Friday, March 14, 2014

ይሁን, የሚሆነው ሁላ ፤ ቀን እስክትመጣ፤ ፅዋ እስክትሞላ ...



By Afework Z Blue
______የሚሆነው ሁሉ ይሁን!!!________
እኛን ሲውጠን መከራ
አዎ እናንተማ ዝለሉ፤ ከበሮ ምቱ ዳንኪራ፡፡
ቁረጡ ጮማ እና ጎድን፤ ተራጩ ውስኪ እና ቢራ፡፡
እሰይ እናንተ ዝፈኑ፤ ድምፃችሁ ያምራል ቆንጆ ነው፡፡
እዬዬ ዋይታው ለእኛ ነው፡፡
ሳቁ ቦርቁ ፈንድቁ
ከአበባና ከጨረቃ፤ ከኮከብ በላይ ድመቁ፡፡
እሬሳችን ላይ ደንሱ፤ አጥንታችንን አድቅቁ፡፡
እናንተ ብሉ ጥገቡ፤ ተራጩ ውስኪና ቢራ፡፡
እኛ በረሃብ እንሙት፤ ስቃይ እንግልት እናውራ፡፡
የእናንተ ህይወት ይታደስ፤
የእኛ እምባ ግዴለም ይፍሰስ፡፡
የእናንተ ኑሮ ጣፈጠ፤
እኛ አለም ግን ኮመጠጠ፡፡
እናንተ ወርቆች አልማዞች፤
እኛ ገለባ እንክርዳዶች፡፡
ይህ ሁሉ ይሁን እንዳሻው!!!
ይሁን የሚሆን በሞላ!!!
ያቺ ቀን እስክትመጣ፤ ያቺ ፅዋ እስክትሞላ፡፡ 

No comments:

Post a Comment