'ኤርትራ ከኢትዮጲያ ጋር ለመሸማገል ጥያቄ አቅርባለች መባሉ የፕሮፓጋንዳ ብልጫ ለማግኘት የሚደረግ የህፃናት ጨዋታ ነው" የ ኤርትራው ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኤርትራ ቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት ከሁለት ጋዜጠኞች ጥያቄ እየቀረበላቸው እሳቸውም ምላሽ ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ ረጅም ቆይታ የነበራቸው ቢሆንም ኢትዮጵያን በተመለከተ የተናገሩትን ላልተመለከታችሁት ወይም ተከታትላችሁም ቋንቋውን ለማትሰሙት ጀባ ልበላችሁ፡፡ ትርጓሜዬ ግን ቃል በቃል ወይም እንደወረደ ሳይሆን ፅንሰ ሃሳቡን መሰረት ያደረገ መሆኑን እንድትረዱልኝ አሳስባለሁ፡፡
ጋዜጠኛው <<ሰሞኑን በመገናኛ ብዙሃን ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ለመሸማገል ጥያቄ አቅርባለች እየተባለ ነው፡፡ እውነት ነውን?>> ሲል ጠየቃቸው፡፡ እርሳቸውም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፡፡
<<ኤርትራ ሸምግሉኝ አለች፤ እንዲህ ብላለች፤ እንዲያ ተብሏል የሚባል ወሬ ብቻ ነው፡፡ ወያኔ ሲዳከም የሚያደርገው የህዝብ ግንኙነት /PR/ ስራ ነው፡፡
ውይይት እንፈልጋለን፤ ምናምን፤ ያላንኳኳው በር የለም፡፡ የፕሮፓጋንዳ ብልጫ ለማግኘት የሚደረግ የህፃናት ጨዋታ ነው፡፡
ይሄ ነገር ይቅርባችሁ ነው የምለው፡፡ ለምን በዚህ ግዜያቸውን እንደሚያጠፉ አይገባኝም፡፡ አንዳንድ ግዜም ይገርመኛል፡፡ ማንን ለማታለል ነው እንዲህ የሚያደርጉት፡፡ ፍላጎታቸው እኛን ሰይጣን አስመስለው የማሳየትና እራሳቸውን መልዓክ አድርገው የማቅረብ ሙከራ ነው፡፡
ውጭ ያለውም ሆነ እዚህ ያለው ወጣት በንዲህ አይነት ወሬ መደናገር የለበትም፡፡ ምንም አዲስ ነገር የለም፡፡>> ሲሉ መልስ ሰጥተዋል፡፡
የቀድሞው የአሜሪካ አምባሳደር ኮህን ኤርትራ ከኢትዮጵያና ከአሜሪካ ጋር ሊኖራት ስለሚገባው ቀጣይ ግንኙነት የሰጡትን አስተያየት በተመለከተም ጋዜጠኞቹ ጥያቄ አንስተውላቸዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በሰጡት አስተያየትም <<አምባሳደሩ እኔን የኤርትራ እጣ ፈንታ ከኢትዮጵያ ጋር የተሳሰረ ነው ብሎኛል ማለቱ ሀሰት ነው>> ብለዋል ኢሳያስ አፈወርቂ፡፡
<<ይሄ ማለት እኮ ያለ ኢትዮጵያ ኤርትራ የለችም እንደ ማለት ነው፡፡ ይህን እንኳን ልናገረው አስቤው አላውቅም፡፡>> ሲሉ መልሰዋል፡፡
በከበደ ካሳ DireTube

No comments:
Post a Comment