቸውንፁሀን እስረኞች በአለማቀፍ ደረጃ ክብርን የተጎናፀፉ መሆናቸውን ስንናገር እኛየምንደግፈውን ሀሳብ ስለደገፉ ወይም አምባገነናዊውን ስርዓት ስለሚቃወሙ ብቻ አይደለምስለእውነት ስለቆሙ ነው። የወያኔም መንግስት የሚጠላቸው ሊያጠፋቸውም ሌት ተቀንየሚታትረው የሱን በውሸት የተመሰረት ስርዓት የሚያጋልጥ የጠራ እውነት በመፃፋቸውበመናገራቸው ነው። አዎ ለወያኔ ስርዓት አሸባሪ ናቸው ምክንያቱም የውሸት ክምር አንዲትእውነት ትንደዋለችና።
በተለያዩ ግዜያት የተለያዩ አለማቀፍ ተቋማት ለነኚህ ለእውነትና ለነፃነት የቆሙጀግኖች የተለያዩ ሸልማቶችን በክብር ሰጥተዋቸዋል። ነገር ግን የወያኔ ጥቅመኞች እነኚህንክቡር ሽልማቶች ለማቃለል ሲጥሩ ይስተዋላል። እኔም የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን የ2014 “ወርቃማ የነፃነት ብዕር (Golden Pen of Freedom Award)” ተሸላሚነት አስታክኬ ስለሸልማቶቹ ክቡርነት ፣ ስለሸላሚ ድርጅቶችታላቅነትና ለዚህ ክብር ስለበቁ የነፃነትና የእውነት ፈርጦቻችን አንዳንድ ነገር ለማለት ብዕሬን አነሳሁ።
ወርቃማ የነፃነት ብዕር (Golden Pen of Freedom Award)
ይህ ሽልማት በ አለማቀፍ ጋዜጦችና የዜና አዘጋጆች ማህበር (World Association of Newspapers and News Publishers WAN-IFRA) በሚባል አለማቀፍ ማህበር አመታዊ የፕሬስ ነፃነት ወርቃማ የነፃነት ብዕር ሽልማት በሚል ስያሜ እ ኤ አ ከ1961 ጀምሮበአለማቀፍ ደረጃ በየአመቱ የተከበረውን የጋዜጠኝነት ሞያ ለነፃነትና ለእውነት ያዋሉ በብዕራቸው ጨቋኝ መንግስታትን የታገሉ ግለሰቦችን ሲሸልም ቆይቷል።ማህበሩ ዋና መቀመጫውን በፈረንሳይ ፓሪስና በጀርመን ዳርምስታት እንዲሁም አጋር ቢሮዎችን በሲንጋፖርና ህንድ ያደረግ አለማቀፍ የጋዜጦችና ዜና አዘጋጆችማህበር ነው። ማህበሩም በአለማችን 120 ሀገራት የሚገኙ 18 ሺህ አለማቀፍ ዜና አታሚዎችን ፣ 15ሺህ ድረገፆችንና 3ሺህ ድርጅቶችን ይወክላል። ይህምታሪካዊ ሽልማት በየአመቱ በአለማቀፍ የጋዜጦች ኮንግረስና አለማቀፍ አርታኢዎች ፎረም (World Newspaper Congress and World Editors Forum) አመታዊ በዓል መክፈቻ ስነስርዓት ላይ ለተሸላሚው ይበረከታል።
በእስከዛሬውም ከተለያዩ የአለማችን ሀገራት ለነፃነትና ለእውነት የቆሙ ጋዜጠኞችና የጋዜጣ አዘጋጆች ለዚህ ክብር በቅተዋል። ለአብነት ለመጥቀስምያህል በ2013 የማይናማር ዜጋ የሆኑት ዶክተር ታን ኦንግ ፣ በ2012 ደግሞ የሜክሲኮን የፖለቲካ ሙስናና ስውር የሀሺሽ ንግድ የማጋለጥ ታላቅ የጋዜጠኝነትሞያዋን ለተወጣችው ሜክሲኮአዊቷ አናቤል ኸርናንዴዝ ፣ በ2011 ደግሞ በሀገር ክህደት ወንጀል ተከሶ በእስር ላይ የሚገኘው ኤርትራዊው ጋዜጠኛ ዳዊትይሳቅ ይገኙበታል። ጋዜጠኛ ዳዊት የስውዲን ዜግነት ያለው ኤርትራዊ ሲሆን በኤርትራ ታዋቂ የነበረችው የ “ሰቲት” ጋዜጣ አዘጋጅ ነበር።
በ2014 ደግሞ ማህበሩ በጃንዋሪ 27 2014 እንዳሳወቀው ኢትዮጲያዊው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ለዚህ የተከበረ ሽልማት በቅቷል። በቅርቡኢትዮጲያን ጎብኝተው የእውነተኛ ጋዜጠኞችን እስርና እንግልት እንዲሁም የፕሬስ ነፃነት መታፈን ያስተዋሉት የማህበሩ ፕሬዝዳንት ቶማስ ብሩንጎርድ የጋዜጠኛእስክንድርን የጋዜጠኝነት ሞያና ስነ ምግባር እንዲሁም ለእውነት ሲል የከፈለውን መስዋትነት አድንቀው የኢትዮጲያ መንግስት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋንእንዲሁም ሰለሞን ከበደን ፣ ውብሸት ታየን ፣ ርዕዮት አለሙን ፣ ዩሱፍ ጌታቸውንና መሰል ንፁሃን እስረኞችን በአስቸኳይ እንዲፈታ በአፅን ኦት ጠይቀዋል።
ጋዜጠኛ እስክንድር አቻ በማይገኝለት የጋዜጠኛ ስነ ምግባሩ በ2012 የባርባራ ጎልድ ስሚዝ የመፃፈ ነፃነት The PEN/Barbara Goldsmith Freedom to Write Award ተሸላሚም ነበር። ይህም ሽልማት ከተጀመረበት ከ1987 ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ በአለማቀፍ ዙሪያ ለ42 ጋዜጠኞች ተበርክቷል። ከነዚህም 42 ተሸላሚዎች ሰላሳ ሁለቱ ሽልማቱን ባሸነፉ ግዜ በእስር ላይ ነበሩ። በዚህ የሽልማት ዘርፍ ከጋዜጠኛ እስክንድር ሌላበ1989 ማርታ ኩምሳ የተባለች ኢትዮጲያዊት ጋዜጠኛ ተሸላሚ እንደነበረች የተሸላሚዎች ዝርዝር ያሳያል።
ሌላኛዋ በጋዜጠኝነት ሞያዋ ለአለማቀፍ የክብር ሽልማት የበቃችው ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ናት። የኮሎምቢያ ኤል ኤስፔክታዶር ጋዜጣ አዘጋጅየነበረውና የኮሎምቢያን ሀሺሽ ነጋዴዎችን በማጋለጡና በመቃወሙ ሳቢያ የተገደለው ጋዜጠኛ ጉዊሌርሞ ካኖ ስም የተሰየመው የዩኒስኮ ጉዊሌርሞ ካኖአለማቀፍ የፕሬስ ነፃነት ሽልማት (UNESCO/Guillermo Cano World Press Freedom Prize) የ2013 ተሸላሚ ሆናለች።
ከዚህ በተጨማሪም ጋዜጠኛ ርዕዮት በአለማቀፍ የሴቶች ሚዲያ ፋውንዴሸን (International Women's Media Foundation IWMF) የ 2012 Courage in Journalism Award ተሸላሚም ነበረች። ይህ ድርጅት መቀመጫውን ዋሽንግተን ዲሲ አድርጎ በ አለማቀፍደረጃ በተለያዩ የሚዲያ ተቋማት የሴቶችን ተሳትፎ የሚያበረታታ ድርጅት ነው። በዚህ የሽልማት ዘርፍ የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ባለቤት የሆነችው ጋዜጠኛሰርካለም ፋሲል የ2007 ተሸላሚ እንደነበረች የተሸላሚዎች ዝርዝር ያሳያል።
እነኚህ ጋዜጠኞች ከላይ ከጠቀስኳቸው በተጨማሪ ለበርካታ ክብርና ሽልማቶች መብቃታቸውን በዚህ ፅሁፍ ግን ዋና ዋናዎችን ብቻ ማንሳቴን አንባቢ ልብ እንዲልልኝ እማፀናለሁ። ለዛሬ በዚህ ላብቃ። በሌላ ግዜ ደግሞ ሌሎች ለነፃነትና ለእውነት የቆሙ በሃገራችን ብቻ ሳይሆን በአለማቀፍ ደረጃእውቅናና ክብርን ያገኙ ጀግኖቻችንን ለማቅረብ እሞክራለሁ።
“እውነት ነፃ ነች ፣ ውብ ነች ከጎኗም የቆመ ዘላለም እንደተከበረ እንዳማረ ይኖራል”
ለእውነትና ለነፃነት የቆሙ ንፁሃን ጋዜጠኞች ከእስር ተፈተው ከስደት ተመልሰው በሃገራቸው ስለሃገራቸው በነፃነት እንዲፅፉ የበኩላችንን እንታገላለን !!
No comments:
Post a Comment