Tuesday, December 30, 2014

የመሰናዶ ተማሪዎች የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠና ላይ ተቃውሙ አሰሙ



• በሶስት ከተሞች ረብሻዎች ተነስተዋል
(ነገረ-ኢትዮጵያ) በምስራቅ ጎጃም ዞን ሁሉም ትምህርት ቤቶች የ11ኛ እና የ12ኛ ክፍል መሰናዶ ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቁመው እንዲወስዱ የተደረገውን የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠና ላይ ተቃውሞ ማሰማታቸውን ምንጮን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
በስልጠናው ወቅት የህዝቡ አስተሳሰብ፣ የግል ሚዲያ፣ ተቃዋሚዎች ለኢትዮጵያ እድገት ጠንቅ ተደርገው የቀረቡ ሲሆን ተማሪዎች ይህንን አቀራረብ ተቃውመውታል፡፡ በአንጻሩ ከወራት በፊት ስልጠናውን የወሰዱት መምህራንም ዳግመኛ ስልጠናውን እየወሰዱ ቢሆንም ዝምታን መምረጣቸው ተገልጾአል፡፡
ተማሪዎቹ ‹‹የምርጫ ቅስቀሳ ከሆነ ለተቃዋሚዎችም ይፈቀድ፣ ለምን ለግጭት የሚጋብዙ ቅስቀሳ ትቀሰቅሳላችሁ፣ የኢህአዴግ ፖሊሲ ምሁራንንም ጭምር ለስደት የዳረገ ነው፣ ከቻይና እና ከኮሪያ የሚያስተሳስረን የታሪክም ሆነ የባህል መሰረት የለንም፣ ኢህአዴግ 23 አመት ያልተገበረውን ዴሞክራሲ ሊያስተምረን አይችልም›› የሚሉ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን አንስተዋል፡፡
በስልጠናው ወቅት ተቃውሞዎች እየተነሱ ሲሆን በተለይም ደብረማርቆስ፣ ባሶ ሊበንና ሞጣ ላይ ተማሪዎቹ ‹‹ኢህአዴግ ሌላ፣ ኢህአዴግ ሌባ›› የሚል ጩኸት በማሰማታቸው ሲሰለጥኑበት ከነበረው ሰፊ አዳራሽ 20፣ 20 ሆነው በየክፍሉ እንዲሰለጥኑ ተደርገዋል፡፡ በተለይ በደብረማርቆስ ከተማ በሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቹ የካድሬ ስልጠና አንሰለጥንም በማለት መረር ያለ ተቃውሞ እያሰሙ እንደሚገኙ ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡

ኢትዮጵያ ለወሲብ ንግድና ለህገወጥ የሰዎች ዝውውር መነሻ አገር ሆናለች ሲል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታወቀ


የአሜሪካ የስቴት ዲፓርትመንት ባወጣው የ2014 ሪፖርት ኢትዮጵያ ለግዳጅ ሥራ፣ ለወሲብ ንግድና ለሕገወጥ የሰዎች ዝውውር የተዳረጉ ወንዶች፣ ሴቶች እና ሕፃናት መነሻ፤ በተወሰነ ደረጃም መዳረሻ አገር ናት ብሎአል።
sex_worker_europeአዲስ አበባ የሚገኘው ዋና የገበያ ማዕከል ከአፍሪካ ቀዳሚው የወሲብ ንግድ ቤቶች መገኛ ነው የሚለው ሪፖርቱ፣ ዕድሜያቸው እስከ 8 ዓመት የሚሆኑ ልጃገረዶች በነዚህ ቤቶች በሴተኛ አዳሪነት ተሰማርተዋል ይላል።
ኢትዮጵያውያን ወጣት ሴቶች ከኢትዮጵያ ውጪም በተለይ በጂቡቲ፣ደቡብ ሱዳን እና በመካከለኛው ምስራቅ አገራት ውስጥ በቤት ሠራተኝነት እና በሴተኛ አዳሪነት እንዲሰሩ እንደሚገደዱ፣ ኢትዮጵያውያን ወጣት ወንዶች ደግሞ ጂቡቲ ውስጥ በሱቅ ሰራተኝነት፣ በተላላኪነት፣ በቤት ሰራተኝነት፣ በስርቆት እና በጎዳና ላይ ልመና ለግዳጅ ሥራ ተዳርገዋል ብሎአል።
በርካታ ወጣቶች ሥራ ፍለጋ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሲሰደዱ ጂቡቲ፣ ግብጽ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን ወይም የመንን እንደመሸጋገሪያ ይጠቀማሉ የሚለው ሪፖርቱ፣አንዳንዶቹ ሊሄዱ ካሰቡበት አገር ሳይደርሱ እንደመሸጋገሪያነት ባረፉበት አገር ተይዘው ለብዝበዛ፣ለእስራት፣ለግዳጅ ስራ እና ለመታገት ይዳረጋሉ ብሎአል።
በመካከለኛው ምሥራቅ አገራት በቤት ሰራተኝነት የተሰማሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን ሴቶች አካላዊ እና ወሲባዊ ጥቃት፣ ደሞዝ ክልከላ፣ እንቅልፍ መነፈግ፣ የፓስፖርት መያዝ፣ በቤት ውስጥ መታገት እና ግድያን ጨምሮ አስከፊ ጥቃቶች እንደሚደርስባቸው፣ በአንዳንድ አጋጣሚዎች ኢትዮጵያውያን ሴቶች ስራ ፍለጋ ከአገር ከወጡ በኋላ፣ በወሲብ ንግድ ቤቶች፣ በማዕድን ማውጫ ቦታዎች፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ውስጥ በሚገኙ ነዳጅ ዘይት ማውጫ አካባቢዎች ለወሲብ ንግድ ብዝበዛ ይዳረጋሉ ብሎአል።
የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በቀን እስከ 1500 የሚደርሱ ኢትዮጵያውን በሕጋዊ መንገድ ከአገር እንደሚወጡ ቢገልጽም፣ ይህ ቁጥር ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ከሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከ30 እስከ 40 በመቶ ብቻ የሚወክል ብሎአል። ከ60 እስከ 70 በመቶ የሚሆኑት ሠራተኞች በሕገ ወጥ ደላሎች አማካኝነት ለህገወጥ የሰዎች ዝውውር ወይንም ስደት እንደሚዳረጉ ጠቅሷል።
መንግስት በአስቀጣሪ ኤጀንሲዎች ላይ ክልከላ ቢጥልም ክልከላውን ተከትሎ በሱዳን በኩል የሚደረግ ሕገወጥ የሰራተኞች ፍልሰት መጨመሩን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሪፖርት ጠቁሟል። እ.ኤ.አ. ከሕዳር 2013 ጀምሮ የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት ከ163 ሺ 000 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንን ከአገሩ ያስወጣ ሲሆን ከነዚህም መካከል ከ94 ሺ 000 የሚበልጡት በኮንስትራክሽን ዘርፍ ውስጥ የተሰማሩ ወንዶች፤ ከ8 ሺ 000 የሚልቁት ደግሞ በእረኝነት እና በቤት ሰራተኝነት የተቀጠሩ ሕጻናት ናቸው ብሎአል።
መንግሥት ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለማስወገድ የተቀመጡትን ዝቅተኛ መስፈርቶችን ሙሉ በሙሉ ባያሟላም፣ ችግሩን ለመቅረፍ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል የሚለው ሪፖርቱ፣ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 106 ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር የፈጸሙ ወንጀለኞች ሕግ ፊት ቀርበው እንዲቀጡ ያደረገ ሲሆን፤ከዓለምአቀፍ አጋሮች ጋር በመተባበርም ለሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባዎች መጠለያ እና የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ አድርጓል ሲል አትቷል።
መንግስት የሕገወጥ ዝውውር ሰለባ የሆኑትን ጨምሮ ከሳዑዲ ዓረቢያ እና ከሌሎችም አገራት የተባረሩ ዜጎች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ የማመቻቸት ስራ ቢሰራም፣ የገንዘብም ሆነ የቁሳቁስ ድጋፍ ሳያደርግ የውጭ አገር ድርጅቶች ይወጡት በማለት ሃላፊነቱን ለእነሱ መተውን ገልጿል።
መንግስት ውጭ አገር በሚገኙ ዲፕሎማቲክ ሚሽኖች የሰራተኛ ጉዳዮችን የሚመለከቱ አታሼዎችን አለመመደቡ፤በኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽ/ቤቶች በሚሰጡ የዜጎች ደህንነት አገልግሎቶች ላይም ማሻሻያ አለማድረጉም ተጠቅሷል፡፡
መንግስት የሕጻናት የወሲብ ንግድን እና ሌሎች በአገር ውስጥ የሚፈጸሙ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀሎችን በሕግ ማስከበር፣ ከለላ በመስጠት እና በመከላከል በኩል በቂ ሥራ አልተሰራም በሚል ስቴት ዲፓርመንት ትችት አቅርቧል።
Source:: Ethsat

Monday, December 29, 2014

ከጀርመን ለውህደቱ የተወከሉት የአርበኞች ግንባር አመራር አቶ ካሳዬ መርሻ አስመራ እንዳይገቡ በሻእቢያ ታገዱ:

የኢሳያስ አፍወሪቂ ጋዜጣዊ መግለጫ እና ወያኔ ከውጪ የሚኖሩ ተቃዋሚዎች ጋር የድርድር ጥያቄ እንዲያዣንብብ እየሰራ መሆኑ ታውቋል:: ተወካዩን አስመራ ለማስገባት ዲፕሎማሲያዊ ጥረቱ ቀጥሏል::
ከአውሮፓ ወደ ኤርትራ ለውህደቱ ስብሰባ እንዲሄድ የተወከለው በጀርመን የሚኖረው አቶ ካሳዬ መርሻ ወደ አስመራ እንዳይገባ በሻእቢያ መከልከሉ ሲታወቅ ከፊል ኤርትራዊ እንደሆነ የሚታወቀው እና ከአውስትራሊያ የተወከለው የወልቃይት ተወላጅ አቶ አለልኝ ከሻእቢያ ፈቃድ ማግኘቱ ታውቋል:: ነዋሪነት በጀርመን የሆነው እና ለአርበኞች ግንባር ትግል ታላቅ አስታውጾ እንዳበረከተ የሚነገርለት አቶ ካሳዬ መርሻ በግንባሩ አባላት አስፈላጊዉን ወጪ ተሸፍኖለት ለጉዞ ሲንደረደር በሻእቢያ መከልከሉ በውጪ የሚኖሩ የግንባሩ አባላትን ያሳሰበ ቢሆንም ሁኔታውን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑ ታውቋል::
በዚህ ምክንያት በውጪ የሚኖሩ የአርበኞች ግንባር አባላት እና ደጋፊዎች የተወከለው አቶ ካሳዬ እንዳይመጣ በሻእቢያ መከልከሉን በተመለከተ ያላቸውን ተቃውሞ በደብዳቤ መላካቸው ሲታወቅ በአስመራ የሚገኙ የግንባሩ አመራሮች ሁኔታውን እንዲፈቱ በደብዳቤያቸው ያሳውቁት አባላቱ በአግባቡ የተወከለው ሰው በውህደቱ ጉባዬ ላይ እንዲገኝ ሲሉ አቋማቸውን ገልጸዋል::የወከሉት ሰው በመከልከሉ በውህደቱ ላይ ያላቸውን ጥርጣሬም አስምረውበታል::በቂ ሃይል እና ተንካራ መዋቅር እንዳለው የሚነገርለት አርበኞች ግንባት አባላቱ በኢትዮጵያ ለሚመጣው ለውጥ ተግተው እንደሚሰሩ እና ማንም እንደማያስቆማቸው ተናግረዋል::
አንድ አስተያየት ሰጪ እንደተናገሩት በሃገር ቤት ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሃገራዊ አቋም እንዳይኖራቸው ሕወሓት/ኢሕ አዴግ በሰርጎ ገብነት እየገባ እንደሚያፋልሳቸው ሁሉ በውጪ የሚኖሩ ድርጅቶችንም እንዲሁ ሻእቢያ በውስጥ ጉዳያቸው እየገባ እሱ በሚፈልገው መልኩ እንዲሽከረከሩ ያደርጋል ሲሉ ተደምጠዋል::
ከጀርመን የተወከሉት አቶ ካሳዬ ወደ አስመራ እንዳይገቡ ካልተፈለገበት አንዱ ምክንያት ከዚህ ቀደም በግንባሩ ላይ በሻእቢያ የሚፈጸሙ ግፎችን ለማስቀረት ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ ሲሆን የግንባሩ አባላት እና ታጋዮች ይህንን በደንብ ስለሚያውቁ በውህደቱ ላይ እንዲገኝላቸው ፍላጎቱ ቢኖራቸውም ሻእቢያ ግን አንድ ጊዜ ጥርስ ስለነከሰበት እንዳይመጣበት ከልክሏል::እንዲሁም በውጪ የሚኖሩ አባላት ውህደቱ ላይ ችግር ካለ እንዲወገድ ወደፊትም ችግሮች እንዳይፈጠሩ አመራሩን ለማስተካከል እና አማራጮችን መጠቀም በሚል ስልት አቶ ካሳዬ የራሱን የፖለቲካ ልምድ ተጠቅሞ ሊያስተካክል ይችላል እንዲሁም ያሉትን ችግሮች እንዲስተካከሉ በፊትለፊት ይናገራል የሚሉ ፍራቻዎች በሻእቢያ ስላሉ የተወከሉት አባል ወደ አስመራ እንዳይገቡ ከልክለዋል::
አቶ ካሳዬ ወደ አስመራ ሁለት ጊዜ ካሁን ቀደም ሂዶ ካለምንም ፍርሃት ለሻእቢያ ግንባሩን በተመለከተ ያለውን ችግር እና ወደፊት መሆን የለበትን ጉዳይ ካለፍርሃት አፍረጥርጦ ስለተናገረ እንዲሁም አቶ ካሳዬ የአርማጮ ተወላጅ በመሆኑ በአከባቢው ያለውን እና በግንባሩ ታጋዮች ዙሪያ ያለውን ጉዳይ አንስቶ ካለፍርሃት ለሻእቢያ መናገሩ ለአሁኑ መከልከል ምክንያት ቢሆንም ጉዳዩን ለመፍታት አስመራ እና አውሮፓ ያሉ የግንባሩ አመራሮች እየጥሩ መሆኑን ምንጮች ከአስመራ ተናግረዋል:
******************************************************************************
የወያኔ አየር ሃይል ባልደረቦች ይዘውት የገቡትን ሄሊኮፕተር ተከትሎ አቶ ኢሳያስ አፍወርቂ የአዲስ አመትን ጋዜጣዊ መግለጫ አስታከው ይናገራሉ ተብሎ በመጠበቅ ላይ ሲሆን የወያኔ ቃል አቀባዮች ሌመንግስት ታማኝ ለሆነ ጋዜጣ ሄሪኮፕተሩ ለማስመለስ ጥረት አለመደረጉን መግለጻቸው ቢታወቅም የሕወሓት ጦር ጄኔራሎች ግን ካልተመለሰ ምሳችንን አስመራ እንበላለን ሲሉ መደንፋታቸው የወያኔ ባለስልጣናቱን አለመናበብ አመልክቷል::
ይህ በእንዲህ እንዳለ ወያኔ በውጪ ከሚኖሩ የተቃዋሚ ሃይሎች ጋር ለመደራደር ማንዣበቡን ፍንጮች ጠቁመዋል:: ወያኔ በስልጣን የመቆየት እድሉ እንደተመናመነ በማወቁ ድርድር የማድረግ ፍላጎት ማሳየቱ እና በታሪክ ልንከስም ነው ያሉት ባለስልጣንን ተከትሎ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ገዢው ፓርቲ የገባበትን አጣብቂኝ ሊወጣው ባለመቻሉ ውንደለመደው በማዘናጋት ጊዜ መግዣ መፈለጉን ያሳያል ሲሉ ተናግረዋል:

Thursday, December 18, 2014

መድረክ የሰላማዊ ሰልፉን አካሄደ

ከ ጎልጉል 

medrek8

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) እሁድ ዕለት ያቀደውን ሰላማዊ ሠልፍ በ37 መፈክሮች በማጀብ አካሂዶዋል፡፡
medrek3አብዛኛዎቹ መፈክሮች ምርጫን፣ ምርጫ ቦርድን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሁኔታን፣ የአገሪቱን የኢኮኖሚ ሁኔታ፣ የኑሮ ውድነት፣ የመሠረታዊ አገልግሎቶች መቆራረጥና መንግሥትን ከሃይማኖት ጣልቃ ገብነት እንዲወጣ የሚጠይቁ ነበር፡፡
ከመፈክሮቹ መካከልም “ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት በነፃና ፍትሐዊ ምርጫ እንጂ በአስመሳይ ፕሮፖጋንዳ፣ በኃይልና በተፅዕኖ አይገነባም”፣ “የአገራችን ችግሮች በነፃና ፍትሐዊ ምርጫ በሚገለጽ የሕዝብ ውሳኔ እንጂ በኃይል ዕርምጃ አይፈቱም”፣ “ከምርጫ በፊት የምርጫ ውድድር ሜዳው የሚስተካከልበት ውይይትና ድርድር ይካሄድ”፣ ወዘተ የሚሉ መፈክሮች ተካተዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ሕዝቡ በ1ለ5 መረብ አፈናና ቁጥጥር ከሚካሄድ የምርጫ ድምፅ አሰጣጥ ነፃ እንዲሆን የሚጠይቁና ገለልተኛ የምርጫ ቦርድ በፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎ እንዲቋቋም የሚጠይቁ መፈክሮችም ተካተዋል፡፡
በሰላማዊ ተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ላይ የሚካሄደው እስራትና ወከባmedrek7እንዲቆም፣ የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ፣ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ለገዥው ፓርቲ የሚያሳዩትን ወገንተኝነት በአስቸኳይ እንዲያቆሙ፣ በልማት ስም በሕገወጥና ግብታዊ በሆነ መንገድ ሕዝብን ማፈናቀል እንዲቆም፣ የውኃ፣ የመብራት፣ የትራንስፖርትና የስልክ አገልግሎቶች ችግሮች በአስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጣቸው የሚጠይቁ መፈክሮችም የሠልፉ አካል እንደሆነ በዝርዝሩ ውስጥ የተካተቱ ናቸው፡፡
ሰላማዊ ሠልፉ ከአራት ኪሎ በስተምሥራቅ ከሚገኘው የግንፍሌ ድልድይ በመነሳት በቀበና ወንዝ ድልድይና በባልደራስ በኩል አድርጐ ወረዳ 8 ኳስ ሜዳ (ድንበሯ ክሊኒክ ፊት ለፊት) ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ላይ ጀምሮ ከቀኑ በሰባት ሰዓት እንደተጠናቀቀ ተገምቶዋል፡፡ (ከሪፖርተር የተወሰደው ተሻሽሎ እንደቀረበ)

የሳውዲ መንግስት ማስጠንቀቂያና እርምጃ – በነቢዩ ሲራክ


  • 4372
     
    Share
ነቢዩ ሲራክ
የሳውዲ መንግስት የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውንና ህጉ በማይፈቅደው መንገድ የመኖሪያ ፈቃዳቸው ካለው ሙያ ውጭ የሚሰሩ የማናቸውንም ሀገር ዜጎች በመላ ሀገሪቱ ለማጽዳት የተደራጀ ዘመቻ ከተጀመረ ወር ደፍኗል። በየቀኑ በመንግስትና በግል መገናኛ ብዙሃን የሚለቀቁት የማስጠንቀቂያ መረጃዎች ከበድ ከበድ ያሉ ናቸው።
saudi-arabia-2
ዛሬ ማለዳ “ህገ ወጦችን ጠራርገን እናስወጣለን” ያሉትን የሰራተኛ ሚኒስትር አድል ፈቂን ይዞ የወጣው አረብ ኒውስ ሚኒስትሩ ሃገራቸው ለህገ ወጥ ሰራተኞች ቦታ እንደሌላት በአጽንኦት መጠቆማቸውን ያስረዳል። የሰራተኛ ሚኒስትሩ በማከልም መንግስት ህገ ወጦችን እግር በእግር እየተከታተለ በመያዝ የማስወጣቱን ስራ እንደሚገፉበት ሲያስታውቁ 150 የሚደርሱ ተጨማሪ የሴት ተቆጣጣሪዎች ስልጠና ተሰጥቷቸው ህገ ወጦችን በማጣራቱ ስራ መሰማራታቸውን አስረድተዋል። ተቆጣጣሪዎች ስራቸው ሲከውኑ በተአማኒነት፣ በሃላፊነትና ፍትሃዊ በሆነ አግባብ ባለው መንገድና ስርአት መሆን እንደሚገባው ሚኒስትር አድል ፈቂ አሳስበዋል። የሰራተኛ ሚኒስትር አድል ፈቂ በቤት ሰራተኛ አቀጣጣጠር ዙሪያ ያለውን ችግር ለመፍታታ ከ200 የተለያዩ ሃገር ዜጎች ጋር መምከራቸውንና በጠቃሚው ምክክር የተገኙትን መፍትሄ ሃሳቦች በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርጉ አሳስበዋል።
ዘመቻው . . .
ወር በደፈነው በዚህ መጠነ ሰፊ ዘመቻ ኢላማዎች ፈርጀ ብዙ በሆነ ምክንያት ሳውዲ ገብተው በህገ ወጥነት የሚኖሩትን ጨምሮ በኮንትራት ቪዛ መጥተው ከአሰሪዎቻቸው የጠፉትን ያጠቃልላል። ዘመቻው ጅዳ ደርሶ በተለያዩ አካባቢዎች በየመኖሪያ ቤቱ አሰሳው ተጠናክሮ መቀጠሉን የሳውዲ መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡት ነው። እስካሁን በቀጠለው በዚህ ዘመቻ በኢትዮጵያውያን ላይ ሲያዙ ማንገላታትም ሆነ የተለየ ጥቃት መስተዋሉን አልሰማሁም። መኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ቢያዙም እየተጣራ ተለቀዋል። ህጋዊ መኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውና ከአሰሪያቸው የጠፉት ግን እየተያዙ ተወስደዋል። ዘመቻው ግን አሁንም ቀጥሏል . . .
በዘመቻው የተያዙት በርካታ ዜጎችን ስልክ እየደወሉ እንደገለጹልኝ ከሆነ “በፍተሻው ስንያዝ የረባ ልብስ እንኳ አልለበስንም፣ ለአመታት ያፈራነው ንብረታችን አልሰበሰብንም፣ የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮች ቢያንስ ሻንጣችን ይዘን የምንገባበትን መንገድ ያዘጋጅልን” ሲሉ ተደጋጋሚ ምሬታቸውን ገልጸውልኛል!
ወደ “ተስፋዋ ምድር” ያላባራው ጉዞ . . .
ወደ “ተስፋዋ” የአረብ ሃገር ምድር ወደ ሳውዲ የሚደረገው ጉዞ አላቆመምም። የእኛ ደላሎች ከሳውዲ እስከ ሀገር ቤት ትላልቅ ከተሞች፣  ገጠርና የወረዳ ከተሞች በዘለቀ የእዝ ሰንሰለት ተደራጅተው በወገናቸው ስደት ተጠቃሚ ሆነዋልና በማን አለብኝነት ሰውን እያጋዙት ይገኛሉ። አምና ካቻምናና ዘንድሮ በአሳር በመከራ ሀገር ቤት የገቡት ኢትዮጵያውያን እነሱ “የተስፋ ምድር ” ወደ ሚሏት ሳውዲ እየጎረፉ ነው። ባሳለፍነው ወር በተደጋጋሚ የየመን የቀይ ባህር ዳርቻ የቅርብ ርቀት ባህር ከበላቸው ወገኖች ባልተናነሰ በየበርሃው በአሸጋጋሪ ደላሎች ታግተው አሳር መከራቸውን የሚያዩትን ወገኖች የከፋ የስቃይ ስደት ህይወት ያማል።
እነ ሞት አይፈሬዎች የእኛ ዜጎች አሳምረው የሚያውቁትን የሞት ጉዞ ተከትለው፣ ሞትን ዳግም ለመፋጠጥ ቆርጠው፣ ከቀያቸው ነቅለው  የመጡ ይመስላል። እነሱን በአደጋ አስከብቦ እዚህ ስላደረዳቸው ምክንያት አብዛኞችን ስንጠይቃቸው ጣራ የነካው የኑሮ ውድነት፣ ድህነት፣ የተሻለ ኑሮ ፍለጋውን አማረው ይነግሩናል። አንዳንዶች ከተጠቀሰው ምክንያት አዳምረው በሀገር ቤት የፖለቲካው ትኩሳት ሙቀት የመለብለቡ ፍርሃቻን እንደ ምክንያት ያቀርቡታል። ያን ሰሞን ሃገር ቤት ለእረፍት የሄዱ የቤተሰብ አባሎቸንና ወዳጆቸን ሀገር ቤት ስላለው የኑሮ ውድነትና ኑሮ ጠይቄያቸው የእድገት ምጥቀቱን፣ ገንዘብ ላለው ሀገር ቤት የመመቸቱንና አንገቱን ደፍቶ ልስራ ላለ ስራ ሰርቶ መለወጥ እንደሚቻል አጫውተውኛል። ታዲያ ሰው ለምን ይሰደዳል? ለሚለው ጥያቄየ ግን መልሱ “እሱ ግራ የሚያጋባ ነው!” የሚል ነው። እርግጥ ነው ይህ ምላሽ አጥጋቢ ሆኖ አላገኘሁትም . . . የሀገር ቤቱ እውነታ እድገት ምጥቀቱ፣ ገንዘብ ላለው ሀገር ቤት የመመቸቱንና አንገቱን ደፍቶ ልስራ ላለ ስራ ሰርቶ መለወጥ እየተቻለ አስከፊውን ስደት የማያውቁትን ቢያጓጓም ከሞት ጋር ተፋጠው ተሰደውና ወደ ሀገር ቤት በዘመቻ ተመልሰው የገቡት እንዴት የመከራ ሰቀቀኑን የአረብ ሀገር ስደት መረጡት? ብሎ መጠየቅ ግድ ይላል፣ ለዚህም ሁነኛ የሆነ መልስ ሰጭ አካል አልተገኘም!  ይህ ምላሽ እስኪያገኝ ግን ወደ “ተስፋዋ የአረብ ምድር ” የሚደረገው ስደት ተጠናክሮ ቀጥሏል …
ላለፉት ሶስትና አራት ተከታታይ አመታት የሁለት ሃገራት ውል ባልተዋዋሉበት፣ ቅድመ ዝግጅት ባልተደረገበት ሁኔታ በኮንትራት ስራ ስም ከግማሽ ሚሊዮን የሚበልጡ አብዛኛው ሴት እህቶቻችን ወደ ሳውዲ ገብተዋል። ምንም እንኳን የተሳካላቸው በተወሰነ መንገድ እራሳቸውን ረድተው ቤተሰቦቻቸውን እየረዱ መሆናቸው ባይካድም መብት ጥበቃ የጎደለባቸው፣ ያለተሳካላቸው ከአሰሪዎቻቸው ጠፍተው ህገ ወጥ ነዋሪነቱን ተቀላቅለው የሰቀቀን ኑሮን እየገፉ ነው። በአንጻሩ በአሰሪዎቻቸው ተቀፍድደው ተይዘው መላወሻ ያጡት የተጨነቁት ምንም ማድረግ ያልቻሉት ከጨለማው ኑሮ ከእገታው ለመላቀቅ በለየለት ወንጀል ተዘፍቀው ስማችን አክፍተውታል። የቀሩት አሁን ድረስ የገሃነም ኑሮን እየኖሩ ነው። የዚህ ሁሉ ክስተት ምክንያት ህጋዊ ውል በሌለበት፣ የመብት ጥበቃው ባልተጠናከረበት ሁኔታ የኮንትራት ስራ መጀመሩ መሆኑን ገና ኮንትራት ሊጀመር ነው ሲባል እኔም ሆንኩ “ያገነባናል” ያልን ባቀረብናቸው ጭብጥ መረጃዎች እንደ ዜጋ ከነመፍትሄ ሃሳቡ ጥቁመን ነበር ።  ያ ሰሚ ሳያገኝ ቀርቶ እዚህ ደርሰናል። ይህ በመሆኑ ትልቅ ስህተት ተሰርቷል ባይ ነኝ።
ዛሬም “ከስህተቱ ተምረናል” ብለን እያቀነቀንን፣ ግን ከስህተቱ ያለመማራችን ጠቋሚ መረጃ እየሰማን ነው። ከአመት በፊት የተዘጋው የኮንትራት ስራ ሊከፈት “ረቂቅ ደንብ ” ወጥቷል ተብሏል። ያን ሰሞን ኤጀንሲዎች በረቂቁ ዙሪያ ሲመክሩ በዜጎች መብት ማስጠበቅ ዙሪያ ያሉት ነገር ባይሰማም ስለሚያስይዙት ገንዘብ አማረው ሲናገሩ ሰምተናል። በውይይቱ የገንዘቡ ከፍ ማለት “ህገ ወጥ ስደቱን ያባብሰዋል” ያሉት ኤጀንሲዎች ስለየትኞቹ ህገ ወጥ ስደተኞች እንደሚያወሩ ግራ እየገባን መመጻደቁን ሰምተነዋል። ይህን ማለቴ ህገ ወጥነትን ያባብሳል ያሉት አይገባምና ነው፣ ለመሆኑ ባህር ቆርጠው በየመን እየገቡ ያሉት አብዛኛው ወንድ ወንድሞቻችን የገጠር ልጆች የኮንትራት ስራ ቪዛው ተጠቃሚ አድርጎ መውሰዱና አግባብ ነውን? ይህ ማስመሰያ ምክንያት ሊታረም ይገባል። ያም ሆኖ በኤጀንሲዎችና በደላሎች አማካኝነት በየመን፣  በሱዳንና በዱባይ የጉብኝት ቪዛዎች ሽፋን እየተሰጣቸው አሁን ድረስ ለሚሰደዱትን መላ አልተገኘለትምና ጉዞው አላቆመም። የኤጀንሲዎች “ህገ ወጥ ጉዞን ያበረታታል” ለማለት የሰጡት ምክንያት እኒህኞቹን ለመታደግ ከሆነ ደግሞ እንደ ዜጋ ኤጀንሲዎች አዲሱ ረቂቅ ከገንዘብ ማስያዙ በላይ ቀድሞውንም ባላስጠበቁት መብት ላይ መነጋገር እንጅ በየጣለባቸው ግዴታ ላለማሟላት ጉንጭ አልፋ ምክክር ማድረጋቸው አያስደስትም ።
ማጠቃለያ
የኢትዮጵያ መንግስት በአረብ ሃገሩ ስደት ጉዳይ ላይ ከፕሮፖጋንዳ ያለፈ ጥልቅ ጥናት ባላደረገበት ሁኔታ የሚሰራውን ስራ ቆሞ ሊመረምር ግድ ይለዋል!
ወገኔ ሆይ፣ በሃገር ቤት ወደ አረብ ሃገራት ለመሰደድ የቋመጠው ወገንም ከፊት ለፊቱ ያለውን አደጋ ሊያስተውልና ሊመረምረው ይገባል! በባህር እና በበርሃው በባዕድ ምድር ደመ ከልብ ሆኖ ከማለፍ በወገን መካከል በሃገር የመጣውን ችሎ ማለፉ ይበጃል ባይ ነኝ!
ባለ ጊዜ ባለጸጋዎች ደላሎች ሆይ፣ ላንድ አፍታ ወደ ነፍሳችሁ ተመልሳችሁ በወገኖቻችሁ በተለይ ለአቅመ አዳም በደረሱና ባልደረሱ እህቶችን ላይ ቅቤ እያነጎታችሁ በማማለል እየፈጸማችሁት ያለውን ዘመን የማይሽረው ግፍና በደል ተረጋግታችሁ አስቡት! ጊዜው ቢያልፍም፣ በሰራችሁት በደል ጠያቄ እንኳ ቢታጣ ውሎ አድሮ ከማይተዋችሁ የህሊና ጸጸት ለመዳን ስትሉ ከክፉው ምግባራችሁ ራሳችሁን ለመግታት ሞክሩ! ሌላ ምን እላለሁ!
ቸር ያሰማን!

የሰሞኑ አደናጋሪ ወሬዎች ,,በአባዱላ ገመዳ የተመራ "የፐብሊክ ዲፕሎማሲ" ልዑክ ቡድን ወደ ግብጽ አምርቷል ,,."የህዝብ ፍላጎት ከሆነ ጅቡቲን ከኢትዮጵያ ጋር እናዋህዳታለን"...



Fasil Yenealem
የሰሞኑ አደናጋሪ ወሬዎች
1- በአባዱላ ገመዳ የተመራ "የፐብሊክ ዲፕሎማሲ" ልዑክ ቡድን ወደ ግብጽ አምርቷል። "ፐብሊክ ዲፕሎማሲ" የተባለው "የህዝብ" ዲፕሎማሲ ለማለት ተፈልጎ መሰለኝ። አባ ዱላ ፖለቲከኛ ነው፣ ያውም አፈ ጉባኤ። ፓለቲከኛው እየመራ የወሰደውን ቡድን እንዴት ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ልንለው እንችላለን?። ይሁን ግዴለም ብለን ብንቀበለው እንኳ " ፐብሊክ ዲፕሎማሲ" የሚሰራው ስራ ምንድነው? የሚለውን ለመመለስ በቀላሉ የሚቻል አይመስለኝም። በአለማቀፍ ግንኙነት ውስጥ ፐብሊክ           ዲፕሎማሲ የሚባል ነገር መኖሩን አላውቅም። ዲፕሎማሲ ጥቅምን ለማስጠበቅ ፖለቲከኞች የሚጫወቱት ጨዋታ ነው። የዲፕሎማሲን ጨዋታ የሚጫወቱት ፖለቲከኞች ብቻ ናቸው። አሸናፊም ተሸናፊም ሆነው የሚወጡት እነሱ ናቸው፤ ጉልበትና እውቀት ያለው ብዙውን ጊዜ አሸናፊ ይሆናል፤ አልፎ አልፎ ጉልበት ሳይኖርህ እውቀት ካለህ ታሸንፋለህ፣ ልክ ኤርትራ በባድሜ ላይ የተደረገውን ክርክር እንዳሸነፈች ማለት ነው ። ፊርማ የማኖር ስልጣንም የእነሱ ብቻ ነው። ህዝብ ድጋፍ ወይም ተቃውሞ ከማድረግ ውጭ ሌላ ሚና የለውም።
ዲፕሎማቶች በቅድሚያ ስልጣናቸውን ከዚያም አገራቸውን ግምት ውስጥ አስገብተው ይደራደራሉ። ጥቅምና ጉዳቱን እየመዘኑ እየሰጡ ይቀበላሉ። ግብጽ በኢትዮጵያ ላይ የምትከተለውን ፖሊሲ በህዝብ ጋጋታ ማስቀየር አይቻልም፤ አይደለም 20 ልኡካን፣ 90 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ግብጽ ቢገቡ እንኳ የአገሪቱ ዲፕሎማቶች ጥቅማቸውን አስልተው ከሚወስኑት ውሳኔ አንድ ጋት ፈቀቅ አይሉም። ቴውድሮስ አድሃኖም የዲፕሎማሲውን ስራ መስራት ሲያቅተው "የህዝብ ዲፕሎማሲ" እያለ ያታልላል። በህዝብ ጋጋታ ጠብ የሚል ነገር አይኖርም፤ ራስን ለማታለል ወይም በአገር ሃብት ለመቀለድ ካልሆነ በስተቀር።
አንድ አገር የዲፕሎማሲ ሃይል እንዲኖራት ከተፈለገ በቅድሚያ ውስጣዊ ሃይሏን ማጠንከር አለባት። ውስጥህ ተዳክሞ ጠንካራ ዲፕሎማሲ ልትገነባ አትችልም። በቅድሚያ አገራዊ አንድነት ካልፈጠርክ ባላንጣህ የውስጥህን ችግር ተጠቅሞ የራሱን ጥቅም ያራምድበታል። ግብጽንም ይሁን ሌሎች አገሮችን ደጅ የምንጠናው ውስጣዊ አንድነት ስለሌለን ነው፤ ውስጣዊ አንድነትን ለመመስረት በቅድሚያ አንድ ሊያደርጉን በሚችሉት ላይ መግባባትና ስምምነት ላይ መድረስ አለብን፣ ይህን ማድረግ የምችለው ደግሞ ዲሞክራሲያዊ መንግስት መመስረት ስንችል ብቻ ነው፤ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር ፍጹም ባይሆንም ከእርሱ የተሻለ አብሮ የሚያኖር ሌላ ስርዓት እስካሁን ስላልተፈጠረ እሱን ከመቀበል ውጭ ሌላ አማራጭ የለንም። ህወሃት መራሹ መንግስት፣ ውስጣዊ አንድነትን ሊያመጣ እንደማይችል አይተነዋል፤ ህወሃት እስካልተወገደና የሁሉም የሆነ መንግስት እስካልተመሰረተ ድረስ መቼውን ጠንካራ ዲፕሎማሲ መገንባት አንችልም።
2- ሌላው የገረመኝ የተከበሩ ብቸኛው የፓርላማ አባል የሚባሉት አቶ ግርማ ሰይፉ በዚህ "የፐብሊክ የዲፕሎማሲ" ቡድን ውስጥ መካተታቸው ነው። አቶ ግርማ ስለአባይ ግድብ ጠቀሜታ ግብጾችን ለማስረዳት ነው ወይስ ግብጽን ጎብኝቼ ልምጣ ብለው ነው የሄዱት? በዚህ አያያዛቸው ነገ ለአባይ ቦንድ ቅስቀሳ አውሮፓ ሳናገኛቸው አንቀርም። ሰሞኑን ህገመንግስታችን በነውጠኞችና በታጣቂ ሃይሎች እንዳይፈርስብን ኢህአዴግ ይታደገው እያሉ የጻፉትን የተማጽኖ ደብዳቤ አንብቤዋለሁ፤ ምናልባት ግብጽ እነዚህን ነውጠኞች " እባክሽ አትርጅብን" ብለው ሊለምኑዋት ይሆን ይሄዱት? የኢህአዴግን ፕሮፓጋንዳ አምነው ተቀበሉ ማለት ነው? የምር የኢህአዴግ ፕሮፓጋንዳ አንድን የተቃዋሚ አመራር ማሳመን ከቻለ ዘመኑ ተለውጧል ማለት ነው። ለማንኛውም አቶ ግርማን በቅርቡ " ብቸኛው የግል ተወዳዳሪ የፓርላማ አባል" እያልን የምንጠራቸው ይመስለኛል፤ እንደምንም ከተመረጡ ማለቴ ነው።
3- "የህዝብ ፍላጎት ከሆነ ጅቡቲን ከኢትዮጵያ ጋር እናዋህዳታለን" የሚል ዜናም በሪፖርተር በኩል አይቻለሁ። ለጅቡቲው መሪ " ትዋሃዳላችሁ ወይ?" ብለው ጥያቄ የጠየቁት የእኛዎቹ ጋዜጠኞች ናቸው። የእኛዎቹ ጋዜጠኞች አላማቸው ይታወቃል። መንግስት " ጅቡቲ ወደቡዋን ልትዘጋብን ትችላለች" እያለ ለፈረንጅ ሲጽፍ፣ የእኛ ጋዜጠኞች ደግሞ " ጅቡቲ ከኢትዮጵያ ጋር ልትዋሃድ ነው" እያሉ መጻፋቸው በአገዛዙና በወኪል ጋዜጠኞቻቸው መካከል ያለውን አለመናበብ ያሳያል። የጅቡቲ ጋዜጠኞች የእኛዎቹን ገዢዎች ተመሳሳይ ጥያቄ ቢጠይቁዋቸው ኖሮ ትንሽም ቢሆን አመኔታ ይኖረው ነበር፤ የጅቡቲ ጋዜጠኞች ግን ያውቃሉ፣ መንግስታቸውም ህዝባቸውም ውህደቱን አይፈልገውም።
አንድ አገር ከሌላ አገር ጋር ከመዋሃዱ በፊት ቢያንስ ሶስት ጥቅሞችን እንደሚያገኝ ማረጋገጥ አለበት። አንዱ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ነው። ጅቡቲዎች የነፍስ ወከፍ ገቢያቸው ወደ 850 ዶላር ነው። የእኛ ደግሞ ከ400 ዶላር አይበልጥም። ታዲያ ተረቱም እኮ "ትንሽ ቆሎ ይዘህ ከትልቅ ተጠጋ ነው" የሚለው። ጅቡቲዎች ወደኛ የሚመጡት ድህነታችን ሊካፈሉን ነው? ቀልድ እኮ ነው የምር። ሌላው የመዋሃድ ጠቀሜታ የደህንነት ዋስትና ለማግኘት ነው። ጅቡቲ ደህንነቷን የሚያስጠብቅላት የፈረንሳይ ሚራጅ አለላት። መለዋወጫ የሌላቸው የእኛ ጄቶች እንደማያድኗት በደንብ ታውቃለች። ለደህንነቷ ሰግታ ከኢትዮጵያ ጋር የምትዋሃድበት ምክንያት በፍጹም የለም። ሶስተኛው ጠቀሜታ ስነልቦናዊ ነው። ጀርመኖች ከሁለት ሲከፈሉ የስነ ልቦና ጉዳት ደርሶባቸው ነበር፤ ኮሪያዎችም እንዲሁ። እነዚህ ህዝቦች ሲዋሃዱ ትልቅ የስነልቦና እረፍት አግኝተዋል። አንድ ህዝብ ናቸውና ዘመድ ከዘመድ መገናኘቱ ለጤና ጥሩ ነው። ጅቡቲ የኢሳና የአፋር መኖሪያ ናት። ስልጣን የያዙት ኢሳዎች ናቸው። ኢሳዎች ደግሞ ከኢትዮጵያ ይልቅ ቅርበታቸው ለእናት ሶማሊያ ነው። ከኢትዮጵያ ጋር ከሚዋሃዱ 5 ኮከብ ባላት ሶማሊያ ውስጥ ቢጠቃለሉ ይመርጣሉ። አፋሮች ስልጣን ቢይዙ ይሁን ብለን ልንቀበል እንችላለን። አፋር ልቡም እምነቱም ኢትዮጵያዊ ነው፤ ከኢትዮጵያ ውጭ የሚሄድበት ሌላ አገርም የለውም። ኢሳዎች ወደ እኛ ከሚመጡ ወደ ሶማሊያ ቢያዘግሙ ይሻላቸዋል።

ከፍተኛ ድብደባ የደረሰባቸው አቶ ተሰማ ወንድሙ ህይወታቸው አደጋ ላይ ነው


(ሰማያዊ ፓርቲ) በአዳር ሰልፍ ወቅት ተይዘው ከፍተኛ ድብደባ የደረሰባቸው የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት (መአሕድ) ምክትል ፀኃፊ መቶ አለቃ ተሰማ ወንድሙ ራሳቸውን ስተው ሆስፒታል እንደገቡና ሕይወታቸው አደጋ ውስጥ እንደሆነ የፓርቲው ፕሬዝደንት አቶ ሽዋንግዛው ገ/ስላሴ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
መቶ አለቃ ተሰማ ወንድሙ በአዳሩ ሰላማዊ ሰልፍ ወቅት ተይዘው ከፍተኛ ድብደባ የደረሰባቸው ሲሆን ለአምስት ቀናት ቀዝቃዛና ጨለማ ቤት ውስጥ ታስረው ቆይተዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ከታሰሩበት ጊዜ ጀምሮ የስኳር በሽታ መድሃኒታቸውን በመቀማታቸውና ህክምናም ባለማግኘታቸው ታመው እንደነበር መገለጹ ይታወሳል፡፡
መቶ አለቃ ተሰማ ወንድሙ በድብደባውና በስኳር በሽታ ምክንያት በአሁኑ ወቅት ዘውዲቱ ሆስፒታል የሚገኙ ሲሆን ሆስፒታል ከገቡበት ቅዳሜ ታህሳስ 4/2007 ዓ.ም ጀምሮ ሰው ማናገር አለመቻላቸውን የፓርቲው ፕሬዝዳንት አክለው ገልጸዋል፡፡


AEUP leadership member

Monday, December 15, 2014

አንድነት በጥቂት ቀናት ውስጥ የጠራው ጠቅላላ ጉባኤ በስክት ተጠናቋል ,, ዘ- ሐበሻ


አንድነት በጥቂት ቀናት ውስጥ የጠራው ጠቅላላ ጉባኤ በስክት ተጠናቋል፤ የፓርቲው ተ/ም/ፕሬዝዳንት አቶ ተክሌ በቀለ የጉባኤውን የመዝጊያ ንግግር በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ አቶ ተክሌ በንግግራቸው አንድነት በብሔርም ሆነ በህብረብሔር ፓርቲዎች ጋር አብሮ ለመስራት መዘጋጀቱን እንዲሁም ከአንድነት ጋር ተመሳሳይ ፕሮግራም ላላቸው ፓርቲዎች ሁሉ የውህደት ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ አቶ ተክሌ አክለውም አንድነት የ2007 ምርጫን በአሸናፊነት ለመወጣት እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ከትላንት ጀምሮ እያካሄደ ባለው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ስልጠና እየተሰጠ ነው፤ በዛሬው መርሀ ግብር በሀገሪቱ ነባራዊ ሁናቴዎች(የአርሶ አደሩ ፤የከተማው ነዋሪ፤የባለሐብቱ ሁናቴ) በዳግማዊ ተሰማ የተማሪውና የምሁሩ ሁናቴ በጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ የአንድነት የምርጫ ስትራቴጂ ግብ በፓርቲው ፕሬዝዳንት አቶ በላይ ፈቃዱ ቀርቦአል፡፡ በመቀጠልም የስልጠናው ተሳታፊዎች ጥያቄና አስተያየት በመስጠት የጠዋቱ ስልጠና ተጠናቆ፣ የአንድነት ፓርቲ ም/ፕሬዝዳንት የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ በምርጫ ስትራቴጂ ዙሪያ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡ በመቀጠልም የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የህግና ሰብአዊ መብት ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ገበየሁ ይርዳው የአባላት መብትና ግዴታ ከፓርቲው ደንብና ከፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ አንጻር ስልጠና ሰጥተዋል ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት መድረኩ ለውይይት ክፍት ሆኖ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡
10801506_830102687048482_9079775044209922653_n
10847773_830102467048504_99358985024134609_n
በመቀጠልም የስልጠናው ተሳታፊዎች ጥያቄና አስተያየት በመስጠት የጠዋቱ ስልጠና ተጠናቆ፣ የአንድነት ፓርቲ ም/ፕሬዝዳንት የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ በምርጫ ስትራቴጂ ዙሪያ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡ በመቀጠልም የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የህግና ሰብአዊ መብት ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ገበየሁ ይርዳው የአባላት መብትና ግዴታ ከፓርቲው ደንብና ከፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ አንጻር ስልጠና ሰጥተዋል ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት መድረኩ ለውይይት ክፍት ሆኖ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡
10689712_742890089129261_399577300201419677_n
የፓርቲው ተ/ም/ፕሬዝዳንት አቶ ተክሌ በቀለ የጉባኤውን የመዝጊያ ንግግር በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ አቶ ተክሌ በንግግራቸው አንድነት በብሔርም ሆነ በህብረብሔር ፓርቲዎች ጋር አብሮ ለመስ…
1957988_742880462463557_856926840329555149_n
በአሁኑ ሰዓት ጉባኤው ለጋዜጠኞችና ለክብር እንግዶች ክፍት ሆኗል፡፡ አንድነት ፓርቲ ለዞንና ለወረዳ አመራሮች ያዘጋጀው ስልጠና በስኬት ተጠናቋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ጉባኤው ለጋዜጠኞችና ለክብር እንግዶች ክፍት ሆኗል፡
1501666_742879365797000_2313086908782721306_n
በአሁኑ ሰዓት ጉባኤው ለጋዜጠኞችና ለክብር እንግዶች ክፍት ሆኗል፡፡ አንድነት ፓርቲ ለዞንና ለወረዳ አመራሮች ያዘጋጀው ስልጠና በስኬት ተጠናቋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ጉባኤው ለጋዜጠኞችና ለክብር እንግዶች ክፍት ሆኗል፡

10857738_830102633715154_3545412742057696770_n

የጉባኤውን መዝጊያ በማስመልከት የተለያዩ የሙዚቂ ዝግጅቶች እየቀረቡ ነው፡፡
1979760_830121140379970_5791000346813560187_n
10850209_830120993713318_7821501057591246485_n
10429209_830121313713286_3649092189897821075_n
የጉባኤውን መዝጊያ በማስመልከት የተለያዩ የሙዚቂ ዝግጅቶች እየቀረቡ ሲሆን በየጣልቃው የአንድነት ፓርቲ ድጋፍ ሰጪዎች ከመላው ዓለም የድጋፍ መልዕክት እያስተላለፉ ነው፡፡
በአሁኑ ሰዓት ጉባኤው ለጋዜጠኞችና ለክብር እንግዶች ክፍት ሆኗል፡፡ አንድነት ፓርቲ ለዞንና ለወረዳ አመራሮች ያዘጋጀው ስልጠና በስኬት ተጠናቋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ጉባኤው ለጋዜጠኞችና ለክብር እንግዶች ክፍት ሆኗል፡፡
10606170_742879392463664_586079173473258862_n10698475_829409667117784_3680643737158512454_n10696378_830102643715153_5337011227327904207_n10868059_742890132462590_6829345466535035832_n10857738_830102633715154_3545412742057696770_n10391385_742367799181490_9096613242778417442_n
10698475_829409667117784_3680643737158512454_n

• ‹‹በፖለቲካ አመለካከቴ ምክንያት ሁልጊዜም እኔን ማባረር ይፈልጋሉ›› አቶ ወሮታው ዋሴ

Negere Ethiopia's photo.
 ምንጭ  ነገረ ኢትዮጵያ  
አየር መንገድ የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራርን ከስራ አባረረ
‹‹በፖለቲካ አመለካከቴ ምክንያት ሁልጊዜም እኔን ማባረር ይፈልጋሉ›› አቶ ወሮታው ዋሴ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሰማያዊ ፓርቲ የፋይናንስ ጉዳይ ኃላፊ የሆኑትን አቶ ወሮታው ዋሴን ከስራ አባረረ፡፡ አቶ ወሮታው ከስራ የተባረሩት ጥፋት ያጠፋን ሰራተኛ አልቀጣህም በሚል ሲሆን በእሳቸው ስር የነበረውና አጠፋ የተባለው ሰራተኛ ጉዳይ ተመርምሮ ወደ ስራ መመለሱ ታውቋል፡፡
አቶ ወሮታው ከእሳቸውም በላይ ጉዳዩ የሚያገባው የማኔጅመንት አባል በተመሳሳይ ጉዳይ የአምስት ቀን ደመወዝ ብቻ ሲቀጣ እሳቸው ከስራ መባረራቸው በፖለቲካ አመለካከታቸው ላይ የተመሰረተና ፖለቲካዊ ውሳኔ እንደሆነ ያሳያል ብለዋል፡፡ ከስራቸው ይሰራ የነበረው ሰራተኛ ጥፋተኛ አለመሆኑን የገለጹት አቶ ወሮታው ‹‹በፖለቲካ አመለካከቴ ምክንያት ሁልጊዜም እኔን ማባረር ይፈልጋሉ›› ሲሉ የተባረሩት በፖለቲካ አመለካከታቸው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
አቶ ወሮታው ዋሴ ከሁለት አመት በፊት በኢሜል ለህዳሴው ግድብ ገንዘብ እንዲያዋጡ በተጠየቁበት ወቅት ለተላከው የኢሜል መልዕክት አልከፍልም ብለው በመመለሳቸው ‹‹ሰራተኛ በማሳመጽ፣ የኢንዱስትሪ ሰላም በማናጋት›› በሚል ተከሰው ተባርረው ከሁለት አመት በኋላ በፍርድ ቤት ወደ ስራ መመለሳቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ 
በወቅቱ አየር መንገድ አቶ ወሮታው ዋሴ ካሳ ተከፍሏቸው እንዲለቁ ይግባኝ ጠይቆ የነበር ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለሁለት አመት ካራዘመ በኋላ ወደ ስራ እንዲመለሱ አዝዞ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ ጥፋተኛ ነው ብሎ ያባረራቸው አየር መንገድ ወደ ስራ በተመለሱ በ15 ቀናት ውስጥ ሰርተውበት ወደማያውቁት ክፍል በማዘዋወር እድገት አግኝተው የማኔጅመንት አባል እንደሆኑ እንደገለጸላቸው የሚናገሩት አቶ ወሮታው እድገቱ ሰራተኛ ሲባረር የመክሰስ መብት ስላለው፣ በተቃራኒው ግን ሳይፈልጉት በእድገት የማኔጅመንት አባል እንዲሆኑ የተደረገው የማኔጅመንት አባል የሆነ ግለሰብ ቢባረርም የመክሰስ መብት የሌለው በመሆኑ ሆን ተብሎ ለማባረር የተደረገ ስልት ነው ብለዋል፡፡ አቶ ወሮታው በወቅቱ ይህን እድገት አልቀበልም ብለው እንደነበርም ገልጸውልናል፡፡
አቶ ወሮታው ዋሴ አሁን ከስራ ባባረራቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ለ14 ዓመታት ያህል ማገልገላቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

Friday, December 5, 2014

በትግራይ፣ አማራ ክልሎች የሃይማኖት መሪዎች የተሰጣቸውን የደህንነት ስራ በትክልል አልሰሩም በሚል ተተቹ // የከምባታ ጠንባሮ ዞን ህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጉ ተገለጸ

በትግራይ፣ አማራ ክልሎች የሃይማኖት መሪዎች የተሰጣቸውን የደህንነት ስራ በትክልል አልሰሩም በሚል ተተቹ
ኀዳር ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ባዘጋጀው የ2006 የጸጥታ የደህንነት ግምገማ ላይ የተገኙ የተለያዩ ክልሎች የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊዎች ባቀረቡት ሪፖርት በአዲስ አበባ የሃይማኖት አባቶች የተሰጣቸውን የደህንነት ተልእኮ በፈቃደኝነት አምነው ሲፈጽሙ በትግራይና ፣ በአማራ ክልሎች ግን የሃይማኖት አባቶች ተልእኮዋቸውን በአግባቡ ሳይወጡ ቀርተዋል።
የትግራይ ጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ እንደተናገሩት በክልሉ አብዛኛው ህዝብ የኦሮቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ ቢሆንም፣ የሃይማኖት አባቶች ሽማግሌዎች በመሆናቸው የተሰጣቸውን ተልእኮ እንደ ፌደራል የሃይማኖት አባቶች በአግባቡ እንደማይፈጽሙና ከአመራሩ መመሪያ የሚጠብቁ የራስ ተነሳሽነት የሌላቸውና የአቅም ውስንነት ያላቸው ናቸው ብለዋል።
ይህንኑ ሃሳብ የአጠናከሩት የአማራው ክልል የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ደሴ አሰሜ ደግሞ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ የሃይማኖት አባቶችን ከክልል እስከወረዳ ለማደራጀት ቢሞከርም ተነሳሽነት በመጥፋቱ የታሰበው ሊሳካ አለመቻሉን ገልጸዋል። በተለያዩ ቦታዎች መስኪዶችን ከአክራሪዎች እጅ እየነጠቁ ለመጅሊሱ ማስረከባቸውንም ሃላፊው ተናግረዋል ። በኦሮምያ የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ ደግሞ የፌደራል መጅሊስ አመራሮች መከፋፈላቸውን ገልጸው፣ ክፍፍሉ እስከታች በመውረዱ ችግር እየፈጠረ በመሆኑ አስቸኳይ መፍትሄ መውሰድ ይገባል ብለዋል
በአዲስ አበባ 7ቱም የሃይማኖት ተቋማት ለመንግስት የደህንነት ስራ እየሰሩ መሆናቸውን መዘገባችን ይታወቃል።


በገዥው ፓርቲ አድሏዊ አሰራር ምክንያት ልማትና መልካም አስተዳደር ባለመኖሩ የከንባታ ጠንባሮ ነዋሪዎች ዛሬ ህዳር 26/2007 ዓ.ም ዱራሜ ከተማ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸውን የከምባታ ህዝብ ኮንግረንስ ሊቀመንበር አቶ ኤርጫፎ ኤርዲሎ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ህዝብ ያለ ማንም ቀስቃሽና አስተባባሪ ሰላማዊ ሰልፍ መውጣቱን የገለጹት አቶ ኤርጫፎ የብሄር ብሄረሰቦችን መብት አከብራለሁ በሚል ለፕሮፖጋንዳ መጠቀሚያ ከማድረጉ ውጭ በተግባር ግን በህዝብ ላይ ከፍተኛ በደል እየፈጸመ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
የከንባታና ጠንባሮ ህዝብ ከ1986 ዓ.ም ጀምሮ ተቃዋሚዎችን በተለይም የከምባታ ህዝብ ኮንግረንስን ትደግፋላችሁ በሚል በደል እንደሚደርስበት የገለጹት አቶ ኤርጫፎ ‹‹ህዝቡ በፖለቲካ አመለካከቱ ምክንያት በደል እየደረሰበት ነው፡፡ ምርጫ ሲደርስ መንገድ፣ ዩኒቨርሲቲና ኮሌጅ ይሰራልሃል ይባላል፡፡ ምርጫው ሲያልፍ ለማታለያነት ይሰራሉ የተባሉ ነገሮች ተግባራዊ አይሆኑም፡፡ እስካሁን ከ1993 ዓ.ም አንስቶ ይሰራል የተባለ መንገድ አልተሰራም፡፡ በምርጫ ወቅት አርሶ አደሮችን እያፈናቀሉ ኮሌጅና ዩኒቨርሲቲ እንሰራለን ይላሉ፡፡ ከምርጫ በኋላ ግን ይህ መሬት የሚሰጠው ለሹመኞች ነው፡፡ ሁለቱም ጠቅላይ ሚኒስትሮች የምርጫ ሰሞን በየ ቦታው የመሰረት ድንጋይ ተክለዋል፡፡ ከምርጫ በኋላ ግን ለሹመኞች ይሰጣል፡፡ ዛሬ ህዝቡ ሰላማዊ ሰልፍ የወጣውም ከዚህ አንጻር ነው፡፡›› ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
የከንባታ ጠንባሮ ህዝብ ባለፉት ምርጫዎች ተቃዋሚዎችን በመምረጥ ከገዥው ፓርቲ ጋር ያለውን ልዩነት በግልጽ እንዳሳየ የገለጹት አቶ ኤርጫፎ ‹‹ወጣቶች ልማትና የትምህርት እድል ስለማያገኙ ወደ ደቡብ አፍሪካና አረብ አገራት እየተሰደዱ መንገድ ላይ እየሞቱ ነው፡፡ በቀን 11 አስከሬን የመጣበት ጊዜ አለ፡፡ በስርዓቱ አድሏዊ አሰራር ምክንያት ከንባታ ጠንባሮ ወጣቱ ከቀየው እየተፈናቀለ የሚሰደድበት ትልቁ ዞን ነው ማለት ይቻላል፡፡›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በዛሬው እለት አርሶ አደሩ፣ ተማሪውና ነጋዴው የዞኑ ጽፈት ቤት ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ከማድረጉም ባሻገር በቀጣይነት በየወረዳዎቹ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚየደርግ ገልጾአል ሲሉ ሊቀመንበሩ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡


 የሰላማዊ ሰልፉ ቅስቀሳ ቀጥሎ አምሽቷል የአዳር ሰላማዊ ሰልፉ ቅስቀሳ ምሽቱን ጭምር ተጠናክሮ እንደቀጠለ በሰማያዊ ፓርቲ በኩል የሰላማዊ ሰልፉ አስተባባሪ አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ አቶ ብርሃኑ እንደገለጹት የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ህዝብ በአገኘው አጋጣሚ ሁሉ የሰላማዊ ሰልፉን ቅስቀሳ እንዲያግዝ ባቀረበው ጥሪ መሰረት ህዝብ የቅስቀሳ ወረቀቶችን በማባዛት ዛሬ ህዳር 26/2007 ዓ.ም ምሽቱን ወረቀት ሲበትን ማምሸቱን ገልጸዋል፡፡ በዚህም መሰረት በአራት ኪሎ፣ ከስላሴ ጀምሮ በፒያሳና ማዕከላዊ ጀርባ በሚገኙ ሰፈሮች እንዲሁም በአዲሱ ገበያ ወረቀቶች እንደተበተኑ ገልጸዋል፡፡ ባለፉት ሁለት ቀናት የ9ኙ ፓርቲዎች ለቅስቀሳ ያዘጋጁት ስቲከር በተለያዩ የከተማይቱ አካባቢዎች እንደተለጠፉ መገለጹ ይታወቃል፡

Wednesday, December 3, 2014

ዘጠኙ ፓርቲዎች የህዳር 27 እና 28 የተቃውሞ ሰልፉን እንደሚያካሂዱ አስታወቁ።


ፓርቲዎቹ ይህን አስታወቁት ባወጡት መግለጫ ነው።

ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው ደብዳቤ ለመቀበል አሻፈረን ሲል የነበረው መስተዳድሩ በፖስታ የተላከለትን ደብዳቤ ከተቀበለ በሁዋላ ከህገመንግስቱና ከአዋጁ ቁጥር 3/1983 ተቃራኒ የሆኑ ምክንያቶችን በመደርደር ለሠላማዊ ሠልፉ ዕውቅና አልሰጠሁም ሲል ህዳር 22 ቀን  ድብዳቤ መጻፉን አስታውቀዋል፡፡
“በመሠረቱ መስተዳድሩ ጊዜና ቦታ እንዲቀየር አስተያየት ከማቅረብ ያለፈ ዕውቅና የመንፈግ መብት የሌለው በመሆኑ ትብብሩ የደብዳቤውን መልዕክት ያልተቀበለ መሆኑንና ሠልፉም በታቀደው ጊዜና ቦታ እንደሚደረግ ወስኖ የመልስ ደብዳቤ ” ማስገባቱንም ገልጸዋል።
የፓርቲዎቹ መግለጫ አያይዞም “ትግላችን ነጻነታችንና ክብራችን የማስመለስ በመሆኑ መንገዱም ፍጹም ሠላማዊ፣ ህጋዊና  ህገ- መንግሥታዊ ስለሆነ የህዳር 27/28  ሠላማዊ ሰልፍ የማይቀርና የማይቀርበት መሆኑን ለመግለጽና ነጻነትና ክብርን ወዳድ ኢትዮጵዊያንና የፖለቲካ ኃይሎች በሙሉ ለዚህ ታሪካዊ ዕለትና ሠላማዊ ትግል ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ጥሪያችንን እናቀርባለን።” ብሎአል።
ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተሰጠ መግለጫ
ኑ- ለነጻነታችንና ክብራችን ድምጻችንን በጋራ እናሰማ!
ከባርነትና ውርደት ለመላቀቅ ነውና በፍጹም አይቀርም፣ አይቀርም!
የ9ኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ ››በሚል መርህ የመጀመሪያ ዙር ዕቅዱን ለህዳር ወር አዘጋጅቶ ወደ እንቅስቃሴ ከገባ ሦስት ሣምንታትን አሳልፏል፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ያከናወናቸውን ተግባራትና የተጓዝንበትን መንገድ ለጉዳዩ ቀዳሚ ባለቤትና ለባለ ድርሻ አካላት ስናሳውቅ የነበረ በመሆኑ ያጋጠሙንን ችግሮች በመደጋገም ማሰልቸት አንሻም፡፡
ስለሆነም የዛሬው መግለጫችን በቀጣይ ለቀሩን ተግባራት የደረስንበትን ድምዳሜና ያወጣነው ዕቅድ በሚመለከት ይሆናል፡፡ በአጠቃላይ በእስከዛሬው እንቅስቃሴያችን ይዘን የተነሳነው ‹‹ ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› የሚለው መርህ ትክክልና ወቅታዊ፣ ያነሳናቸው ጥያቄዎችም አግባብ መሆናቸውን ያረጋገጥንበትና ገዢው ፓርቲ መድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ማለት ፍጻሜዬ ነው በሚል ከገባበት ከፍተኛ የፍርኃት ስሜትና ሥጋት ለተቃውሞ ጎራው እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ማለት በሚያስችል ሁኔታ በሩን ለመዝጋት የተዘጋጀ መሆኑን አገር ለ23 ዓመታት በላይ ካስተዳደረ መንግስታዊ ሥርዓት የማይጠበቅ መረን የለቀቀ የውንብድና ተግባራት ያረጋገጥንበት ነው፡፡ በመሆኑም ጥያቄዎቻችንን በህገ መንግስቱና በአገሪቱ ህጎች መሠረት ለመመለስ ቀርቶ ለመስማትና ለማንበብ ፍቃደኝነቱና የኃላፊነት ስሜቱ እየተሟጠጠ በመሆኑ የአፈናና ማስፈራራት መንገድን ብቸኛ አማራጭ አድርጎታል፡፡ ይህ በመሆኑም የራሱን መንግሥታዊ መዋቅር አሰራር ሥርዓት እንኳ በአደባባይ ለመቀበል እምቢተኛ መሆኑን በአደባባይ አረጋግጧል፡፡ ባለሥልጣናቱ በግንባር ያቀረብነውን ደብዳቤ ካለመቀበል አልፈው በመንግሥታዊው ፖስታ ቤት የተላከ ደብዳቤ ያለመቀበላቸው የሚያመለክተው ይህንና የደረስንበትን የመልካም አስተዳደር አዘቅት ነው፡፡
በተቃራኒው አበረታችና መልካም ዜናም አለ፡፡ ይህም ይህን የአፈናና ማስፈራትት አካሄድ አንቀበልም ያሉ ለነጻነታቸውና ክብራቸው፣የራሳቸው ብቻ ሣይሆን የመንግሥት መዋቅሮችና ባለሥልጣናትም ነጻነት መረጋገጥ አለበት ብለው የቱንም መስዋዕትነት ለመክፈል በቁርጠኝነት የተዘጋጁ በትብብሩ የታቀፉ ፓርቲዎች፣ አመራርና አባላት መኖራቸውና በትግሉ ለመቀጠል መወሰናቸው ነው፡፡ በዚሁ መሠረት ትብብሩ ለመጀመሪያ ዙር ዕቅዱ ማጠቃለያ የህዳር 27/28 የሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ደብዳቤ አመራሩ በግንባር ቢያቀርቡም አሻፈረኝ አንቀበልም ያሉት አሰራርና ባለሥልጣናት ከፖስታ ቤት እንዲቀበሉ ተደርጓል፡፡ለዚሁ ደብዳቤ መስተዳድሩ ከህገመንግስቱና ከአዋጁ (ቁጥር 3/1983) ተቃራኒ የሆኑ ምክንያቶችን በመደርደር ለሠላማዊ ሠልፉ ዕውቅና አልሰጠሁም ሲል በዛሬው ቀን (22/03/07) መልስ አድርሶናል፡፡ በመሠረቱ መስተዳድሩ ጊዜና ቦታ እንዲቀየር አስተያየት ከማቅረብ ያለፈ ዕውቅና የመንፈግ መብት የሌለው በመሆኑ ትብብሩ የደብዳቤውን መልዕክት ያልተቀበለ መሆኑንና ሠልፉም በታቀደው ጊዜና ቦታ እንደሚደረግ ወስኖ የመልስ ደብዳቤ አስገብቷል፡፡ በመሆኑም ለተግባራዊነቱ ዝግጅቱን በሙሉ አቅም ጀምሯል፤ ለዚህም የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ከአገር ውስጥና ከውጪ አጋርነታቸውን ገልጸዋል፤ አበረታተውናል፡፡ ይህም የያዝነው የትብብር የጋራ ዓላማችን ተቀባይነት፤ የኅብረትና አንድነትን ዋጋ አመላካች፣ ለማይቀረው ሠላማዊ ትግላችን ሥንቅ ነውና በታላቅ አክብሮት ተቀብለነዋል፡፡
ስለሆነም ይህ መግለጫ ትግላችን ነጻነታችንና ክብራችን የማስመለስ መንገዱም ፍጹም ሠላማዊ፣ ህጋዊና ህገ- መንግሥታዊ ስለሆነ የህዳር 27/28 ሠላማዊ ሰልፍ የማይቀርና የማይቀርበት መሆኑን ለመግለጽና ነጻነትና ክብርን ወዳድ ኢትዮጵዊያንና የፖለቲካ ኃይሎች በሙሉ ለዚህ ታሪካዊ ዕለትና ሠላማዊ ትግል ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
ነጻነታችንና ክብራችን ለማስመለስ ዋጋ ለመክፈል እንዘጋጅ፣ ያለመስዋዕትነት ድል የለምና!!

ዲሲ የሻማ ማብራት ፕሮግራም -አንዲት ሻማ እና አንዲት ደቂቃ ለቃሊቲ እና ቂሊንጦ


  • 14
     
    Share
አንዲት ሻማ እና አንዲት ደቂቃ ለቃሊቲ እና ቂሊንጦ
በአፋኙ እና አምባገነኑ የህውሃት ኢሃደግ ስርአት በሀሰት የአሸባሪነት ወንጀል ተፈርጀው በየእስር ቤቱ ተጥለው ለኢትዮጵያ ሀዝብ ፍትሃዊ ስርዓት ለማስገኘት ሲሉ መስዋትነት እየከፈሉ ላሉ የፖለቲካ እና የህሊና እስረኛ ወገኖቻችን የአጋርነት መግለጫ ወርሓዊ የሻማ ማብራት ፕሮግራም።
አገር እና ነጻነት ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ በዚህች አጭር የሻማ ማብራት ፕሮግራም ላይ በመገኘት እነዚህን ጀግና ዜጎቻችንን በምንኣብ ጉብኝት እንጠይቃቸው፣ ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ በተለይም ለምንኖርበት የአመሪካ መንግስት እነዚህ ዜጎቻችን የነጻነት ታጋዮች እንጂ ወንጀለኞች እንዳልሆኑ ምስክርነታችንን እናሰማ።
እሁድ ዲሰምበር 7, 2014
ከምሽቱ 6 ሰዐት
ሗይት ሃውስ ፊት ለፊት
3

TPLF shockingly admits failures in Ethiopia


 by: 

By Admasu Belay
TPLFSince it came to power over 20 years ago, the TPLF regime has always declared its achievements in Ethiopia’s political and economic sectors. Everybody knows the state media ETV and its daily nonstop propaganda of how much better Ethiopia has become over the years. Not only that, TPLF has been telling the international community about how it changed and transformed Ethiopia. So much so that it had even deceived some Bush and Obama adminstration officials to believe its lies.
But after over 20 years, the London-based Financial Times (FT) reported today that TPLF has finally admitted its massive failures in Ethiopia.
Shockingly, the TPLF admitted its disasterous policy of landlocking Ethiopia and its economic impact as well as the risk of another famine in Ethiopia.

Lessons for those who harp on TPLF’s non-existing “Economic Growth” and other “achievements”

“The document, seen by the Financial Times, is a sobering reminder of the risk of investing in one of Africa’s less developed nations. With gross domestic product per capita at less than $550 per year, Ethiopia is the poorest country yet to issue global bonds.
In the 108-page prospectus, issued ahead of its expected $1bn bond, Ethiopia tells investors they need to consider the potential resumption of the Eritrea-Ethiopia war, which ended in 2000, although it “does not anticipate future conflict”.
There is also the risk of famine, the “high level of poverty” and strained public finances, as well as the possible, if unlikely, blocking of the country’s only access to the sea through neighbouring Djibouti should relations between the two countries sour.
Addis Ababa, Ethiopia’s capital, also warns that it is ranked close to the bottom of the UN Human Development Index – 173rd out of 187 nations – and cautions about the possibility of political turmoil. “The next general election is due to take place in May 2015 and while the government expects these elections to be peaceful, there is a risk that political tension and unrest?.?.?.?may occur.” “
For the last two decades, this “F word,” was banned by Meles and all his TPLF disciples. In the past, If any foreign officials dared to use the words “famine” and “Ethiopia” in the same sentence, the wrath of TPLF’s “ministry of foreign affairs (mfa)” would attack and humiliate them with endless MFA press releases. Meles himself told Ethiopians to forget about famine and promised that even our poorer people “will eat three times a day very soon.” That promise was made in 1994! Ironically today, the TPLF government sent a document to international investors, admitting another ” risk of famine, the high level of poverty” in Ethiopia, according to the Financial Times.
Not only has Ethiopia lost most of its hard currency reserves but the “steadily depreciating exchange rate may adversely affect Ethiopia’s economy?,” according to the TPLF document
That is not all. TPLF also admitted the chance of “resumption” of the war with Eritrea and more unrest from “political turmoil” as well as bad relations with Djibouti causing the “blocking of the country’s only access to the sea.”
It is about time TPLF accepted its failures!


Regarding the 5th TPLF policy, everybody knows TPLF has failed. Soon it will admit this failure too.
In 1995, TPLF claimed its “ethnic federalism” system will empower tribes without dividing Ethiopians. But today, Ethiopia is the most ethnically divided country in the world. Ethnic hatred, propaganda and tensions today are the highest ever in history. Just like the 1990s Rwanda, tribalism has destroyed Ethiopian nationalism and humanity. Sooner or later, TPLF will be forced to admit its last and final failure.
Regardless, Today will go down in history as the day TPLF admitted that it has achieved almost nothing (other that a few tall buildings) since it removed the DERG regime in 1991. It has failed Ethiopia in every way possible. The only reason TPLF is still in power is because Ethiopians are peaceful people, unlike the warmongering and hate-filled TPLF.
For all those EPRDF ruling party supporters and TPLF footsoldiers worldwide, this must be the most embarasssing day. One single TPLF document has virtually dismissed over 20 years of ETV propaganda.