Saturday, February 15, 2014

ሕወሃት/ኢሕአዴግ ከዉስጥ ከፍተኛ ጫና እየደረሰበት ነው !


ኢሕአዴግ የዘረጋቸው ትላልቅ ፕሮጅክቶች የሕዝቡ ተሳትፎ እንደሚጠይቁ የተገነዘቡት በርካታ የኢሕአዴግ ደጋፉዎችና አባላት፣ ኢሕአዴግ መሰረታዊ ማሻሻያዎችን እንድያደርግ፣ የፖለቲካ ምህዳሩን እንዲያሰፋ፣ እስረኞችን እንዲፈታ ዉስጥ ዉስጡን ጫና እያደረጉ እንደሆነ ከኢሕአዴግ አካባቢ ያሉ ምንጮቻችን ይገልጻሉ።
biniam_meles















ትግራይን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች በኢሕአደግ ዘንድ ባሉ የመልካም አስተዳደር፣ የኢፍትሃዊነት ችግር ላይ፣ እንዲሁም አልቻል በተባለው የኑሮ ዉድነት የተነሳ፣ የሚነሱ ተቃዉሞዎች እየተበራከቱ መሆኑ ያዩ ኢሕአዴግን የሚደግፉ ወገኖች፣ ኢሕአዴግ የሕዝብን ጥያቄ እንዲያዳምጥ፣ ከሕዝብ ግር እንዲታረቅ ጥሪ እያቀረቡ ናቸው።
«የዛሬዎቹ ኢሕአዴጎች የዚህ የደሃ ሕዝብ እንባና ሮሮ የማያትያቸው ናቸው»
«እዚህ አገር ላይ መልካም አስተዳደር ድራሹኑን ጠፏቷል»
ኢሕአዴጎችን «እነዚህ ክፉ የጫካ ሹሞች ….»
«ሕዝቡ ተማሯል»
«አስተዳደሩ ተበላሽቷል። የአቶ መለስን የቀድሞ አባባል ልዋስና በስብሷል ማለት ይቻላል»
«እዚህ ክፍለ ከተማ ሕዝብ አስለቅሶ በሙሰኝነት ሲነሳ የሰማችሁት ግለሰብ፣ የድርጅት አባል ስለሆነ ተብሎ ወዲያኛው ክፍለ ከተማ ሲሾም ታዩታላችሁ። ይሄ ነገር ምንድን ነው ስትሉ ,አይ ግድ ለየም ሂሱን ወጧል የሚሉት አነጋገር አላቸው»
«የሕዝብ እንደራሴ ተብለው የተመረጡ፣ ፓርላምዉን ያጣበቡ ብዙ ናቸው። መቼ ነው ወደ መረጣቸው ሕዝብ ሄደው ምንድን ነዉ ችግሩህ ያሉት ?፡»
እነዚህ አባባሎች የተናገሩት አቶ ቢኒያም ከበደ ይባላሉ። የኢትዮጵያ ፈርስት ድህረ ገጽ አዘጋጅ ናቸው። እርሳቸው ገለልተኛ መሆናቸውን ቢናገሩም የገዢዉ ፓርቲ ኢሕአዴግ ደጋፊ እንደሆኑ የነገርላቸዋል። በተለይም ሟቹን ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊን በጣም እንደሚወዱና እንደሚያደንቁ በተለያዩ ጊዜ ሲገልጹ ተሰምተዋል።፡
አቶ ቢንያም በአሁኑ ጊዜ መኖሪያቸውን ከአሜሪካን ወደ አዲስ አበባ በማዞር ከዚያዉ ከአገር ቤት አልፊ አልፎ ዘገባዎች ያቀርባሉ።
በቅርቡ በድህረ ገጻቸው ላይ፣ ባልተጠበቀ መልኩ፣ በኢሕአዴግ ላይ ጠንካራ ትችት አሰምቶናል። አቶ ቢንያም ኢሕአዴግ እየበሰብሰ እንደመጣ በመናገር በአገሪቷ መልካም አስተዳደር ፈጽሞ እንደጠፋ፣ ህዝቡ በኢሕአዴግ ካድሬዎች እየተጎላላ እንዳለ ይናገራሉ። የዉሃ እጥረት ከፍተኛ ደረጃ በመድርሱ ጀሪካን እየያዝን ነው የምንወጣው ያሉት አቶ ቢኒያም፣ የመብራት ችግር በጣም አሳዛኝ መሆኑን ሲገለጹ፣ «መብራቱ አሥሬ እየበራና እየጠፋ፣ የምሽት ዳንስ ቤት ነዉ የሚመስለው» በማለት ነበር።
99.9 በመቶ የሚሆኑ በፓርላማ የሚቀመጡ የሕዝብ እንደራሴዎች ላይ ሳይቀር፣ አቶ ቢኒያም ያላቸውን ምሬት ገልጸዋል። « በቴንትድ (በጠቆረ) መስኮት መኪና ዉስጥ ተሸሸገው ፣ ከሕዝቡ የማይገናኙ፣ የተደበቁ፣ የሕዝብኑን ብሶት የማያዳምጡ ናቸው» ሲሉ የፓርላማ ተወካዮች ምን ያህል የማይረቡ መሆናቸውን አቶ ቢኒያም ለማስረዳትም ሞከረዋል።
ኢሕአዴግ የሕዝብ ጥያቄ የማይሰማና ሕዝብን የማያከብር ከሆን፣ ይሄ የመረረዉ ሕዝብ ቅጣቱን እንደሚያወርድ ያስጠነቀቁት አቶ ቢኒያም፣ ኢሕአዴግ አፋጣኝ ለዉጦች እንዲያመጣ፣ ለሕዝብ ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጥና ሕዝብን እንዲያከበር መክረዋል።

No comments:

Post a Comment