Sunday, March 16, 2014

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ይዞታና የዩናይትድ ስቴትሱ ዓመታዊ ሪፖርት


የሰውን ፣ ሰብአዊ መብት ለማክበር ፣ በኤኮኖሚ፤ በልማት መደርጀት ቅድመ ግዴታ አይሆንም። የትምህርት መሥፋፋት፣ እርግጥ እገዛ ሊያደርግ ይችላል። ሙሉ ወሳኝነት አለው ተብሎ ግን አይታሰብም።
Äthiopien Omo Fluss Tal Landschaft Staudamm Gibe III
ሰውን የተሟላ ሰው የሚያደርገው በተፈጥሮ ያገኘው ሰብአዊ መብቱ ነጻነቱና ሰብአዊ ክብሩ ሳይሸራረፍ ተከብሮ ሲገኝ ነው። ይህ መሠረታዊ መብት በተባበሩት መንግሥታት አዋጅ የተጠቀሰና በብዙ ዴሞክራሲን በሚከተሉ፣ የህግን የበላይነት በሚያከብሩ አገሮች እንደሚሠራበት የታወቀ ነው።
የሰብአዊ መብት ጥያቄ፣ የአንድ ሀገር ዜጎች በደል ሲደርስባቸው ፣ በሀገራቸውና በዓለም አቀፍ ሕግጋት ተመርኩዘው አቤት የሚሉበት ጉዳይ ቢሆንም፣እንደ ችግሩ ስፋት መጠን፤ መሠረታዊ ሰብአዊ መብትን ፣የሰብአዊ መብት ተቋማትን፣ አላከበረም በሚባል በማንኛውም ሀገር መንግሥትም ሆነ የተለያዩ አክራሪ ቡድኖች ላይ ወቀሳ ወይም ውግዘት ማቅረብ፣ አንዳንዴም ማዕቀብ እስከመጣልና ማግለልንም የመሳሰለ እርምጃ በታዛቢ የተባበሩት መንግሥታት አባል ሃገራት በኩል እስከመውሰድ ይደረሳል።በቅርቡ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ባወጣው የ 2013 ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት፤ የሰብአዊ መብት ዘገባ፣ በዓለም ዙሪያ የተለያዩ ሃገራት ፈጸሟቸው ያላቸውን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በዝርዝር አውጥቷል። ከተጠቀሱት ሃገራት አንዷ ኢትዮጵያ ናት። ከዚህ ከአሜሪካው የሰብአዊ መብት ይዞታ ዘገባ በመነሣት ፤ ለውይይት 3 እንግዶች ጋብዘናል።

ተክሌ የኋላ
አዜብ ታደሰ

No comments:

Post a Comment