Thursday, August 28, 2014

የሰማሁት ለጆሮ ይዘገንናል (እየሩሳሌም አርአያ)



እየሩሳሌም አርአያ

እየሩሳሌም አርአያ
ከአንድ ሰው ጋር ለረጅም ሰአት አወራን። ይህ ኤርትራዊ (ያደገው ኢትዮጵያ ነው) ከነወ/ስላሴ፣ መላኩ ፈንታ፣ ገ/ዋህድ ..ሌሎች ጋር “ኔትዎርክ” እያለ የሚጠራው የዘረፋ ቡድን አባል ነበር። የዘረፋው ዋነኛ መሪዎች፣ የኋላ ደጀኖችና የጥቅም ተካፋዮች ከሆኑት አዜብ መስፍንና በረከት ስሞኦን ይጠቀሳሉ። ለ15 አመት እንዴት አገሪቷን እንደተቀራመቷት ሲናገር መስማት ይዘገንናል። የሚገርመው መለስ ዜናዊ በሚገባ ይህን የዘረፋ ኔትዎርክ አሳምረው ማወቃቸው ነው። ከአንድ ባለስልጣን በቀር ሁሉም እስከአንገቱ በሙስና ተጨማልቋል፣ በሃብት ደልቧል ይላል። በቀድሞ የኮሜኒኬሽን ሚ/ር የተፃፈውን መፅሐፍ በተመለከተ ሲናገር « ስለዘረፋ ሩብ ያክል አልተፃፈም። እንዳውም አልፃፈም ማለት እችላለሁ። መጠነ ሰፊና ተከታታይ መፅሐፍ ሊወጣው የሚችል ዘረፋ (ሙስና) ተፈፅሟል፤ ገ/ዋህድ ቤት የተገኘው የሚሊዮኖች ኖት ሁሉም ባለስልጣን ዘንድ መጠባበቂያ ተብሎ የሚቀመጥ በመሆኑ አይገርምም። ዋናው ገንዘብ እኮ አልተነካም! የሁሉም ባለስልጣን ገንዘብ አገር ውስጥ የለም..» ይላል።
ይህ ኔትዎርክ እንዲበጣጠስ የተደረገው በበረከት ስሞኦን ሲሆን ይህን በማድረግ ስልጣናቸውን ታድገዋል ሲል ያክላል። ..አሜሪካ ሸሽቶ የመጣው ይህ ሰው ለረጅም ሰዓታት ያወጋኝን በጥቂት ገፆች ፅፌ የምጨርሰው አይደለም። ከዚህ ይልቅ በኢሳት ወጥቶ ቢናገር ሁሉም ወገን የዝችን አገር መሪዎች ጉድ ሊያውቅ ይችላል ብዬ አስብኩ። አንዳንድ የሚጨርሳቸው ጉዳዮች ስላሉ እነሱን ካስተካከለ በኋላ በሚዲያ እንዲወጣ ለማድረግ ይሞከራል። .

No comments:

Post a Comment