Wednesday, June 4, 2014

ከሱዳን ካርቱም የደረሰኝ መረጃ]በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያኖች ዘግናኝ ግፍ እየተፈጸመባቸው ነው

በሱዳን በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጸመው ግፍ ቀጥሏል:: በየጊዜው ለስራ ፍለካ ምክንያትና በኢትዮጵያ ባለው የፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት ሀገራቸውን እየለቀቁ ወደ ሱዳን የሚገቡ ኢትዮጵያኖችን ብዙ ሲሆን እነዚህ ኢትዮጵያኖች ወደ ሱዳን ከገቡ በኋላ ለተለያዩ ችግሮች እየተዳረጉ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል :: በተለይም በሱዳን በሚኖሩ ኢትዮጵያን ዜጎቻችን ላይ ከመቼውም ጊዜ በተለየ ሁኔታ ኢሰብዓዊ ድብደባ እየተፈጸመባቸውና በሀገሪቱ ፖሊስ እና በሱዳን ማህበረሰብ ዘግናኝ ግፍና በደል እየደረሰባቸው እንዳለ ለማወቅ ተችሏል :: በዛው በሱዳን ካርቱም ነዋሪ ከሆነ ግለሰበ እንዳገኘውት ምንጭ ከሆን በኢትዮጵያኖች ላይ ፖሊስ የተለያያ ድብደባና ጥቃት የሚያደርስባቸው ሲሆን በሀገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች ሴቶች በእነዚህ ፖሊሶች እና በወጣት ሱዳን ወንዶች በግሩፕ በየቦታው እየተደፈሩ ሲሆን በፖሊሶችና በሱዳን ወጣት ወንዶች ወሲባዊ ጥቃት እየደረሰባቸው ያሉ አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ሴቶች የስነ ልቦና ቀውስ ውስጥ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል::
እነዚህ በሱዳን የሚኖሩኢትዮጵያውያኖች የድረሱን ጥሪ አያቀረቡ ሲሆን ነገር ግን ማንም ሊደርስላቸው እንዳልቻለና በሱዳን ካርቱም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ችግሩን ለመፍታት ምንም አይነት ጥረት እያደረገላቸው አይደለም:: ኢምባሲው ወገኖቻችን ችግር ሲደርስባቸው ፈጥኖ ደርሶ የዜጓቹን ችግር ከመፍታት ይልቅ በሱዳን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ የማፍያዎች ስብስብ ሆኖል ስለ ዜጋ የሚቆረቆርና ሀላፊነት የሚሰማው አንድም ሰው የለም ካርቱም ኢትዮጵያ ኢምባሲ ሰራተኛ የሆኑ ለሕዝብ የሚያገለግሉና ሀላፊነት የሚሰማቸው ሰዎች እንዳይደሉ ::ነገር ግን እዛ ቁጭ ብለው ምንም ስራ እንደማይሰሩ በኢትዮጵያ ኢምባሲ ስም ብቻ በሙስና ሀብት ማካበት ብቻ እንደሆነ የደረሱኝ መረጃዎቹ ይጠቁማሉ ::
በነዚህ ሁለት ወራት ውስጥ በጣም አሳዛኝ ነገር ከመቼውም ጊዜ በተለየ ለየት ያለ ኢትዮጵያዊያንን የማጥቃት ዘመቻ በካርቱም ተጦጥፎ ይገኛል:: ካርቱም ያሉ አራቱም ወህኒ ቤቶች ኩበር፣ሶባ፣ኦምዱራምሃ፣ሀል ሁዳ የተባሉ እስር ቤቱች በእስረኛ ተጨናንቀዋል በተለየ ኢትዮጵያኖች ከአስር እስከ ሃያ አመት ፍርደኛ ናቸው:: አንዲትም ቀን የኢትዮጵያ ኢምባሲ ሂዶ ጠይቋቸውም አያውቅም በአሁኑ ሰአት ደግሞ ህገ ወጥ ስደተኛ ተብለው ከሶስት መቶ በላይ ኢትዮጵያዊ ስደተኞች በሆዳ እስር ቤት ይገኛሉ እንደዚሁ ህገ ወጥ ስደተኛ ተብለው ሆዳ እስር ቤት የታጎሩ ሰዎች ባለፈው 21/5/2014 ሶስት ኢትዮጵያውያን ሞተዋል:: ምክንያቱም ለሰባት ቀን ያህል በር ተዘግቶባቸው ያለ ምግብና ውሃ በመቆየታቸው ሰውነታቸው ተዳክሞ ሲሆን ሌሎች 30 ሰዎች በወህኒ ቤቱ ግቢ ህክምና ተደርጎላቸው አስራ ሁለቱ ከተወሰነ ሰአት በኋላ ሲመለሱ አስራ ስምንቱ በአንድ የፖሊስ ሆስፒታል በዝግ አይሱዚ መኪና ተወስደዋል:: በወቅቱ ጉዳዩን መቀመጫው ካርቱም ኢትዮጵያ ኢምባሲ አማባሳደር አቶ አብዲ ዘሙ ተደውሎ ተነግሯቸው የነበረ ሲሆን እሳቸው ግን ችግሩን ችላ በማለት ጅብ ከሄድ ውሻ ጮኸ እንደሚባለው በነጋታው ሰው በማስላክ አይተዋቸዋል ::ከዛ እንደለመደው በመዋሸት ምንም የሞተ ሰው የለም በማለት አወራ::ምክንያቱም ጉዳዩን ካርቱም ያለ አብዛኛው አበሻ ስለሰማ ለመሸፋፈን ቢሆንም ነገር ግን ሆስፒታል የነበሩ የተቀሩት ሐበሾች ወዲያውኑ ከተመለሱ ጉዱ ስለሚገለጥ ፍርዳቸውን ሳይጨርሱ የት እንደሚወስዶቸው አልታወቀም ፈተው ወደ ሀገር ቤት እባረዋቸው ይሆን ወይም እነሱም የሶሰት ወንድሞቻቸው እጣ ፈንታ ደርሶቸው ይሆን ምንም የታወቀ ነገር የለም::
ሌላው በጣም የሚገርመው ነገር በዛው ካርቱም ኢትዮጵያ ኢምባሲ ባሉት አረመኔዎች እህቶቻችን ወሲባዊ ጥቃት ይፈጸምባቸዋል::አቶ መሀመድ ቱፋ የሚባል የኢምባሲው ሰራተኛ የሆነ ከኢትዮጵያ ጫት እያስመጣ የሚነግድ አደገኛ የጫት ነገዴ እንደሆ ነው የሚነገርለት::ሌላው ደግሞ ሌባ የኢምባሲው ሰራተኛ አቶ በላቸው ገብረ መስቀል ይባላል ከአሁን በፊት የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ በካርቱም ብር ዘርፎ ሀገር ቤት ሄዶ ነበር ተመልሰው አምጥተውት ከፍ ያለ ስልጣን ተሰቶት ካርቱም በኢትዮጵያ ኢምባሲ እየሰራ ነው:: ካርቱም ኢትዮጵያ ኢምባሲ ባጠቃላይ የህገ ወጡች ስብስብ ሆኖል::

 ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ ሌና

No comments:

Post a Comment