Thursday, August 7, 2014

በሳምንቱ ከወያኔ ከድተዋል ከተባሉ መኮንኖች ውስጥ ሶስቱ 'ዎው' ከተባለ የደቡብ ሱዳን ከተማ ተይዘዋል።

በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የቀድሞ ሰራዊት (የደርግ) መኮንኖች ማህበር መስርተዋል።


በዚህ ሳምንት ውስጥ ከሰማናቸው አበይት ጉዳዮች ውስጥ አንዱ በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ የቀድሞ የደርግ መኮንኖች ተሰባስበው ማህበር በኒቫዳ ውስጥ እንደመሰረቱ ሲሆን የማህበሩ ተግባር ሃገርን ነጻ ማውጣት ይሁን አሊያም የመረዳጃ እድር እስካሁን አልታወቀም።
የደርግ ወታደሮቹ /መኮንኖች በተለያዩ የጦር ወንጀሎች የተሳተፉ እና አምባገነኑን ደርግ ሲያገለግሉ የነበሩ ሲሆን አሁን ከ እነሱ ስልጣኑን የተረከበው ወያኔም ከደርጎች ባልተናነሰ መልኩ ከባባድ የጦር ወንጀሎችን በመፈጸም ላይ ይገኛል። ለዚሁም በኦጋዴን እና በጋምቤላ ክልል የፈጸመው እንዲሁም በምርጫ 97 የወያኔ ኮማንዶ ጦር አግአዚ የፈጸመው ወንጀል ተጠቃሽ ነው።
በጦር ወንጀለኝነት በቀይ ሽብር ተዋናይነት የሚፈረጁት የደርግ መኮንኖች በሃገሪቱ ታሪክ ውስጥ ለአንድነት እና የውጪ ጠላትን አሳፍሮ በመመለስ ረገድ ሚና የተጫወቱ ቢሆንም ከወያኔ እና ሻእቢያ ጋር በመመሳጠር በገንዘብ ተደልለው ሃገሪቷን አሁን ላለችበት የወያኔ አውሬያዊ መንጋጋ እንዳበቋት የማይካድ ሃቅ ነው። አሁን አሜሪካን አገር መሰረትን የሚሉት ማህበር ስራው እና ተግባሩ በግልጽ ባይታወቅም ለዳግም የስልታን ጥም እንዳያገለግል ይህ ትውልድ ስጋት ሊያድርበት ቢችልም ጎን ለጎን በሃገሪቱ ላይ ለሰሩት ወንጀል ለመጠየቅ መሰባሰባቸው አመቺ መሆኑን የሚገልጹ አልጠፉም ከዚህም ጋር ተያይዞ ለሃገራቸው አንድነት እና ነጻነት አስታውጾ በማድረግ ሕዝቡን ሊያስደስቱ እና ሊክሱት እንደሚችሉም የሚናገሩ አሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በሳምንቱ እንደተሰወሩ የታወቁት 16 የወያኔ መኮንኖች ውስጥ ሁለቱ በደብረዘይት እስር ቢት ከመንገድ ታፍነው እንደተወሰዱ የገለጽን ሲሆን ወደ ደቡብ ሱዳን ገብተዋል ተብልው ከተጠረጠሩት አስረአንዱ ውስጥ ሶስቱ ዎው ከሚባለው የደቡብ ሱዳን ግዛት ታድነው መያዛቸው ታውቋል። የወያኔ ወታደራዊ ደህንነቶች ባደረጉት ክትትል በተሽለ የዶላር ክፍያ ለደቡብ ሱዳን ተቃዋሚ በአሰልጣኝነት ለመቀጠር ከአዋዋይ ደላሎች ጋር የተያዙት ሻለቃ ደምለው ታደለ (ጎጄ) ፣ ሻምበል ደረሰወርቅ ነጬ እንዲሁም ሻምበል ዋበላ እንድሪስ ከደቡብ ሱዳን ዋው ግዛት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል። በአሁኑ ወቅት የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚ ታጣቂ ሃይሎች በጥሩ ክፍያ አሰልጣኝ መክንኖችን ለማግኘት እየጣሩ መሆኑ ታውቋል ። ቀሪዎቹን ለማግኘት ፍለጋው መቀጠሉ ታውቋል።
‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

ዜና ልማት፤ የአዲሳባ መስተዳድር፤ ”ለዜጎች የስራ እድል እየፈጠርኩ ነው” አለ። (ወጣቶች አንድ ሰው በሶስት ብር ጎርፍ ሲያሻግሩ ዋሉ)

ዜና ልማት፤ የአዲሳባ መስተዳድር፤ ”ለዜጎች የስራ እድል እየፈጠርኩ ነው” አለ። (ወጣቶች አንድ ሰው በሶስት ብር ጎርፍ ሲያሻግሩ ዋሉ) ትላንት በአዲሳባ የሚገኙ ወጣቶች አንድ ሰው በሶስት ብር ሂሳብ እያንከበከቡ በመሸከም መንግስት በፈጠረላቸው አስፋልታዊ ጎርፍ ላይ ሲያሻግሩ ዋሉ። ወጣቶቹ፤ ”መንግስታችን አስፋልት እንጂ የውሃ መተላለፊያ ያልሠራው አቅቶት ሳይሆን ለእኛ አስቦ በመሆኑ ምን ያህል ስራ ፈጣሪዎችን የሚያበረታታ መሆኑን የሚያሳይ ነው” ሲሉ ለመንግስታቸው ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል። ”መንግስት ለቀጣይ ክረምቶችም የውሃ ፍሳሻቸው ያልተዘጉ መንገዶችን ቱቧቸውን በመዝጋት የእኛን እንጀራ እንደሚከፍትልን ተስፋ እናደርጋለን” ሲሉም በስራ ፈጠራው ተጠቃሚ የሆኑ ወጣቶች ገልጸውልናል። የአዲሳባ አስተዳደር በበኩሉ፤ ዛሬ በአስፋልት ላይ የታየውን ጎርፍ በአምስት አመቱ የትራንስፎርሜሽን እቅድ በየቤቱ ለማስገባት እንደሚጥር ይሄም በርካታ ዜጎችን ለስራ ፈጠራ እንደሚያነሳሳ ገልጿል። እያልን እየቀለድን የትላንትናውን የአዲሳባ ቦሌ መንገድ ውሎ የምታስቃኝ ቪዲዮ እንካችሁ በታደሰ አለሙ አራዳ ሙዚቃ ታጅባለች።

On Monday we filmed a pitched street battle between Sudanese and Eritrean immigrants

There have been three serious rioting incidents in Calais in the last 24 hours. Last night 51 people were injured as immigrants attacked each other in the French port. Channel 4 News was there.
Image
On Monday we filmed a pitched street battle between Sudanese and Eritrean immigrants (above).
In a disused car park, by the river in Calais, the queue for the outdoor soup kitchen had over a thousand people in it. The bulk of the crowd were Eritreans and Sudanese men.
Hundreds of migrants are currently living in camps across Calais, trying to get access to Britain illegally. French police have tried to break up the camps, but the migrants say they have no option but to stay.
Last night, a group of local charities started serving rice and stew at 6pm but the immigrants started arriving at 4pm. By 7.30pm everyone was fed and the fighting started.
Initially a lone police car with two officers tried to control the situation. It only started to die down when the riot police arrived about 20 minutes later. Tears gas and rubber bullets were fired.

Turf war

We spoke to a number of Eritrean immigrants to try to find out what the fighting was actually about. We were told it is a turf war over which group has access to the lorry parks around the port where the trucks park over night before boarding the ferry for Dover.
The Sudanese are becoming the largest group of immigrants in Calais. We were told they had laid claim to one of the big over night lorry parks. They were only allowing Sudanese immigrants over the fence to try to hide inside the lorries.
The street brawls were battles for access to a car park, access to a lorry, access to the UK.

Article Tags

 

የአቶ በረከት የዛሬ ውሎ፤ ባለስልጣኑ ለደህነታቸው ጥበቃ ከሆስፒታል መልስ የጅዳን ቆንስላ ጽ/ቤት ዛሬ ጎበኙ


  • 2390
     
    Share
Bereket Simon weeping with his wife over Meles Zenawi's death
Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ
አቶ በረከት ስሞኦን ከሆስፒታል ቀጠሮአቸው መልስ ዛሬ የጃዳ ቆንስላ ጽ/ቤትን ለመጀመሪያ ግዜ መጎብኘታቸው ታውቋል ። አቶ በረከት እግር መንገዳቸውን ለዲፕሎማቱ ስለጤንነታቸው ሁኔታ ገለጻ እንዳደረጉ ከቆንስላው ጽ/ቤት የወጡ ምስጢራው መረጃዎቻችን ያመለክታሉ:: አቶ በረከት ስሞን በሼክ መሃመድ አላሙዲን የግል አውሮፕላን በሚስጠር ሳውዲ አረቢያ ለህክምና ከገቡ ወዲህ ለደህነታቸው ሲባል ሃገርቤት ካሉ የመንግስት ከፍተኛ ባለ ስልጣናተም ሆነ እዚህ ሳውዲ አረቢያ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት እምነት ጥሎባቸው ሃገር እና ህዝብን ወክለው ከተቀመጡ ዲፕሎማቶች በስልከም ሆነ በአካል ሳይገናኙ በድብቅ የልብ ህክምና ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወሳል ።
እኚሕ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ሳኡዲ አረብያ ጅዳ ለህክምና መግባታቸውን ተቃዋሚ ከሚሏቸው ከሶሻል ሚዲያዎች ያረጋገጡት የቆንስላው ዲፕሎማቶች አቶ በረከት ስሞኦን በፈጸሙት ስህተት ሲበሳጩ መስተዋላቸውን ምንጮቹ አክለው ገልጸዋል። የአቶ በረከት ስሞን ለህክምና ወደ ሳውዲ አረቢያ ጅዳ መግባትን ተከትሎ በሶሻል ሚድያ በመናፈሱ ባለስልጣኑ ህክማናቸውን በአግባቡ መከታተል እንዳልቻሉ በወቅቱ መዘገቡ ይታወሳል።
ከዛሬው የሆስፒታል ቀጠሮ መልስ በኋላ ጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት ጎራ ያሉት አቶ በረከት ለቆንስላው እና ለዲፕሎማቱ እውቅና ክበር ከመስጠት ሳይሆን ባለስልጣኑ ከሆስፒታል ከወጡ ወዲህ የተለያዩ ሆቴሎችን በመከራየት በድብቅ ሲያስታምሞቸው እና ድጋፍ ሲያደርጉላቸው የከረሙት ሼክ አላሙዲን ከሁለት ቀን በፊት ለስራ ጉዳይ ወደ አሜሪካ መብረራቸውን ተከትሎ የጤንነታቸው ሁኔታ እንብዛም አስተማማኝ ያልሆነው እኚሕ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ወደ ሃገር እስኪመለሱ ለደህነታቸው ጥበቃ እንዲያደርግላቸው የዘየዱት መላምት መሆኑ ከቆንስላው ጽ/ቤት የወጡ መረጃዎች ያስረዳሉ።
ባለስልጣኑ አርፈውበታል የተባለው ሆቴል ማማሻውን በማቅናት መረጃ ለማሰባሰብ ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም ።

የደመወዝ ጭማሪው የመንግሥት ሠራተኞችን ቅር አሰኝቷል ተባለ



በሰኔ ወር 2006 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋ የተደረገው የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ባለፈው ቅዳሜ መጠኑ ተገልጿል፡፡ ጭማሪው በመዘግየቱና እዚህ ግባ የሚባል ባለመሆን የመንግሥት ሠራተኞች ቅሬታቸውን ማሰማታቸውን ዘ ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል፡፡
በ2003 ዓ.ም. በተደረገው ጭማሪ 420 ብር የገባው የመንግሥት ሠራተኞች መነሻ ደመዝ 46.43 በመቶ ጭማሪ ተደርጎለት ከ582 ብር እስከ 700 ብር መስተካከሉ ባለፈው ቅዳሜ ይፋ ተደርጓል፡፡ መካከለኛ ተከፋይ የሆኑ የመንግሥት ሠራተኞች እስከ 36 በመቶ ጭማሪ የተደረገላቸው ሲሆን፣ ከፍተኛ ተከፋዮች ደግሞ በአማካይ 33 በመቶና ከዚያ በታች እንደሚያገኙ ይፋ ተደርጓል፡፡
የደመወዝ ጭማሪውን ይፋ ያደረጉት የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሩ አቶ ሱፍያን አህመድና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ምሥራቅ መኰንን፣ መንግሥት በአጠቃላይ ለጭማሪው በዓመት 10.3 ቢሊዮን ብር ያወጣል ብለዋል፡፡
‹‹መንግሥት ይህንን 10.3 ቢሊዮን ብር ለደመወዝ ሲያወጣ ፕሮጀክቶችን አጥፎ ነው፤›› ያሉት ሚኒስትሩ አቶ ሱፍያን፣ ‹‹ከደመወዝ ጭማሪው ውጪ በቀጣዩ ዓመት ለመንግሥት ሠራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት ይቀርባል፡፡ እንዲሁም የቤት ባለቤት የሚሆኑበት አማራጭ እየተጠና ነው፤›› ብለዋል፡፡
የደመወዝ ጭማሪው በሐምሌ ወር መጨረሻ ላይ ይደርሳል ተብሎ የነበረ ቢሆንም፣ ወጥ የሆነና በመላ አገሪቱ እስከ ወረዳ ድረስ ያሉ ሠራተኞች የደመወዝ ቀመርን የማዘጋጀቱና ወጥ የሆነ ደረጃ መፍጠሩ ጊዜ የሚወስድ በመሆኑ በነሐሴ ወር ደመወዝ ላይ እንደሚካተት ዶ/ር ምሥራቅ ገልጸዋል፡፡
አንዳንድ የመንግሥት ሠራተኞች፣ ‹‹ሠራተኛው ከኑሮ ውድነት ጋር የገባውን ግብግብ መንግሥት የተረዳው አይመስለንም፤›› በማለት ቅሬታቸውን እየገለጹ ነው፡፡ አንዳንዶች ደግሞ ‹‹የዋጋ ጭማሪው መንግሥት ካደረ ገው የደመወዝ ጭማሪ ይበልጣል፤›› በማለትም በምሬት ይገልጻሉ፡፡
ሚኒስትሩ አቶ ሱፍያን ለመንግሥት ሠራተኞች የትራንስፖርትና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞችን እንደሚያቀርቡ ቢገልጹም፣ ሠራተኞች ይህ ይሆናል የሚል ተስፋ የላቸውም፡፡
የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ግን መንግሥት የሚያወጣው 10.3 ቢሊዮን ብር በጣም ከፍተኛ ነው ይላሉ፡፡ አሁን ባለው የዋጋ ንረት ላይ ከዚህ በላይ ገንዘብ ወደ ገበያው ቢገባ የዋጋ ንረቱ ሊያገረሽ ይችላል ሲሉም ያስጠነቅቃሉ፡፡
በመሆኑም ሁሉንም ኅብረተሰብ ያገናዘበ ጭማሪ ነው በማለት ይከራከራሉ፡፡

አራዳ ፍርድ ቤት ዛሬ እንዲህ ሆነ


ዛሬ ከቀኑ 8፡00 በአራዳ ምድብ ችሎት ሐብታሙ አያሌው ዳንኤል ሺበሺና የሺዋስ አሰፋ እንደሚቀርቡ በመነገሩ ብዛት ያላቸው ሰዎች ቀደም ብለው በፍርድ ቤቱ ቅጥር ግቢ ተገኝተው ነበር፡፡ፖሊስ በፍርድ ቤቱ የተሰጠውን የቀጠሮ ሰዓት አክብሮ እስረኞቹን ማቅረብ በመቻሉ ላይ ብዙዎች ስጋት የነበራቸው ቢሆንም አልተሳሳቱም፡፡
መደበኛው የስራ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ከፍተኛ ታጣቂ ሃይል የፍርድ ቤቱን ቅጥረ ግቢ ተቆጣጠረው ከደቂቃዎች በኋላም አንድ ማንነቱን ቀደም ብለን ለማወቅ ያልቻልነው ቀጠን ያለ ወጣት እጆቹን ታስሮ ወደ ችሎት ገባ፡፡በኋላ ላይ ማረጋገጥ እንደቻልኩት ወጣቱ ዘላለም የሚባል ሲሆን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የማስተርስ መርሀ ግብር ተማሪ ነበር፡፡ፖሊስ በተመሳሳይ መልኩ እነ ሐብታሙን በያዘበት ዕለት በቁጥጥር ስር መዋሉን ለማወቅ ተችሏል፡ በመለጠቅም ዳንኤል ሺበሺ ሁለት እጆቹ በካቴና ታስረው ነጠላ ጫማ ፣ጥቁር ሱሪና ቱታ ጃኬት ተላብሶ ወደ ውስጥ ዘለቀ፡፡
ከጺሙ ማደግ በስተቀር ዳንኤል ፊትና አካል ላይ ምንም አይነት ለውጥ አይታይም፡፡ስሙን እየጠሩና በእጆቻቸው እያጨበጨቡ አድናቆታቸውን ለሚገልጹለት ሰዎች ጥርሱን ብልጭ እያደረገ አጸፌታውን ከመመለስ ውጪ ምንም አልተናገረም፡፡
የዳንኤልን ችሎት ለመከታተል ጋዜጠኞችና ቤተሰቦቹ ጥያቄ አቅርበው አይቻልም የሚል ተሰጥቷቸው የነበረ ቢሆንም ጉዳዩን የተመለከቱት ሴት ዳኛ ቤተሰቡ እንዲገባ በማዘዛቸው ባለቤቱ ችሎቱን ተከታትላለች፡፡
የዳንኤል ጉዳይ እየታየ በነበረበት ሰዓት የሺዋስ አሰፋን የያዘችው መኪና ፍርድ ቤት ቅጥር ግቢ ደረሰች፡፡ለደቂቃዎች ያህልም የሺዋስ በመኪናው ውስጥ እንዲቆይ ተደረገ፡፡ዳንኤልና ዘላለም እንደጨረሱና ግቢውን እንዲለቁ ከተደረጉ በኋላ የሺዋስ እንዲገባ ተደረገ፡፡ሙሉ ነጣ ያለ ቱታ ያጠለቀው የሺዋስ ግቢው ውስጥ እንደገባ ደመቅ ያለ ጭብጨባና በርታ የሚሉ መልእክቶች ጎረፉለት፡፡ፖሊሶች በጭብጨባውና በመልእክቶቹ ደስተኞች አለመሆናቸውን ቢገልጹም ከውስጥ ፈንቅለው የሚወጡ ስሜቶችን በቁጣና ማስፈራሪያ ሊያስቆሙ እንደማይችሉ የተረዱ ይመስሉ ነበር፡፡
የሺዋስ እንደሁልገዜው ዘና ያለና የተረጋጋ ነው፡፡ፈገግታውን በመርጨትና ሰላምታ በመለገስ የታሰሩ እጆቹን እያወዛዘወዘ ችሎት ገባ፡፡የሺዋስ የውስጥ ጉዳዩን ከውኖ እንደጨረሰም በተመሳሳይ የወዳጆቹና የትግል አጋሮቹ ጭብጨባና አድናቆት ታጅቦ ግቢውን ለቀቀ፡፡
በመጨረሻም ሐብታሙ አያሌው ወደ ውስጥ እንዲገባ ተደረገ፣ ሐብታሙ እግሮቹ ግቢውን እንደረገጡ ተሰብስበው ለጠበቁት ሰዎች ጥልቅ ፈገግታውን በመለገስ ሰላምታ አቅርቧል፡፡‹‹እንወድሃለን፣አይዞን››የሚሉ ቃላት ከደማቅ ጭብጨባ ጋር በግቢው አስተጋቡ፣ አጃቢዎቹም ፈጠን እንዲል እየወተወቱት ችሎት አስገቡት፡፡
ከወጣት ዘላለም በስተቀር በዕለቱ ችሎት ጠበቃ ተማምና ገበየሁ ታሳሪዎቹን ወክለው ቀርበዋል፡፡ሀብታሙ በመጣበት አጀብ ግቢውን እንዲለቅ ከተደረገ በኋላ ሁለቱ ጠበቆች ‹‹ተለዋጭ ቀጠሮ ለነሀሴ 26/2006 መሰጠቱን አውስተዋል፡፡ፖሊስ በዛሬው ችሎት በተጠርጣሪዎቹ ላይ ምንም አይነት ማስረጃ አለማቅረቡን መረጃ ለማሰባሰብ እንዲረዳው የጠየቀው ቀን እንደተሰጠውም አብራርተዋል፡

የሕዳሴ አብዮቱን ለመቀልበስ የተደረገ ነው” ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ



የወያኔ መንግስት ሕገመንግሥታዊሥርዓቱን በአመጽ ለመናድ…» በሚል ክስ በአምስት መጽሔቶች እና አንድ ጋዜጣ ላይ ላይ በሕዝብ ላይ ሽብርተኝነት የሚነዙ ሽብርተኛ ናቸው ብሎ ከስ ማቅረቡ ይታወቃል ይህንንም ተከትሎ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የፋክት መጽሔት ባልደረባ እንዲህ ይላል ይህ ክስ “የሕዳሴ አብዮቱን ለመቀልበስ የተደረገ ነው”
ክሱን በሚመለከት የደረሰን ነገር የለም። ጉዳዩን ከመንግስት መገናኛ ብዙሐን ነው የሰማነው። ይህ ለምን እንደሆነ በራሱ ግራ የሚያጋባ ነው። ምክንያቱም በተለመደው አሰራር ክስ ሲመሰረት ተከሳሹ መጥሪያ ደርሶት ቃል እንዲሰጥ ይደረጋል። 
ፍትሕ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሰጠው መግለጫ ከፈረሱ ጋሪው የቀደመበት ሁኔታ ነው መሆኑን ነው ያሳየን። 
ለምን ይሆን ተብሎ ለሚነሳው ጥያቄ መንግስት ጋዜጠኞችን ከሀገር ማባረር ስልት አድርጐት ስለያዘው ከተከሰሱት መጽሔቶችና ጋዜጦች መካከል የተባለውን የክስ መግለጫ ሰምተው ቀድመው ከሀገር እንዲሸሹ ስለተፈለገ ነው።


የተነገረው የክስ መግለጫ በእኛ ሥራ ላይ በቀጣይ የሚያስከትለው ነገር የለም። 
ዞሮ ዞሮ ከዚህ ክስ በስተጀርባ ያለው ፍርሀት እየተቃረበ የመጣውን በፋክት መጽሔት በተከታታይ እየቀረበ ያለውን “የሕዳሴው አብዮት”ን ነው። መግለጫውም ይህን የህዳሴውን አብዮት ለመቀልበስ የተደረገ ሙከራ ነው።
የሕግ ክፍተት በመኖሩ የተፈፀመ ተደርጐ መወሰድ የለበትም። በፋክት ላይ የተዘገቡት የሐሰት ወሬዎች አይደሉም። 
እርምጃው ፖለቲካዊ ነው። ስርዓቱ በጣም ስለተደናገጠ እየተፈረካከሰ ስለሆነ መቃብሩ አፋፍ ላይ ስለቆመ የመጨረሻው ግብአት መሬቱን የሚያውጀውን የሕዳሴ አብዮትን ለመቀልበስ የተደረገ ሙከራ ነው። ይህ የአፈና ተግባር ነው