Thursday, August 7, 2014

ዜና ልማት፤ የአዲሳባ መስተዳድር፤ ”ለዜጎች የስራ እድል እየፈጠርኩ ነው” አለ። (ወጣቶች አንድ ሰው በሶስት ብር ጎርፍ ሲያሻግሩ ዋሉ)

ዜና ልማት፤ የአዲሳባ መስተዳድር፤ ”ለዜጎች የስራ እድል እየፈጠርኩ ነው” አለ። (ወጣቶች አንድ ሰው በሶስት ብር ጎርፍ ሲያሻግሩ ዋሉ) ትላንት በአዲሳባ የሚገኙ ወጣቶች አንድ ሰው በሶስት ብር ሂሳብ እያንከበከቡ በመሸከም መንግስት በፈጠረላቸው አስፋልታዊ ጎርፍ ላይ ሲያሻግሩ ዋሉ። ወጣቶቹ፤ ”መንግስታችን አስፋልት እንጂ የውሃ መተላለፊያ ያልሠራው አቅቶት ሳይሆን ለእኛ አስቦ በመሆኑ ምን ያህል ስራ ፈጣሪዎችን የሚያበረታታ መሆኑን የሚያሳይ ነው” ሲሉ ለመንግስታቸው ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል። ”መንግስት ለቀጣይ ክረምቶችም የውሃ ፍሳሻቸው ያልተዘጉ መንገዶችን ቱቧቸውን በመዝጋት የእኛን እንጀራ እንደሚከፍትልን ተስፋ እናደርጋለን” ሲሉም በስራ ፈጠራው ተጠቃሚ የሆኑ ወጣቶች ገልጸውልናል። የአዲሳባ አስተዳደር በበኩሉ፤ ዛሬ በአስፋልት ላይ የታየውን ጎርፍ በአምስት አመቱ የትራንስፎርሜሽን እቅድ በየቤቱ ለማስገባት እንደሚጥር ይሄም በርካታ ዜጎችን ለስራ ፈጠራ እንደሚያነሳሳ ገልጿል። እያልን እየቀለድን የትላንትናውን የአዲሳባ ቦሌ መንገድ ውሎ የምታስቃኝ ቪዲዮ እንካችሁ በታደሰ አለሙ አራዳ ሙዚቃ ታጅባለች።

No comments:

Post a Comment