ህዝብ ግፍህ በዛብኝ ብሎ በህወሃት ላይ ህዝባዊ አመጽ ሲጀምርና ታጣቂ ልጆቹም ከጎኑ ሲቆሙ፤ ጠላት የተባለው የኢትዮጵያ ህዝብና ህወሃት ያልሆነ ታጣቂ ምን ያስብ ይሆን?
ፈረሰኛ ሲሮጥ እግረኛ ምን ይዟል? ይቺ አባባል የተተረተችው፤ በዱሮ ጊዜ፤ ዱሮ መቼ ነው አትበሉኝና፤ ሰዎች ግማሾቹ በፈረስ ሌሎች በእግራቸው ሲጓዙ ከፊት ከሗላቸው ከባድ ዝናብ ሲመጣ ያዩታል፤ ፈረሰኞቹ ከዝናቡ ለመሸሽ መጋለብ ይጀምራሉ፤ እግረኞቹ ደግሞ አናመልጥም በሚል ተስፋ መቁረጥም ይሆን በስንፍና ቀስ ብለው መጓዝ ይቀጥላሉ፤ በዚህ ጊዜ ነበር አንዱ መካሪ ፈረሰኛ ሲሮጥ እግረኛ ምን ይዟል ብሎ መሮጥ የጀመረው እና ሌሎቹም ተከተሉት፤ ይባላል። ይችን ያነሳሗት ሰሞኑን በትግራይ ክልል የአጽብሂ አካባቢ ህዝብ ህወሃት የሚያደርስበት አስተዳደራዊ በደል አንገፍግፎት ህወሃትና ካድሬዎቹን ዞር በሉ በማለቱ የህወሃት ካድሬዎችና ባለስልጣኖች የአካባቢውን ሚሊሺያ ህዝቡን እንዲደበድብ ያዙታል፤ ሚሊሺያውም ህዝቤን አልደበድብም ከማለቱም ሌላ የህዝብ ብሶት ብሶቴ ነው፤ የህዝቡ ጥያቁ የኔም ጥያቄ ነው፤ እኔ ከህዝብ የተገኘሁ ህዝብ ውስጥ የምኖር እንጂ ባዕድ አካል አደለሁም በሚል መንፈስ ከአጽብሂ ህዝብ ጎን መሰለፉን አብረሃ ደስታ ከሃውዜን ዜናውን አድርሶናል በ አሁኗ ጊዜም ዜናውን እየተከታተለ እያቀረበልን ነው፤ በዚህም አጋጣሚ ለአጽብ ህዝብና ለአጽብሂ ታጣቂዎች ያለኝን አክብሮትና ለአብርሃ ደስታ ምስጋና ማቅረብ አፈልጋለሁ በመሰረቱ ህወሃት ሲመሰረት የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጭ ግንባር ሲሆን ዋና ጠላት አድርጎ የተነሳው ደግሞ አማራንና ኦርቶዶክስ ሃይማኖትን ይበል እንጂ አጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብንና ኢትዮጵያዊነትን እንደነበር ተደጋግሞ ከራሳቸው ከህወሃት መስራች አንደበት የተነገረ ሃቅ ነው።
ታዲያ አንተን ነጻ አወጣሃለሁ የተባለው ህዝብ ግፍህ በዛብኝ ብሎ በህወሃት ላይ ህዝባዊ አመጽ ሲጀምርና ታጣቂ ልጆቹም ከጎኑ ሲቆሙ፤ ጠላት የተባለው የኢትዮጵያ ህዝብና ህወሃት ያልሆነ ታጣቂ ምን ያስብ ይሆን?
If it is true ...... I don't have words
ReplyDelete