Sunday, November 3, 2013

የሸንጎ ውሎ “ስልብ ጃንደረባ በጌታው ብልት ይፎክራል”



በሸንጎ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካይ አቶ አክሊሉ እና በአቶ ኤፍሬም ማዴቦ የግንቦት 7 ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ መካከል የተደረገውን ረጅም ውይይት በአዲስ ድምጽ ሬድዮ ስከታተል ዋልኩ።

 ሸንጎ የበርካታ አንጋፋ የፖለቲካ ድርጅቶች ስብስብ እንደሆነ ተወካዩ የገለጹ ሲሆን እንደ (መ. ኢ. ሶ. ን) አይነት ግማሽ ምዕተ ዓመት እድሜ ያላቸው ድርጅቶች የሸንጎው አባል ናቸው።

አምርረው ግንቦት 7 በኤርትራ በኩል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ያወግዛሉ፣ ይነቅፋሉ። ከፕሮግራሙ መሪ ጋዜጠኛ አበበ በለውና ከአድማጮች ለሚጠየቁ ጥያቄዎች የግንቦት 7ቱ ተወካይ አቶ ኤፍሬም ማዴቦ በተቻለ መጠን ቀጥተኛ መልሶች ለመመለስ ጥረት ሲያደርጉ አስተውያለው።

 ይሁንና የሸንጎው ተወካይ አቶ አክሊሉ በአብዛኛው የድርጅታቸውን አቋም በተመለከተ ሲጠየቁ ስለ ሰማያዊ ፓርቲ፣ ስለ አንድነት ፓርቲ፣ ስለ መድረክ እና መኢህአድ ማውራት ይቀናቸው ነበር።

እነዚህ የፖለቲካ ድርጅቶች ውክልና የሰጧቸው አይመስለኝም ታድያ ምነው የራሳቸው ፓርቲ እንደሌለ አድርገው ስለሌሎች ማውራት መምረጣቸው? “ስልብ ጃንደረባ በጌታው ብልት ይፎክራል” ይሏል ይሄው ነው።
 November 2, 2013 ሶስና፣ ከዋሽንግቶን ዲሲ

No comments:

Post a Comment