To breathe Democracy in Ethiopia , lets us fight together for our Freedom and Justice !!!!!
የሰው ልጅ ካመረረ ቀጥሎ ምን እንደሚመጣ ማሰብ አይችልም፡፡ ለነፍሱም ፈጽሞ አይሳሳም፡፡ ወቅቱ 1998 ዓ.ም ነው፡፡ የ97 ሰባቱን ምርጫ ተከትሎ በተነሳው ብጥብጥ ባህር ዳር ከተማ ውስጥ ይኖር የነበረ ስሙን ለጊዜው የማላስታውሰውን ወጣት ሁኔታ ላካፍላችሁ፡፡ በእለቱ ከተማ ውስጥ ከፍተኛ ረባሻ ነበር፡፡ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ብጥብጡ ተዛምቱዋል፡፡ ቀደም ብሎ ተማሪዎች ወደ ክፍል እንዳይገቡ ስጋት ተፈጥሩዋል፡፡ ግቢው በፌዴራል ፖሊስ ተከቡዋል፡፡ የከተማው ወጣቶች ወደ ዩኒቨርሲቲው ገብተው ተማሪዎችን ይዘው መውጣት ያፈልጋሉ፡፡ ተማሪዎችም ከህብረተሰቡ ጋር ተቀላቅለው ድምጻቸውን ማስማት እና ተቃዉሞአቸውን መግለጽ ይፈልጋሉ፡፡ በመሀል ዙሪያውን የከበበው የፌዴራል ፖሊስ በታጠቀው መሳሪያ በማስፈራራት እየተከላከለ ያገኛል፡፡ ከውጪ ወደውስጥ እንዳይገቡ ሲከላከሉ ከውስጥያ ያለው ደግሞ ወደ ውጪ እንዳይወጣ በመሀል ሆነው ይከላከላሉ፡፡ ማሪዎች ያሳደባሉ፤ ይጮሀሉ፡፡ በዚህ መሀል በአዲሱ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንጻ በኩል አንድ ረዘም ያለ መልካማ ወጣት መሳሪያ ደግነው ለግዳይ የሚጠባበቁትን ወታደሮች ከምንም ሳይቆጥር ከወደ ስላሴ ቤተክርስቲያን አቅጣጫ በከፍተኛ ፍጥነት እየሮጠ መጣ፡፡ ወታደሮች ተመለስ! ተመለስ! ትሞታለህ እያሉ ይጮሀሉ፡፡ በለው! በለው! ያባባላሉ፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ያ ነፍሱ ፍትህ የተጠማች ወጣት ግቡ ወደ ግቢው በመምጣት ድምጹን ማስማት በመሆኑ የወታደሮችንም ጩኸት ሆነ የተደቀነውን መሳሪያ ከምንም አልቆጠረውም፡፡
No comments:
Post a Comment