Tuesday, February 11, 2014

አሜሪካ ለግብጽ የጦር ጄት ልትልክ ነው


ላለፉት በርካታ ወራት ሲወራለት የነበረውን F-16 የጦር አውሮፕላን በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ከአሜሪካ ወደ ግብጽ እንደሚላኩ BBC ዘግቧል።

የግብጽ ፕሬዝዳንር ሞ ሃመድ ሞርሲ ከስልጣን መባረር እንደመፈንቅለመንግስት ተወስዶ ቢሆን አሜሪካ ለግብጽ የምታደርገው የጦር መሳሪያ ድጋፍ ይቋረጥ የነበረ ሲሆን አሜሪካ ጉዳዩ ሳያሳስባት ማለፏ ግንኙነታቸው ላይ ተጽዕኖ እንደማይፈጥር ያሳያል።

በቅርቡ በሞ ሃመድ ሞርሲ የተመራው የፖለቲካ መሪዎች ስብሰባ ላይ የአባይን ጉዳይ ሲወያዩ ኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ማወጅን እንደ አንድ ሃሳብ ያቀረቡም ነበሩበት። ከዚያ ቀደም ብሎም ግብጽ በኢትዮጵያ ላይ ክተት ልታውጅ አስባለች የሚል ወሬ ከተለያዩ ምንጮች ሲናፈስ ቆይቷል።

ግብጽ ኢትዮጵያ የምትገነባውን ታላቁን የህዳሴ ግድብ አጥብቃ ከመቃወሟም ባሻገር ግንባታውን እንድታቆም ጠይቃለች። ኢትዮጵያም ግንባታውን በምንም ምክንያት እንደማታቆም በይፋ ገልጻለች።

አሁን የሚሰጧት የጦር አውሮፕላኖች ከታቀዱ ሃያዎቹ መካከል አራቱ ሲሆኑ ስምንቱ ባለፈው ጥር ወር የተላኩ መሆናቸው ይታወቃል። ይህ ዜና የተሰማው ኢትዮጵያም የጦር መሳሪያ ግዢ ልትፈጽም ማሰቧ በተወራ ሰሞን መሆኑ ይህ ጉዳይ ወዴት እያመራ እንደሆነ የማወቅ ጥያቄ የሚያስነሳ ነው።

ምንጭ wolaita.com via ኤኤፍፒ

No comments:

Post a Comment