የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ ወጣት ክንፍ ድርጅት(ኢወክንድ) የተሰጠ መግለጫ
የሳዑዲ አረቢያ መንግስት በወገኖቻችን ላይ እያደረሰ ያለውን ኢሰብአዊ ግድያና ወከባ እናወግዛለን
አገራችን ዜጎቿ በፀረ-ኢትዮጵያው የወያኔ መንጋ እየተዋከቡ በሀገራቸው የመኖር ነፃነት አጥተው በስደት ዓለም እጅግ
አሰቃቂ የሆነ ግፍ እየተፈፀመባቸው ይገኛሉ። ሰሞኑን በሳኡዲ አረቢያ ውስጥ በፅንፈኛ ሃይማኖት የነሆለሉ እና በነዳጅ
ድፍድፍ በተሳከሩ መሪዎች ሰብአዊ መብታቸው እየተረገጠና በአደባባይ ቀጥቅጠው በግፍ የገደሏቸውንም በሬሳቸው ላይ
ቆመው ሲያላግጡ ስናይ ልባችን እጅጉን ይደማል። አምርረንም እናወግዛለን።
ወያኔም ሆነ የሳኡዲ ገዥወች በውጭ ሃይል የተተከሉ ናቸውና ግብራቸው ሁሉ ልክ እንደፈጣሪዎቻቸው ስረ መሰረታቸው
ሁከት መፍጠርና ዘረኝነት መሆኑ የሚገርም ባይሆንም፣ ይህ ራቁቱን የወጣ አረመኔ ድርጊታቸው ግን ሰላም ወዳድ የሆኑ
ሁሉ በጥብቅ ሊያወግዙት ይገባል ። እንዲሁም በዓለም ዙሪያ እየተገፋ ያለውን ፀረ-ኢትዮጵያዊ ወከባ የትኞቹ ክፍሎች
ከኻላ እንዳሉበትም አይኑን ለከፈተ ሁሉ ግልጽ ነው። አንድን አገር ማጥፋት የፈለገ መጀመሪያ የስነ-ልቡና ጦርነት
የሚከፍተው የዜግነት ክብርን ማሳጣት ላይ እነደሚሆን በታሪክ የታየ ነውና።
ሰሞኑን በኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች አንድነት ኮሚቴ፣ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት እንዳስቀመጠው፣ የፊሊፒን
መንግስት ዜጎቹን ወደ ሳኡዲ እንዳይሄዱ አግዷል። ይህም የሆነበት ቢያንስ የዜጎቹን ክብር የሚያስጠብቅ መንግስት ስላላት
ነው። ይህ የወገን ፍዳ ማስቆም የሚቻለው በአቤቱታ ሳይሆን መንስኤ የሆነውን ዘረኛ ቡድን በኢትዮጵያ የፖለቲካ
ህይወት ሲያጣና በተባበረ ሕዝባዊ አመፅ ግብአተ መሬት ሲገባ ብቻ ነው።
ዲፕሎማሲ በመሳሪያ አፈሙዝ ላይ የተንጠለጠለ ትርጉም የለሽ ክስተት እየሆነ በመጣበት በአሁኑ ዓለም፣ በልመና የሚገኝ
ክብር የለም። የአንዲት አገር ዜጎች ወይም አንድ ትውልድ በታሪክ የሚደርስበትን ሃላፊነት ለመወጣት የሚከፈለውን
መስዋዕትነት ሁሉ ከፍሎ መብቱንና ዜግነቱን ሊያስከብረ ግድ ይላል። ኢ-ወክንድም ሆነ እናት ድርጅቱ ኢሕአፓ አገር
እናድን እያለ በወገኑ ስቃይ፣ የመብትና ዜግነት መረገጥ ለሚቆጭ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የትግል ጥሪውን እያስተጋባ ነው።
ብሄራዊ ክብራችንን በትግላችን እናስከብራለን!!
Tel : 202-291-5832 5309 Georgia Ave. NW 2
nd
Fl. Washington DC 20011
e-mail: eprpylnew @gmail.com Website: www.eprpyl.com
No comments:
Post a Comment