Thursday, August 7, 2014

የአቶ በረከት የዛሬ ውሎ፤ ባለስልጣኑ ለደህነታቸው ጥበቃ ከሆስፒታል መልስ የጅዳን ቆንስላ ጽ/ቤት ዛሬ ጎበኙ


  • 2390
     
    Share
Bereket Simon weeping with his wife over Meles Zenawi's death
Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ
አቶ በረከት ስሞኦን ከሆስፒታል ቀጠሮአቸው መልስ ዛሬ የጃዳ ቆንስላ ጽ/ቤትን ለመጀመሪያ ግዜ መጎብኘታቸው ታውቋል ። አቶ በረከት እግር መንገዳቸውን ለዲፕሎማቱ ስለጤንነታቸው ሁኔታ ገለጻ እንዳደረጉ ከቆንስላው ጽ/ቤት የወጡ ምስጢራው መረጃዎቻችን ያመለክታሉ:: አቶ በረከት ስሞን በሼክ መሃመድ አላሙዲን የግል አውሮፕላን በሚስጠር ሳውዲ አረቢያ ለህክምና ከገቡ ወዲህ ለደህነታቸው ሲባል ሃገርቤት ካሉ የመንግስት ከፍተኛ ባለ ስልጣናተም ሆነ እዚህ ሳውዲ አረቢያ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት እምነት ጥሎባቸው ሃገር እና ህዝብን ወክለው ከተቀመጡ ዲፕሎማቶች በስልከም ሆነ በአካል ሳይገናኙ በድብቅ የልብ ህክምና ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወሳል ።
እኚሕ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ሳኡዲ አረብያ ጅዳ ለህክምና መግባታቸውን ተቃዋሚ ከሚሏቸው ከሶሻል ሚዲያዎች ያረጋገጡት የቆንስላው ዲፕሎማቶች አቶ በረከት ስሞኦን በፈጸሙት ስህተት ሲበሳጩ መስተዋላቸውን ምንጮቹ አክለው ገልጸዋል። የአቶ በረከት ስሞን ለህክምና ወደ ሳውዲ አረቢያ ጅዳ መግባትን ተከትሎ በሶሻል ሚድያ በመናፈሱ ባለስልጣኑ ህክማናቸውን በአግባቡ መከታተል እንዳልቻሉ በወቅቱ መዘገቡ ይታወሳል።
ከዛሬው የሆስፒታል ቀጠሮ መልስ በኋላ ጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት ጎራ ያሉት አቶ በረከት ለቆንስላው እና ለዲፕሎማቱ እውቅና ክበር ከመስጠት ሳይሆን ባለስልጣኑ ከሆስፒታል ከወጡ ወዲህ የተለያዩ ሆቴሎችን በመከራየት በድብቅ ሲያስታምሞቸው እና ድጋፍ ሲያደርጉላቸው የከረሙት ሼክ አላሙዲን ከሁለት ቀን በፊት ለስራ ጉዳይ ወደ አሜሪካ መብረራቸውን ተከትሎ የጤንነታቸው ሁኔታ እንብዛም አስተማማኝ ያልሆነው እኚሕ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ወደ ሃገር እስኪመለሱ ለደህነታቸው ጥበቃ እንዲያደርግላቸው የዘየዱት መላምት መሆኑ ከቆንስላው ጽ/ቤት የወጡ መረጃዎች ያስረዳሉ።
ባለስልጣኑ አርፈውበታል የተባለው ሆቴል ማማሻውን በማቅናት መረጃ ለማሰባሰብ ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም ።

No comments:

Post a Comment