Monday, August 18, 2014

የዩኒቨርስቲተማሪዎችየሚያነሱዋቸው ጥያቄዎች ለኢህአዴግ ፈታኝ እንደሆኑበት ተሰብሳቢዎች ገለጹ Aug18,2014


ነሃሴ ፲፪(አስራ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የትምህርትሚኒስቴርከ360 ሺህበላይነባርናአዳዲስየዩኒቨርሲቲተማሪዎችየመንግሥትንፖሊሲናስትራቴጂን
እንዲሰለጥኑአስገዳጅመመሪያማውጣቱን ተከትሎ በጎንደር ዩኒቨርስቲ የተሰበሰቡ ከ1500 በላይ ተማሪዎች ያነሱዋቸው ጥያያቄዎች ለኢህአዴግ ካድሬዎች ፈታኝ እንደሆኑባቸው ውይይቱን የሚከታተሉት ወኪሎቻችን ገልጸዋል። በከፍተኛ መሰላቸትና ጫጫታ የሚካሄደው ስብሰባ ዋና አላማ ተማሪውን ስለመጪው ምርጫማዘጋጀትና አዳዲስ አባላትን መመልመል ነው። ባለፈው አርብ በተደረገው የመጀመሪያ ቀን ስብሰባ ተማሪዎች ከመብት ፣ ከዲሞክራሲና ከኢኮኖሚ ጋር የተያያዙጥያቄዎችን አንስተዋል። 

እውን በአገራችን የብሄር እኩልነት አለ ወይ ሲሉ የጠየቁት ተማሪዎች፣ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች በሚገኙ ከፍተኛ የስልጣን ቦታዎች የአንድብሄር የበላይነት ጎልቶ እንደሚታይ፣ ብሄሮች እኩል ናቸው ብሎ መናገር እንደማይቻልና በተለይ የአማራ ብሄር እንወክለዋለን ብለው በተቀመጡ ባለስልጣኖች ሳይቀር እየተሰደበ መሆኑን ገልጸዋል። በአገሪቱ ዲሞክራሲ የሚባል ነገር እንደሌለ የተናገሩት ተማሪዎች፣ የሃይማኖት እኩልነት አለ መባሉንም በጥርጣሬተመልክተውታል። 
ኢህአዴግ ስለ ደርግ ደጋግሞ ቢያወራም፣ የእስካሁን የሰራው ከደርግ የማይሻልና ኢህአዴግና ደርግ የተለያዩ ናቸው ብሎ ለመውሰድ እንደማይቻልተማሪዎች ገልጸዋል። 
በኢኮኖሚው ረገድ የተለየ ነገር አለመምጣቱን የገለጹት ተማሪዎች፣ የተጀመሩ መንገዶች አይጠናቀቁም፣ ስኳር ጠፍቷል፣ መንግስት ኢኮኖሚው አድጓል ቢልም በቅርቡ የወጡ መረጃዎች ኢትዮጵያን ከአለም የመጨረሻዋ ደሃ አገር እንዳደረጋትና አብዛኛው ግንባታዎች የሚካሄዱት ከቻይና በተገኘ ብድር መሆኑን ተናግረዋል። የቀድሞ መንግስታት በራሳቸው ወጪ ግንባታዎችን ያካሂዱ ነበር ያሉት ተማሪዎች፣ በኢህአዴግ የምንሰማው ግን ቻይና ብድር ፈቀደች፣ ቻይና ብድር ሰረዘች
የሚል መሆኑን ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያን ታሪክ ከእናንተ በተሻለ እናውቀዋለን በማለት ተማሪዎች በታሪክ ላይ ተመስርቶ የሚሰጣቸውን ተንተና እንደማይቀበሉት ገልጸዋል። 

በሱዳን እና በኢትዮጵያ መካከል ስላለው ድንበር እና ኢትዮጵያ ለሱዳን ስለሰጠችው መሬትም ጥያቄ ተነስቷል። ዩኒቨርስቲዎችን የፖለቲካ ማራመጃ መደረጋቸውን የተቃወሙት ተማሪዎች፣ በእረፍት ሰአታቸው ላይ ተማሪዎችን ያስፈለገበት አላማ እንዲገለጽላቸውም ጠይቀዋል። አንዳንድ ተማሪዎች ግን ምርጫ ሲደርስ ነው የምታስታወሱን
በማለት የስብሰባው አላማ ከምርጫ ጋር የተያያዘ መሆኑን ጠቅሰዋል። ተማሪዎች አሰልቺ ነው ባሉት ስብሰባ፣ የገዢው ፓርቲ ተወካዮች ለተነሱት ጥያቄዎች በቂ መልስ ለመስጠት ባለመቻላቸው ተማሪዎችን ይበልጥ ማበሳጨቱን ወኪሎቻችን ገልጸዋል። በሥልጠናውላይተሳትፎየምስክርወረቀትያልያዘተማሪ በዩኒቨርሲቲዎቹትምህርቱንመቀጠል እንደማይችልሉ ተነግሮአቸዋል። የትምህርትሚኒስትሩአቶሺፈራውሽጉጤሰሞኑንለጋዜጠኞችእንደገለጹትበመንግሥትፖሊሲዎችናስትራቴጂዎችላይ ከ250ሺህ
በላይነባርየዩኒቨርሲቲተማሪዎችእናከ116 ሺህበላይአዳዲስተማሪዎችለተከታታይ 15 ቀናት አበል በመክፈልባሉበት አካባቢበፕላዝማሥልጠናእንደሚሰጥቃል የገቡ ቢሆንም፣ ከገጠር አካባቢ ለመጡት መጠነኛ አበል ከመስጠት በስተቀር ሌሎች ተማሪዎች አላገኙም። በዚህም በተማሪዎችና በባለስልጣኖች መካከል ጭቅጭቅ ተፈጥሮ እንደነበር
ለማወቅ ተችሎአል።
ሥልጠናውንየሚሰጡትከፍተኛየመንግሥትባለስልጣናትመሆናቸውንየሥልጠናውዝርዝርእናየሚፈጀውወጪምንያህል እንደሆነእስካሁን ግልጽ አይደለም።ይህሥልጠና ኢህአዴግበመንግሥትወጪለቀጣዩምርጫድጋፍለማግኘትእንዲሁም ነባር አባላቱን በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለመተካት ለዘረጋው መርሃ ግብር ማስፈጸሚያ ነው ኢሳት ያነጋገራቸው ተማሪዎች እንደሚሉት ኢህአዴግን የስልጠናውን አላማ ግልጽ አላደረገም። ስብሰባውን ለመሰታፍ በተማሪዎች በኩል ያለው ስሜትም ቀዝቃዛ ከመሆኑ በተጨማሪ በርካታ ተማሪዎች ስብሰባውን ጀምረው ጥለው ይወጣሉ።
የቀድሞው ም/ል ጠ/ሚኒስትር አዲሱ ለገሰ በቅርቡ ባወጡት ጽሁፍ ኢህአዴግ አሁን ያለውን አመራር ይዞ ረጅም እርቀት እንደማይጓዝና ነባር አመራሩን በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለመተካት መንቀሳቀስ እንደሚገባ አመላክተው ነበር።

No comments:

Post a Comment