Thursday, February 13, 2014

Babille Tolla
“ ‘መለስ’ የሚለው ስም በረሃ ከገባ በኋላ የወጣለት ስም ነው። በ 60ዎቹ የጀኔራል ዊንጌት ት/ቤት ተማሪዎች እያለን ‘ለገሰ ዜናዊ’ ብለን ነበር የምንጠራው። ለገሰ ከፊት የመጀመሪያው ረድፍ ነበር የሚቀመጠው። በአመቱ መጨረሻ እንደሚደረገው፣ ከተለያዩ ያገሪቱ ክፍሎች የተወጣጣ የተማሪዎች ቡድን የባህል ትርኢት ያቀርባል። ታድያ በክፍላችን አንድ አበራ አብርሃ የሚባል በጣም ጎበዝ ተማሪ የሆነ የትግራይ ልጅ ነበር። ቁመቱ ዘለግ ያለው አበራ የትግራይ ተወላጆችን ከክፍላችን ለባህሉ ሊያዘጋጅ ፈልጎ፣ እስቲ የትግራይ ተወላጆች እጃችሁን አውጡ” ይላል። ከትግራይ የመጡት እጃቸውን ሲያወጡ፣ ለገሰ ዜናዊ ሳያወጣ ይቀራል።ቆሞ እጅ ያወጡትን ሲቆጥር የነበረው አበራ፣ “አንተ እጅህን አታወጣም እንዴ?” ይላል ለገሰን በአግራሞት ቁልቁል እያየ።
ለገሰም “ለምን አወጣለሁ?” “ከአድዋ አይደለህም እንዴ?” “ከአድዋ መጣሁ እንጂ እኔኮ ኤርትራዊ ነኝ! ብሎ ሲመልስለት ድፍን ክፍል ያውቃል።” ያሉን ዛሬ በአትላንታ፣ ጆርጅያ ኗሪ የሆኑ ለጊዜው ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈልጉ አንዱ ኢትዮጵያዊ ምሁር ናቸው።ትግራይ ተወልደው ያደጉ በርካታ ኤርትራውያን በትግሉ ወቅት ወደ ሻብያ መቀላቀል ቢያምራቸውም፣ ከሻብያ የተሰጣቸው ትእዛዝ ግን “እሳቱን እዛው ባላችሁበት አቀጣጥሉት” የሚል ነበር። በተሰጣቸው ትእዛዝም ለትግራይ ተቆርቋሪ መስለው ህወሓትን በብዛት ተቀላቀሉ (መለስ ዜናዊ ከሌሎች የሻብያ ስልጠና ለመውሰድ ኤርትራ ከገቡት 9 ሰዎች ተለይቶ ለወራት አስመራ መቆየቱ፣ ኋላ ግን ወደ ህወሓት ተመልሶ አረጋዊ በርሀ እግር ስር ወድቆ ‘ማረኝ’ ብሎ መመለሱ ልብ ይሏል)። ቀስ በቀስ እነ መለስም ተደራጅተው ኤርትራን “ከኢትዮጵያ የባእድ አገዛዝ ነፃ ለማውጣት” በጽናት ተንቀሳቀሱ። ዓላማቸውን የሚቃወም ትግራዋይ በተለያዩ ዘዴዎች ያጠፉት ጀመር። የኤርትራ ቅጥረኞች ሰለባ ከሆኑት በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱት
1) ገሰሰ አየለ (ስሑል) 2) መሓሪ ተኽለ (ሙሴ) እና 3) ዶ/ር አታኽልቲ ቀፀላ ናቸው
(አድሃሪ ፊዩዳል፣ ኢዲዩ፣ ኢህአፓ፣ የደርግ ሰላይ፣ ወዘተ እያለ ህወሓት የገደለው የትግራይ ህዝብ ቁጥር በትንሹ ከ 50ሺ እስከ 100ሺ እንደሚደርስ ራሳቸው የወያኔ ታጋዮች ይመሰክራሉ። ያሁኑ ትኩረታችን ግን ‘ወያኔን ለኤርትራ ግንጠላ’ እንዳንጠቀምበት እንቅፋት ይሆኑናል ያልዋቸውን የትግራይ ተወላጆች እንዴት በጠላት እንደጠፉ ለናሙና ያክል እናቀርባለን።) 1. ስለ ገሰሰው አየለ (ስሑል) አገዳደል በ1967 የካቲት ወር ህወሓት ሲመሰረት መሪው ገሰሰው አየለ (ስሑል) የሚባል ነበር። የሽሬ ተወላጁ ስሑል እንኳን ትግራይ ሊያስገነጥል፣ ኤርትራም የኢትዮጵያ አካል ናት ብሎ የሚያምን ፍጹም ደፋር ሰው ነበር። በንጉሱ ጊዜ የፓርላማ አባል የነበረው ስሑል፣ ድፍን የሽሬ ህዝብም እንደይኑ ብሌን ነበር የሚንከባከበው። ይህን ያጠኑ የድርጅቱ አባላትም (እንደ የማነ ጃማይካ የመሳሰሉ በግልጽ በኢሳያስ ትእዛዝ ለስለላ የተላኩ እና እንደነ ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊ፣ ብርሃነ ገ/ክርስቶስ፣ ቴድሮስ ሓጎስ ወዘተ ትውልደ ኤርትራ የሆኑት አደገኛ ቅጥረኞችን ጨምሮ) ድርጅቱ በሁለት እግሩ እስኪቆም ድረስ ጥርሳቸውን ነክሰው ስሑልን መሪ እንዲሆን አደረጉት። በሽሬ ህዝብ ምግብና መጠለያም ተጠቅሞ የወደፊቱ የኢትዮጵያ ደመኛ ጠላት የሆነውን ድርጅት በቀለ። የምንጠራ ጊዜም ደረሰ! የመሳሪያ እርዳታ እንደሚያደርግ አስታውቆ፣ ሻብያም አንድ ቀጭን ትእዛዝ ሰጠ። ስሑል የሚባለው የደርግ ሰላይ እና የኤርትራ ነፃነት ተቃዋሚ ግለሰብን አስወግዱ የሚል። ትእዛዙን ተቀብሎ ለመተግበር የተሰማራው ደግሞ መሰሪው ስብሃት ነጋ ነበር። ስብሓት ስሑልን ለማስመታት ዘመቻውን ተያያዘው፤ የስሁል ስምም ጥላሸት ይቀባ ጀመር። በህቡ እ የተደራጁት ቅጥረኞቹም ዘመቻውን አቀጣጠሉት። ቀኑ ደርሶም “ግምገማ” ጠሩ። “ግምገማ” ከድርጅቱ ለማስወገድ የሚፈልጉትን ሰው ስሑል (ገሰሰ አየለ)“እንኳዕ ካባኹም ተወለድና! እንኳዕ ናይማትና ዘይኮንኩም!” (እንኳን ከናንተ ተወለድን! እንኳን የሌላ ያልሆናችሁ!”) ብሎ ነበር አቶ መለስ ስልጣን በያዘ በአመቱ መቀሌ ተገኝቶ ንግግር ሲያደርግ። ጊዜ አልፎ፣ ማንነቱን ታውቆ፣ ንግግሩ “ደሮን ሲያታሏት የፈላን ውሃ ለገላሽ ነው አሏት” እንዳሉት ቀልደኞች መሆኑ ሲታወቅ፣ ጠርጣራው መለስ በሰላዮች ታጅቦ፣ የሞባይል ስልክ ኔትወርክ አስከርችሞ፣ ሰው ሳይሰማው መቀሌ ገብቶ ይወጣ ነበር። ምን ያረጋል? ስውየው ብዙ ራእይ ነበረው፣ ሞት ቀደመው እንጂ።
የሚጠቀሙባት እስከዛሬ ድረስ የዘለቀች ልዩ የመምቻ መሣሪያ ናት)። በግምገማው ወቅትም የስሑልን ሞራል ካደቀቁ በኋላ፣ከሊቀመንበርነት አውርደው በተራ ታጋይነት እንዲሰለፍ ወሰኑ (ጊዜው ወያኔ በተለይ ከኢዲዩ ሠራዊት ጋር በየቀኑ እጅግ ዘግናኝ የሆነ ጦርነት የሚያደርግበት ስለነበር፣ ስሑልን ወደ ታጋይነት ማውረድ ማለት ሞት መፍረድ ማለት ነው። እንዳቀዱትም ስሑል ተሰዋና አፍቃሪ የኢትዮጵያ አንድነት መሪ ተመነጠረ፣ ስብሃት ነጋም የመሪነቱን ቦታ አጠናከረ፤ የኤርትራ የቅጥረኞች ጡንቻም ፈረጠመ)።
2. ሙሴ (መሓሪ ተኽለ) - (ግድያ ሁለት) ሙሴ ትውልዱ ትግራይ ሆኖ ኤርትራ ተወልዶ ያደገ ነበር። ገና ወያኔ ሳይወለድ በአዲስ አበባ በተማሪዎች ትግል በነበረው ተሳታፊነት በፖሊስ ሲፈለግ ሳይወድ ወደ ሻእቢያ ገብቶ ታዋቂ ተዋጊ እና አዋጊ የነበረ ሰው ነው። ህወሓት ሲመሰረት ግን ወደ ወያኔ ገባ። ሙሴ ከነኢሳያስ ጋር ለአመታት ካሳለፈ በኋላ ወያኔን የተቀላቀለው በመሪነት ነበር። ሙሴ ወያኔ ውስጥ እነማን እንዳሉ ሳያውቅ ወያኔ በምንም መልኩ ከኤርትራውያን ድርጅቶች እርዳታ ሳይጠይቅ ራሱን ችሎ እንዲወጣ ጽኑ ፍላጎት ነበረው። ስለዚህ ወያኔን በሞራል ለማነጽ ይንቀሳቀስ ጀመር። “ሁለቱ የኤርትራ ድርጅቶች ተራ የወንጀለኞች (የማፊያ) ድርጅቶች እንደሆኑ እያብራራ የትግራይ ታጋዮች ራሳቸውን እንዲችሉ ያበረታታ ነበር። “እናንት የትግራይ ልጆች! ሻብያና ጀብሃ ስለማታውቋቸው ነው እንጂ እንኳን ለናንተ እርስበርሳቸውም የማይተማመኑ ተራ ወረበሎች ናቸው። እራሳችሁን ቻሉ! ደግሞ የአክሱም ኦፕሬሽን ትምህርት ሊሆነን ይገባል። የኢትዮጵያ ሰራዊት በሚርመሰመስበት አክሱም አይደለም እንዴ ባንኩን የዘረፍነው?” ይላል ሙሴ። “ደግሞኮ እንደ ሻብያ ደህና መሣሪያ ቢኖረንማ ኑሮ ሌላ ተአምር እንሰራ ነበር።ስለዚህ ሻብያን ከቁም ነገር አታስገቡት!” እያለ የወያኔውን ወኔ ሲቀሰቅስ እነ ስብሃት፣ መለስ ዜናዊ እና በነሱ የተኮላሹት አባይ ፀሀዬ፣ስዩና መስፍን ወዘተ. የሙሴን የሞት ወጥመድ ያዘጋጁ ጀመር። አሁንም ከኢድዮ ጋር በተደረገው ጦርነት ሙሴ እየተዋጋ እያለ በጀርባው ተመታ። ዞር ብሎ ወደ ኋላው ሲያይ ከ“ወገን” በኩል የተተኮሰ ጥይት እንደመታው ህይወቱ እስክታልፍ ድረስ ይናገር ነበር።
3ኛ) ዶ/ር አታኽልቲ ቀፀላ (ግድያ ሦስት) በጎንደር ከተማ ያደገው ስመ-ጥሩ ዶ/ር አታክልቲ ቀፀላ ከሁሉም የወያኔ መሪዎች በትምህርት የላቀ ነበር። ወያኔን ሲቀላቀል አምባገነናዊው “የደርግ ወታደራዊ” አገዛዝን በብረት ተፋልሞ ፍትህና ሰላም ለማስገኘት ነበር እንጂ የኤርትራ የማስገንጠል እግረኛ ወታደር ለመሆን አልነበረም። ለዚህም ነው እነ መለስ ዜናዊ የፖሮፕጋንዳ አስተማሪዎች ሆነው ነጋ ጠባ ስለ ኤርትራ በኢትዮጵያ መገዛትና መረገጥ ሲሰብኩ፣ ዶ/ር አታክልቲ “እናንተ ልጆች እስቲ ቀልዱን አቁሙ! ምንድነው ኤርትራ ኤርትራ የምትሉት? ኤርትራኮ ትናንት አሉላ አባነጋ ሲያስተዳድሯት የነበረች፣ ከጥንት ጀምራ የኢትዮጵያ አካል ሆኖ የቆየች ናት?” እያለ ፈገግታ ባጀበው ፊት ይመክር ነበር። እንደ ሙሴ እና እንደ ስሑል እሱም ያላወቀው ነገር ቢኖር እንደወንድሞቹ የትግራይ ልጆች አርጎ የሚያያቸው ታጋዮች “ወያኔ ትግራይ” በሚል አጨበርባሪ ስም በስተጀርባ ተደብቀው የሚንቀሳቀሱ አደገኛ የኤርትራ ቅጥር ነፍስ-ገዳዮች መሆናቸውን አያውቅም ነበር።
የዶ/ር አታክልቲ ቀጸላ የኤርትራን ጉዳይ ማሳነስ፣ ይልቁንም የኢትዮጵያ ባንዲራ ትክሻው ላይ ጣል እያረገ መታየቱ ለተቀረው ታጋይ ኢትዮጵያዊ ማንነቱን ለማስረገጥ ደጋግሞ መሞከሩ በነመለስና ስብሃት ነጋ ጥርስ ውስጥ እንዲገባ ሆነ። ዶ/ር አታክልቲ ቀፀላ የህክምና ባለሙያ ይሁን እንጂ በወታደራዊ አመራርም በጣም ገኖ የወጣ፣ በታጋዮች ልክ እንደ ሀየሎም አርአያ ተወዳጅነትን ያተረፈ ወታደራዊ ኮማንደር ነበር። ታድያ በሬ ካራጁ ጋር ይውላል ሆነና እሱም የሚታረድበት መንገድ ይፈላልግ ጀመር። እንዲህም ተብሎ በወያኔ ካምፕ ተለፈፈ፤ “የደርግ አልሞ ተኳሽ ሰርጎ-ገቦች በትግራይ በረሀ ተሰማርተዋል። አላማቸውም የወያኔ ኮማንደሮችን መምታት ነው። ስለዚህ ኮማንደሮች ተጠንቀቁ” የሚል ነበር። አንድ ቀን ወያኔ ቀጣዪን ጦርነት ተምቤን ዓብይ ዓዲ ከነበረው የወገን (የኢትዮጵያ) ጦር ጋር ለመፋለም በጥዋቱ ይገሰግሳል። ከፊት ሆኖ የወያኔ ሰራዊትን የሚመራው ስዬ አብርሃ ሲሆን፣ ከመሀል ደግሞ ዶ/ር አታክልቲ ነበር። ከሰራዊቱ መጨረሻ ደግሞ ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ የስለላ፣ የቶርቸርና የግድያ አባት የሆነው ስብሃት ነጋና ሳሞራ የኑስ ነበሩ።አንድ አሳቻ ቦታ ላይ ሲደርሱ አንድ ጥይት ተተኮሰች። ዶ/ር አታክልቲም ጥቅልል ብሎ ተደፋ። የመርዛማ የራሽያ ሲሞኖፍ ጥይት የዶ/ር አታክልቲን ጀርባ ሰንጥቃ ሄደች። የተደናገጠው ሰራዊት ወደፊት እንዲቀጥል ከመቅጽበት ታዘዘ። ህወሓት ያዘጋጀው የቁጩ “አዳኝ ቡድን” ደግሞ የዶ/ር አታክልቲን ገዳይ ለመያዝ በሩጫ ወደ ቁጥቋጦው ተሰወረ።ሁለት ታማኝ ታጋዮች ብቻ ወደ ኋላ ቀርተው ዶ/ር አታክልትን እንዲቀብሩ ታዘዙ። እጅግ ራቅ ብሎ ከኮረብታ የሰራዊቱን እንቅስቃሴ በሬድዮ ሲከታተል የነበረው የጦር አለቃ አረጋዊ በርሄም ዶ/ር አታክልት በደርግ ሰርጎ-ገብ እንደተገደለ ተነገረው።
ዶ/ር አታክልቲ ቀፀላን ቅበሩት ከተባሉት አንዱ (ዶ/ር አባዲ)፣ ድምጹን ቀንሶ እያለቀሰ “አየኸው አይደል! ሳሞራ እኮ ነው የገደለው! ሳሞራ! ወይ ጉዳኛዬ! ወይ አታኽልቲ! ዋይ ወንድሜ! ዋይ ወንድሜ!” ብሎ ያለቅሳል። “ኧረ ቀስ በል!” ይላል ሁለተኛው ታጋይ። “አዎ ሳሞራ ነው! ሳሞራ ተኩሶ ሲገድለው እኔም አይቻለሁ!” ይላል ታጋዩ - ገ/መድህን አርአያ የተባለ!
የድርጅቱ መሪ ይሆናል የተባለው፣ እንደዋርካ ገዝፎ ወቶ የነበረው ኮማንደር አታክልቲ እንዲሁ እንደቀላል ቆርጠው ሲጥሉት ያየና የሰማ ታጋይ ፍርሃት እስከ አጥንቱ ድረስ ሰረፀበት። እኔማ ትንሹ ፍጡር ምን ዋስትና አለኝ? ብሎ ራሱን ጠየቀ። ምንም! ዋስትናው የድርጅቱን መሪዎች እንደ ጣኦት እያመለክ፣ የተሰጠህን ትእዛዝ በፍጹም ታማኝነት መፈፀም ነው። አለበለዚያ፣ ማምለጫ የለም፤ በውስጥም በውጪም የእሳት ረመጥ ሆኗል አገሩ። እንዲህ እያለ በድርጅቱ ፍርሃት ነገሰ። ኤርትራ እስከ ጅቡቲ ድንበር ድረስ የዘለቀ፣ ሁለት ወድብ ያላት የቀይባህር ባለቤት መሆንዋን ደረትን ገልብጦ መናገር የኤርትራ ቅጥረኞች የሚቆጣጠሩት “ወያኔ” በተባለው መንደር የመኖር ዋስትና ሆነ። በድርጅቱ አመራር የነበሩት ከኤርትራ ጋር ምንም የዘር ትስስር ያልነበራቸው የትግራይ ተወላጆችም በፍርሃት ተሸማቀው የኤርትራ ነፃነት ጠበቆች፣ የኢትዮጵያ ጠላቶች ሆነው ዘለቁ! (በቅርቡ ዶ/ር አረጋዊ በርሄ አግኝቼ ስለ ዶ/ር አታክልት አገዳደል የሚያውቀው ነገር ቢኖር ጠይቄው በደርግ “ሰርጎ-ገብ” አንደ ተገደለ ብቻ ነበር ያጫወተኝ። የሳንቲሙ ሌላኛው ገጽታ ለማሳየት ስምክር ግን በተመስጦ ነበር ያየኝ። ይህም ማለት በህቡእ ሲንቀሳቀስ የኖረው የነመለስ/ስብሃት ነጋ ቡድን በአመራር ላይ ለነበሩ እንደነ አረጋዊ የመሳሰሉ ኢትዮጵያውያን ሚስጥሩን እንደማያካፍሏቸው ነበር የተገነዘብኩት። ይህ እውነታ የሚያጠናክሩ ሌሎች ማስረጃዎችም አሉ። እነኚህ እውነታዎች ሌላ ጊዜ እመለስባቸዋለሁ። ስመ-ጥር ኢትዮጵያዊው ገ/መድህን አርአያ ዛሬ የፐርዝ፣ አውስትራሊያ ነዋሪ ነው። ለአገሩ በየጊዜው የሚያደርገው እንቅስቃሴም በፐርዝ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ መሸለሙ ይታወቃል።)
በፀረ-ኢትዮጵያ ቡድን የሚመራው “ወያኔ” በለስ ቀንቶት በ1983 አ.ም. አዲስ አበባ ሲገባ በጠላት የተሰዉብን የድርጅቱ አንጋፋ መሪዎች ብሎ ፎቶ ግራፋቸውን በትልቁ አደባባይ ካወጡት አንዱ የዶ/ር አታክልት ቀፀላን ነበር። የጠላት ጥበብ ይሏል ይህ ነው። ዛሬ እስክንደር ነጋ፣ አንዷለም አራጌ፣ በቀለ ገርባ፣ ኦልባና ሌሊሳ፣ ውብሸት ታዬ፣ ርእዮት አለሙ እና ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹህ ኢትዮጵያውያን በጠራራ ጸሀይ ለበርካታ አመታት ወደ እስር ቤት መወርወር “የጠላት አገዛዝ ውጤት” ከማለት ይልቅ ሌላ ሊባል ፈጽሞ አይቻልም! ዛሬ የወጣቱን ተስፋ ገድሎ፣ ሞራሉን በአደንዛዥ እጽ አድቅቆ፣ ትምህርትን አዳክሞ፣ የኢትዮጵያን ለም መሬት ለባዕዳን እየቸበቸቡ ገብሬውን መሬት አልባ አርጎ ማፈናቀል፣ ህዝቡን በሰው ሰራሽ ረሀብ መቅጣት፣ ከቶ በአገሩ ተስፋ ቆርጦ በገፍ ወደ ውጭ እንዲሰደድ መገፋፋት “ዲክተተርሺፕ” ሳይሆን “የጠላት አገዛዝ” ይባላል።
በትግራይ ህዝብ ስም ኢትዮጵያን አንቆና አዋርዶ እየገዛ ያለው የጠላት ቡድን ያለምንም ጥርጥር በህዝባዊ ሃይል ይወገዳል።በወጣቶች የሚመሩት ሰማያዊ እና አንድነት ፓርቲዎች ሌሎችን በውህደት አቅፈው ለድል ይበቃሉ!
የኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ይመለሳል!

1 comment:

  1. Wednesday, 25 May 2011
    Systematic genocide against Ethnic Amhara, by Kesto

    It was before yesterday , a participant which is called Kesto, spoke about the systematic genocide of the Ethnic Amhara in the present weyane's Ethiopia. He was explaining that there is a project which had been planned by the weyanes to curb the growth rate of the Ethnic Amhara and he further explained that in the so called weyanes' Ethnic Amhara region (Shewa, Gojam , Gonder, wello), there was a vaccination which had been given to women from that region, a vaccine against birth which is birth control (in amharic tsins mamken)

    Kesto, he was talking about the Ethnic Amhara, how they have been deprived in this system. He explained that we need to be a voice for the voice less.

    For me , i am not comfortable to see things with a glass of ethnic tribal lines , i consider ethiopia as one nation, indivisible, intertwined to each other. I wrote and i responded to the guy , by writing that, why we focus on the tribes, TPLF does not care for any body, they care only for their power, do you think these guys care for the Tigryans, of course not , they want the ethnic backed thinking in order to keep us divided, at the end which keeps them in power.

    But we Ethiopians are beyond that. Ethiopians are the smartest nation, no body could divide us, we are far from that.

    At the end of the day, I had decided to look or read further to make my own investigation. It is a broad light truth that this government has shown and has campaigned in destroying Ethnic Amhara. TPLF has been preaching a hate monger campaign against Ethnic Amhara starting from their birth as an organization, taking this in to my account I started to read the two census, 1994, 200.

    Accordingly in the 2007 census the number of Ethnic Amhara were diminishing comparing to the other tribes. It was scary, how could it be? The population growth was 1.7% where as in the others it was more than 2.4%. why only in Ethnic Amhara region? Is there a systematic genocide which had been imposed there? I further tried to read in google and in the channel called you tube. I got some valuable information, a video which had been posted by nitro Ethiopian.

    I watched that video and the video was compiled with interviews between a journalist and weizero samya of weyanes' census official . She was not able why more than 2 .4 million Ethnic Amhara have been withered away. She could not explain that. Any ways she defended that the census was correct. She said that they have tried to investigate in all angels, whether the Ethnic Amhara from rural areas have been immigrated to the cities or other regions, she said still not, but she could not classify the reason, actually it is sad !

    The same official has been answering for questions in the weyane's parliament. She was responding in the same way, an intersting thing the so called, the representatives from that region specially Addisu Legesse has not shown any emotion, only one guy has asked a serious question that he has expressed his doubt.

    In the video, in the election campaign one guy was showing about the child mortality report, which shows that in Ethnic Amhara region, it was the highest one, at the end he has asked that there is something wrong , which lead to the lowest population growth comparing to the other tribes in the other region.

    It is scary, it could be a silent genocide against Ethnic Amhara , Kesto might be correct !!!

    ReplyDelete