Sunday, June 15, 2014

ወጣቶቹና- ቅዳሜ፣ አንዷን ቅዳሜ በፍርድ ቤት


ጽዮን ግርማ

Jailed blog9 bloggers in court

ለአብዛኛው ወጣት አዲስ አበባ ላይ ‹‹ቅዳሜ›› ትርጉም አላት፡፡ የሣምንቱን የሥራ ቀናት በየፈርጁ ያሳለፈው ኹሉም ወጣት ‹‹ቅዳሜ››ን ደግሞ እንደየ ምድቡ ይውልባታል፡፡ እንደሰማኹት ከኾነ ለዞን ዘጠኝ አባላትና ጓደኞቻቸውም ቅዳሜ ልዩ ቀን ናት፡፡ ለወጣቶቹ አብሮነት የጡመራ መድረኩ ቢያግዛቸውም ከዛ በላይ ግን ጓደኝነታቸው ቤተሰባዊነትን ፈጥሮላቸው አብዛኛውን ቅዳሜ እንደየ ቅርበታቸው አብረው ያሳልፋሉ፡፡
አብረው እስረኛ ይጠይቃሉ፣የታመመን ያጽናናሉ፣በጋራ ምሳ ይቋደሳሉ፣የተለየ ዝግጅት ካለም አብረው ይሳተፋሉ፡፡ ከዚህ የተረፈ ጊዜ ካላቸው ደግሞ ፈጣንንና ነጻ የገመድ አልባ ኢንተርኔት አገልግሎት በሚገኝበት ሆቴል ገብተው ዓለም በምን ኹኔታ ላይ እንዳለች ለመከታተል ይሞክራሉ፡፡ አገሪቷ ውስጥ ባለው ከፍተኛ የኢንተርኔት ኮኔክሽን ችግር ምክንያት አብዛኛው ጋዜጠኛና ጥቂት ወጣቶች የእነዚህ ትልልቅ ሆቴሎች ገመድ አልባ ኢንተርኔት ተጠቃሚ ነው፡፡ በቅዳሜ ወደእነዚህ ሆቴሎች ጎራ ያለ ከጦማሪያኑ ወይም ከጋዜጠኛEthiopia bloggers in court አንድ ሰው ሊያገኝ ይችላል፡፡ በቃ ሲገናኙ ሰላም ተባብለው መቀላቀል ነው፡፡እናም በአንድ ጉዳይ ጨዋታ ጀመራል፡፡ አብዛኛው ጨዋታ በአገር ጉዳይ ላይ ያተኮረ ሊኾን ይችላል፡፡ ኮምፒዩተሮቻቸውን እየነካኩ ስለ አገራቸው ግድ ያላቸውን ይነጋገራሉ፣ይከራከራሉ አሊያም ይጨቃጨቃሉ፡፡መሄጃው ሰዓት የደረሰበት ደግሞ ተሰናብቶ ይሄዳል፡፡በእነዚህ ሆቴሎች በቀጠሮ የሚገናኝ ሰው የለም፡፡‹‹የት ነህ? የት ነሽ?›› የሚለው የስልክ ጥያቄም ለመገናኘት በቂ ነው፡፡
የተስፋዓለም ቅዳሜ ደግሞ ሌላ ነበረች፡፡ሥራ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ አብዛኛውን አርቦች ከእነ ለሊታቸው በሥራ ያጠፋቸዋል፡፡ቅዳሜንም ረፈድ አድርጎ ይነሳል፡፡ እናም የመጀመሪያ ሥራው ለሕትመት የበቁ ጋዜጣና መጽሔቶችን አበጥሮ ማንበብ ነው፡፡ በማንበብ ብቻም አያቆምም፤ ከዘገባዎቹ አብዛኖቹ የተሠሩት በጓደኞቹ አሊያም በሚያውቃቸው ጋዜጠኞች ስለሚኾን ስልክ ይደውላል፡፡ ከዘገባዎች ውስጥ ተስፋዓለምን የሚያስደስቱት በጣም ጥቂቶቹ ብቻ ሊኾኑ ስለሚችሉ የስልክ ልውውጦቹ ‹‹እንዲህ ብታደርግ/ብታደርጊ ኖሮ፣እንትናን ብታናግረው በዚህ ጉዳይ ላይ መረጃ ይሰጥህ ነበር፣እዚህ ቦታ እኮ እንዲህ ዓይነት መረጃ ነበር፣ይሄ እኮ ከዚህ በፊት እንዲህ ያለ ሕትመት ላይ ወጥቷል፣እውነቱን ለመናገር ይሄ ለሕትመት የሚበቃ ዘገባ ነው ብዬ አላምንም›› በሚሉ አስተያየቶች የተሞሉ ነበሩ፡፡ በዚያው ልክ ደግሞ የሚያስደስተውን ዘገባ ሲያነብ ወይም ፕሮግራም ሲሰማ አዘጋጁን አወቀው አላወቀው ስልክ አፈላልጎ በመደወል ያበረታታል፡፡ የተስፋዓለም ግማሽ ቅዳሜ የምታልቀው ይህን ሲያደርግ ነው፡፡
አኹን እነዚህ ወጣቶች ቅዳሜያቸውን በፌደራል ወንጀል ምርመራ መምሪያ (ማዕከላዊ) ፖሊስ ተነጥቀዋል፡፡ ሃምሳ ቀናት ታስረው ዘጠኝ ቅዳሜን አጥተዋል፡፡ እንዳሻቸው የሚያደርጓትን ቅዳሜ አኹን እነርሱ አያዙባትም፡፡ ከጠዋቱ ዐስራ ሁለት ሰዓት ሲል ከእንቅልፋቸው ይቀሰቀሳሉ፡፡ ለቁርስ ዳቦ በሻይ ይሰጣቸዋል፡፡ (ቤተሰብ የሚያወስድላቸው ምግብ ቁርስ ከበሉ በኋላ ነው የሚደርሳቸው) እናም ተመልሰው ገብተው ይዘጋባቸዋል፡፡አብዛኞቹ ለየብቻ ከሌሎች እስረኛ ጋር የታሰሩ ሲኾን ሁለት፣ ሁለት ተደርገው የታሰሩም አሉ፡፡እናም ከምርመራ የተረፈ ቀናቸውን በዝጉና በጨለምተኛው ክፍል ያሳልፋሉ፡፡ በአንዷ ቅዳሜ ደግሞ እንደዛሬው ፍርድ ቤት ይቀርባሉ፡፡
አንዷን ቅዳሜ- በፍርድ ቤት
ሦስቱ ወጣቶቹ እነርሱ በማያዙባት ቅዳሜ እጆቻቸውን በካቴና ታስረው ፒያሳ በሚገኘው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ግቢ ውስጥ ሲደርሱ ከሌላው ጊዜ የበለጠ ቁጥር ያለው በዐይን ግምት ሦስት መቶ የሚደርስ ችሎት ተከታታይ በግቢ ውስጥ ተገኝቶ ነበር፡፡ የዛሬዎቹ ጠባቂ የፌደራል ፖሊሶች ባለፈው ጊዜ ከነበሩት ሻል ያሉ ስለነበሩ ቤተሰቦች ችሎት ውስጥ ገብተው እንዲታደሙ ባይፈቀድላቸውም ግቢ ውስጥ ከመቆም የከለከላቸው ወይም ያመናጨቃቸው አልነበረም፡፡ bloggers in court Addis Ababa, Ethiopia
ከጠዋቱ አራት ሰዓት ከሃያ ደቂቃ አካባቢ ሲኾን ችሎቱ በሴት ዳኛ በመሰየሙ፤ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ፣የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎቹ ናትናኤል ፈለቀና አጥናፉ ብርሃነ እጃቸውን በሰንሰለት እንደታሰሩ ወደ ግቢው ገቡ፡፡ ዛሬ ወጣቶቹ በስስ ፈገግታ ‹‹አይዞአችሁ ደህና ነን›› የሚል የተስፋ ምልክት ለቤሰተቦቻቸውና ለጓደኞቻቸው አሳይተዋል፡፡ ከእነርሱ ቀጥለው በፖሊስ ታጅበው የገቡት ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ፣ጋዜጠኛ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስና የሕግ መምሕርና የዞን ዘጠኝ ጦማሪ ዘለዓለም ክብረት እጆቻቸው በካቴና እንደታሰረ ለቤተሰቦቻው ሰላምታን ሰጥተዋል፡፡ የእነርሱ ፈገግተኛ መኾን ለቤተሰቦቻቸው፣ለጓደኞቻቸውና ለወዳጆቻቸው ጥቂትም ቢኾን እፎይታን ሰጥቷል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ችሎት የቀረቡት እንደወትሮው ኹሉ በሁለት መዝገብ ተከፍለው ቢኾንም ፖሊስ ያቀረበው ምክንያትና መከራከሪያ አንድ ዓይነት ነበር፡፡ ችሎቱ ከተሰየመ በኋላ ፖሊስ በተሰጠው ጊዜ ቀጠሮ በርካታ ጉዳዮችን ሲመረምር መቆየቱንና አሁንም ያልተጠናቀቀ ምርመራ ስለሚቀረው ተጨማሪ ሃያ ስምንት ቀናት እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡
ጠበቃው አቶ አመሐ፤‹‹ፖሊስ ከዚህ ቀደም በወሰደው ጊዜ ቀጠሮ ሰንድ ለማስተርጎም፣ የምስክሮችን ቃል ለመቀበል፣ኢሜሎቻቸውን ለመፈተሽ እንዲሁም ያልተያዙEthiopian Jailed bloggers ግብረአበሮቻቸውን ለመያዝ ብሎ እንደነበርና አሁን ዝም ብሎ በጥቅሉ በርካታ ሥራዎችን ሠርቼያለሁ እንደገና ይጨመርልኝ ማለቱ አግባብ አይደለም›› ሲሉ አመልክተው ነበር፡፡ ዳኛው ፖሊስ የሠራውን ሥራና የሚቀረውን ምርምራ እንዲያስረዳ በማዘዛቸው፣‹‹ከሠራናቸው በርካታ የምርመራ ሥራዎች መካከል የተባባሪዎቻቸውን ቤት ፈትሸናል፣ለተለያዩ ባንኮች የተጠርጣሪዎቹን ዝርዝር መረጃ እንዲሰጡን ጠይቀን ከተወሰኑት ምላሽ አግኝተናል፣የተወሱ ምስክሮችንን ቃል ተቀብለናል፣ ከትርጉም ሥራውም የተወሰነውን ሠርተናል፡፡ ግብረአበሮቻቸው ወደ ክፍለ ሃገርና ወደ ተለያዩ አገራት እየሸሹ መያዝ ስለተቸገርን የፖሊስ ኃይል አሰማርተን እያፈለግናቸው ነው እነርሱንም መያዝ ይቀረናል፡፡›› በማለት ተናግሯል፡፡
አቶ አመሐ በበኩላቸው፤‹‹ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ካዋለ ሃምሳ ቀናት ሞልቶታል፡፡ እነዚህ የሚላቸውን ነገሮች አጠናቆ ለመጨረስ የነበረው ጊዜ ከበቂ በላይ ነው፡፡አሁንም ቢኾን እነዚህን ምርመራዎች ለማድረግ የደንበኞቼን አስሮ ማስቀመጥ አስፈላጊ አይደለም ስለዚህም ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብቻውን ሊያከብርላቸው ይገባል፡፡ ይህን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ባይቀበለው እንኳን ከዚህ በኋላ ፖሊስ በሚሰጠው ሃያ ስምንት ቀናት ጊዜ ውስጥ ምርመራውን አጠናቆ እንዲመጣ፤አጠናቆ ባይመጣ ደግሞ ጥያቄው ተቀባይነት እንደማይኖረው ተደርጎ ይመዝገብልን›› በማለት ጠይቀዋል፡፡
ዳኛዋ አቤቱታውን ካደመጡ በኋላ፤ፖሊስ ከዚህ በኋላ ሲቀርብ ለተጨማሪ የምርመራ ቀነ ቀጠሮ መጠየቂያ አሁን የጠቀሳቸውን ምክንያቶች በምክንያትነት ይዞ እንዳይቀርብ በማሳሰብ የጠየቀውን የሃያ ስምንት ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ፈቅደዋል፡፡zone9 bloggers in court
በዛሬው ዕለት ችሎት ከቀረቡት መካከል ጋዜጠኛ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ ፤ከፍተኛ የኾነ የጀርባ ሕመም ስላለበት ወንበር እንዲገባለት መጠየቁንና እስካኹን ሊገባለት እንዳልቻለ ጠቅሶ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ እንዲሰጥለት አመልክቷል፡፡ ዳኛዋ ከምንም ነገር በላይ የጤና ጉዳይ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ በማሳሰብ የጠየቀው ወንበር እንዲገባለት ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በችሎት የተገኘው መርማሪ ፖሊስ፤‹‹በአጋጣሚ የእርሱ መርማሪ እኔ ነኝ የጀርባ ሕመም እንዳለበት ነግሮኛል፡፡ ወንበር እንዲገባለት ግን አልጠየቀኝም፡፡ አሁን ቢኾን ይህ በጣም ቀላልና እዛው እኛው ጋር ሊያልቅ የሚችል ነገር ነው፡፡ ችግር የለም እናስገባለታለን›› ሲሉ ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡
እስረኞቹ ከችሎት ሲወጡ እንደ አገባባቸው በፈገግታ ሰላምታ እየሰጡ ሲኾን ችሎቱን ለመከታተል መጥቶ ፍርድ ቤቱ ግቢ ውስጥ ቆመው ሰውም እጁን በማውለብለብ ተሰናብቷቸዋል፡፡ (ፎቶ አዲስ ስታንዳርድ)

No comments:

Post a Comment