Monday, December 29, 2014

ከጀርመን ለውህደቱ የተወከሉት የአርበኞች ግንባር አመራር አቶ ካሳዬ መርሻ አስመራ እንዳይገቡ በሻእቢያ ታገዱ:

የኢሳያስ አፍወሪቂ ጋዜጣዊ መግለጫ እና ወያኔ ከውጪ የሚኖሩ ተቃዋሚዎች ጋር የድርድር ጥያቄ እንዲያዣንብብ እየሰራ መሆኑ ታውቋል:: ተወካዩን አስመራ ለማስገባት ዲፕሎማሲያዊ ጥረቱ ቀጥሏል::
ከአውሮፓ ወደ ኤርትራ ለውህደቱ ስብሰባ እንዲሄድ የተወከለው በጀርመን የሚኖረው አቶ ካሳዬ መርሻ ወደ አስመራ እንዳይገባ በሻእቢያ መከልከሉ ሲታወቅ ከፊል ኤርትራዊ እንደሆነ የሚታወቀው እና ከአውስትራሊያ የተወከለው የወልቃይት ተወላጅ አቶ አለልኝ ከሻእቢያ ፈቃድ ማግኘቱ ታውቋል:: ነዋሪነት በጀርመን የሆነው እና ለአርበኞች ግንባር ትግል ታላቅ አስታውጾ እንዳበረከተ የሚነገርለት አቶ ካሳዬ መርሻ በግንባሩ አባላት አስፈላጊዉን ወጪ ተሸፍኖለት ለጉዞ ሲንደረደር በሻእቢያ መከልከሉ በውጪ የሚኖሩ የግንባሩ አባላትን ያሳሰበ ቢሆንም ሁኔታውን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑ ታውቋል::
በዚህ ምክንያት በውጪ የሚኖሩ የአርበኞች ግንባር አባላት እና ደጋፊዎች የተወከለው አቶ ካሳዬ እንዳይመጣ በሻእቢያ መከልከሉን በተመለከተ ያላቸውን ተቃውሞ በደብዳቤ መላካቸው ሲታወቅ በአስመራ የሚገኙ የግንባሩ አመራሮች ሁኔታውን እንዲፈቱ በደብዳቤያቸው ያሳውቁት አባላቱ በአግባቡ የተወከለው ሰው በውህደቱ ጉባዬ ላይ እንዲገኝ ሲሉ አቋማቸውን ገልጸዋል::የወከሉት ሰው በመከልከሉ በውህደቱ ላይ ያላቸውን ጥርጣሬም አስምረውበታል::በቂ ሃይል እና ተንካራ መዋቅር እንዳለው የሚነገርለት አርበኞች ግንባት አባላቱ በኢትዮጵያ ለሚመጣው ለውጥ ተግተው እንደሚሰሩ እና ማንም እንደማያስቆማቸው ተናግረዋል::
አንድ አስተያየት ሰጪ እንደተናገሩት በሃገር ቤት ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሃገራዊ አቋም እንዳይኖራቸው ሕወሓት/ኢሕ አዴግ በሰርጎ ገብነት እየገባ እንደሚያፋልሳቸው ሁሉ በውጪ የሚኖሩ ድርጅቶችንም እንዲሁ ሻእቢያ በውስጥ ጉዳያቸው እየገባ እሱ በሚፈልገው መልኩ እንዲሽከረከሩ ያደርጋል ሲሉ ተደምጠዋል::
ከጀርመን የተወከሉት አቶ ካሳዬ ወደ አስመራ እንዳይገቡ ካልተፈለገበት አንዱ ምክንያት ከዚህ ቀደም በግንባሩ ላይ በሻእቢያ የሚፈጸሙ ግፎችን ለማስቀረት ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ ሲሆን የግንባሩ አባላት እና ታጋዮች ይህንን በደንብ ስለሚያውቁ በውህደቱ ላይ እንዲገኝላቸው ፍላጎቱ ቢኖራቸውም ሻእቢያ ግን አንድ ጊዜ ጥርስ ስለነከሰበት እንዳይመጣበት ከልክሏል::እንዲሁም በውጪ የሚኖሩ አባላት ውህደቱ ላይ ችግር ካለ እንዲወገድ ወደፊትም ችግሮች እንዳይፈጠሩ አመራሩን ለማስተካከል እና አማራጮችን መጠቀም በሚል ስልት አቶ ካሳዬ የራሱን የፖለቲካ ልምድ ተጠቅሞ ሊያስተካክል ይችላል እንዲሁም ያሉትን ችግሮች እንዲስተካከሉ በፊትለፊት ይናገራል የሚሉ ፍራቻዎች በሻእቢያ ስላሉ የተወከሉት አባል ወደ አስመራ እንዳይገቡ ከልክለዋል::
አቶ ካሳዬ ወደ አስመራ ሁለት ጊዜ ካሁን ቀደም ሂዶ ካለምንም ፍርሃት ለሻእቢያ ግንባሩን በተመለከተ ያለውን ችግር እና ወደፊት መሆን የለበትን ጉዳይ ካለፍርሃት አፍረጥርጦ ስለተናገረ እንዲሁም አቶ ካሳዬ የአርማጮ ተወላጅ በመሆኑ በአከባቢው ያለውን እና በግንባሩ ታጋዮች ዙሪያ ያለውን ጉዳይ አንስቶ ካለፍርሃት ለሻእቢያ መናገሩ ለአሁኑ መከልከል ምክንያት ቢሆንም ጉዳዩን ለመፍታት አስመራ እና አውሮፓ ያሉ የግንባሩ አመራሮች እየጥሩ መሆኑን ምንጮች ከአስመራ ተናግረዋል:
******************************************************************************
የወያኔ አየር ሃይል ባልደረቦች ይዘውት የገቡትን ሄሊኮፕተር ተከትሎ አቶ ኢሳያስ አፍወርቂ የአዲስ አመትን ጋዜጣዊ መግለጫ አስታከው ይናገራሉ ተብሎ በመጠበቅ ላይ ሲሆን የወያኔ ቃል አቀባዮች ሌመንግስት ታማኝ ለሆነ ጋዜጣ ሄሪኮፕተሩ ለማስመለስ ጥረት አለመደረጉን መግለጻቸው ቢታወቅም የሕወሓት ጦር ጄኔራሎች ግን ካልተመለሰ ምሳችንን አስመራ እንበላለን ሲሉ መደንፋታቸው የወያኔ ባለስልጣናቱን አለመናበብ አመልክቷል::
ይህ በእንዲህ እንዳለ ወያኔ በውጪ ከሚኖሩ የተቃዋሚ ሃይሎች ጋር ለመደራደር ማንዣበቡን ፍንጮች ጠቁመዋል:: ወያኔ በስልጣን የመቆየት እድሉ እንደተመናመነ በማወቁ ድርድር የማድረግ ፍላጎት ማሳየቱ እና በታሪክ ልንከስም ነው ያሉት ባለስልጣንን ተከትሎ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ገዢው ፓርቲ የገባበትን አጣብቂኝ ሊወጣው ባለመቻሉ ውንደለመደው በማዘናጋት ጊዜ መግዣ መፈለጉን ያሳያል ሲሉ ተናግረዋል:

No comments:

Post a Comment