ጥር ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኦሚኒበስ አፕሮፕሬሽን ቢል 2014 በድንጋጌው ለኢትዮጵያ ወታደራዊና ፖሊስ ሃይሎች የሚሰጠው ድጋፍ በቅድመ ሁኔታ ላይ እንዲቀመጥ ወስኗል።
የኢትዮጵያ መንግስት የፍርድ ቤቶችን ነጻነት ካልጠበቀ፣ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ካላከበረ፣ የሰዎችን የመሰብሰብ፣ የመደራጀትና የሃይማኖት ነጻነትን ካላከበረ፣ ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪክ ተቋማት ካለምንም የመንግስት ጣልቃ ገብነት ስራቸውን እንዲሰሩ ካልተደረገ የአሜሪካ ኮንግረስ ድጋፍ አያደርግም ።
እንዲሁም መንግስት በሶማሊያ ክልል የሚካሄደውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ለማየት የሚሹ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና የእርዳታ ድርጅቶች ያለምንም ችግር አካባቢውን እንዲጎበኙ እንዲፈቅድ ፣ ይህን ካለደረገ እርዳታ እንዳይሰጠው ወስኗል። ውሳኔውን የሚከታተለው የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሲሆን፣ መስሪያ ቤቱም እነዚህ ቅደመ ሁኔታዎች ካልተሟሉ ገንዘብ እንደማይለቀቅለት ተገልጿል።
የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ፣ የአሜሪካ መንግስት ለኢትዮጵያ መከላከያና ፖሊስ ለስልጠናና ለመሳሪያ መግዢያ ተብሎ የሚሰጠውን እርዳታ በዝርዝር ለኮንገረሱ ማቅረብ ያለበት ሲሆን፣ እርዳታው በሰብአዊ መብቶች ጥሰት ለተሳተፉ ወታደራዊና የፖሊስ ክፍሎች እንዳይሰጥ ደንግጋጓል።
የኢትዮጵያ መንግስት በዚህ ሂደት የተሳተፉትን የመከላከያ እና ፖሊስ ሃላፊዎች ለፍርድ ካላቀረበም ድጋፍ እንዳይደረግ ብሎአል።
ይሁን እንጅ የእርዳታው ቅድመ ሁኔታ በአለማቀፍ ሰላም ማስከበር ስራ ላይ የተሰማራውን ፣ በጸረ ሽብረተኝነቱ ትግል ላይ የሚሳተፈውን፣ በድንበር ጠበቃ ላይ የሚገኘውንና የመከላከያን አዛዦች ለማሰልጠን የሚሰጠውን ድጋፍ አያካትትም።
በጋምቤላና ታችኛው ኦሞ አካባቢዎች ለሚካሄደው የልማት ስራ የሚውለው ድጋፍ ፣ የዜጎችን መፈናቀል የማያስከትል መሆን አለበት ብሎአል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፋይናንስ ክፍል በኢትዮጵያ ለሚገኙ የእርዳታ ድርጅቶች ቀጥተኛ ትእዛዝ እንዲያስተላለፍ ኮንገረስ ወስኗል።
ውሳኔውን በተመለከተ ኢሳት ያነጋገራቸው የኦክላንድ ተቋም የፖሊሲ ዳይሬክተር የሆኑት ፍሬድሪክ ማውሲዩ ውሳኔው ለአመታት ሲታገሉ በነበሩ ጋዜጠኞች፣ የሰብአዊ መብት ድርጅቶችና ሌሎች ወገኖች የመጣ ነው።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ውሳኔውን መተግበር እና አለመተግበሩን ድርጅታቸውና ሌሎች ድርጅቶች እንደሚከታተሉት ማውሴዩ ገልጸዋል ሙሉ ቃለምልልሱ ከዜናው በሁዋላ ይቀርባል

No comments:
Post a Comment