Sunday, June 22, 2014

በሺህ የሚቆጠሩ አማሮች ከምዕራብ ወለጋ ተፈናቀሉ


በሺህ የሚቆጠሩ አማሮች አማራ በመሆናቸው ብቻ ተመርጠው ከምዕራብ ወለጋ ከጊምቢ እና ቄሌም (እንፍሌ ወረዳ አሽ ቀበሌ) ተፈናቀሉ

ጉዳያችን ሰኔ 12/2006 ዓም (ጁን 20/2014)

በብዙ ሺህ የሚቆጠር የአማራ ህዝብ ኢትዮጵያውያን ከምዕራብ ወለጋ ጊምቢ እና ቄሌም በኃይል አካባቢውን እንዲለቁ ከመደረጉ በላይ ድብደባ እና Amhara-People-in-Benshangul-Kilil1ግድያ እንደተፈፀመባቸው ቪኦኤ የአማርኛው አገልግሎት ሰኔ 12/2006 ዓም ምሽት ባስተላለፈው ዘገባ ገለፀ።

ዘገባው የተፈናቃዮችን ምስክርነት እንዳስደመጠው ድብደባው እና ግድያው በከተማው ሕዝብ እና ፖሊስ የታገዘ መሆኑን እና ህይወታቸውን ያተረፉት በኮርኒስ እና ጫካ በመደበቅ መሆኑን ሲገልጡ፣አንድ ምስክርነታቸውን ለቪኦኤ የሰጡ ተፈናቃይ አክለው እንደገለፁት ከጊምቢ ከተማ ብቻ ከሶስት ሺህ በላይ የአማራ ህዝብ ኢትዮጵያውያን መፈናቀላቸውን ተናግረዋል።ሌላው ምስክርነት ሰጪ ደግሞ ቁጥሩን ከስምንት ሺህ ሕዝብ በላይ አድርሶታል።

አምስት ልጆች የነበራቸው መሆናቸውን የተናገሩት ሌላ ተፈናቃይ የነበራቸው መደብር መዘረፉን እና ካለምንም ሀብት መቅረታቸውን፣ጉዳዩን አቤት ለማለት ወደ ባለስልጣናት ቢሄዱም ሰሚ ማጣታቸውን አስታውቀዋል።

የቪኦኤ ጋዜጠኛ ጉዳዩን አስመልክቶ ቀደም ብሎ የአካባቢው የፀጥታ ጉዳይ ኃላፊ የተባሉ እሳቸው ግን የኦሕዴድ ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ነኝ ያሉ አቶ አወቀ የተባሉ የክልሉ ባለሥልጣን ስለጉዳዩ ሲናገሩ ”ያባረረ የለም’ ሲሉ ተደምጠዋል።

የኦሮምያ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳይ ኃላፊ ወ/ሮ ራቢያ ኢሳ ”ሰዎቹ የሄዱት ፈርተው ነው” ካሉ በኃላ ”ቁጥራቸው ”መቶ አይሞሉም ” ማለታቸው ግርምትን ፈጥሯል።የቪኦኤ ጋዜጠኛ አቶ ሰለሞን በመቀጠል ” ቁጥሩ አይደለም ወሳኙ አንድም ሰው ቢሆን ለምን ተፈናቀለ? ደግሞስ ምን ያስፈራቸዋል? ያብራሩልኝ ” ብሎ ለጠየቃቸው ወ/ሮ ራቢያ አጥጋቢ መልስ ለመስጠት ሳይችሉ ቀርተዋል።

የኢህአዲግ/ወያኔ የጎሳ ፖለቲካ ሕዝቡን በአካል መለብለብ ከጀመረ ሰነበተ።ሺዎች የእዚህኛው ሌሎች የእዚያኛው ብሄር ተወላጅ ናችሁ እየተባሉ ተፈናቅለዋል።በተለይ ከአማራው ህዝብ ተወላጅ የሆኑ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከጉርዳፈርዳ፣ከበንሻጉል፣ከኢልባቦር እና ከወለጋ አሰቃቂ ግድያ እና ድብደባ እየተፈፀመባቸው ለዘመናት ያፈሩትን ንብረት እየተነጠቁ መባረራቸውን ያመለከቱ ዘገባዎች ሲወጡ የነበረ መሆኑ ይታወቃል።

No comments:

Post a Comment