‹‹ችግሩ ያን ያህል እንደሚባለው አይደለም፡፡የማህበረሰብ ገጾች ነገሩን አጋነው አቅርበዋል››አምባሳደር ዲና መፍቲ
የሳውዲ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ‹‹ተፈጸመ የሚባለው ድርጊት እንደሚባለው አይደለም ተጋኗል ››አሉ
ባለስልጣኑ ከላይ የተጠቀሰውን አስተያየት የሰጡት ለሸገር ሬዲዮ ጣብያ ነው፡፡የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንድ ባልደረባም ለኢሳት ‹‹የማህበረሰብ ገጾች እንደሚሉት ችግሩ ያን ያህል የተጋነነ አይደለም››ማለታቸውም ተሰምቷል፡፡
አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በውጪ ጉዳይ ሚኒስትርነት የሾሟቸው ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም በአፍአ የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳዮችን የመከታተል ሃላፊነት የተጣለባቸው ቢሆንም ሰውዬው የሳውዲ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ መሆናቸውን በቃል አቀባያቸው በኩል አስመስክረዋል፡፡
በሳውዲ ብዙ ሺህ ኢትዮጵያዊያን ስቃይ፣እንግልት፣መደፈር፣እስራት፣ግርፋትና ግድያ እየተፈጸመባቸው ለመሆኑ መረጃዎች፣የምስል ማስረጃዎችና ዘገባዎች በመጠቆም ላይ የሚገኙ ቢሆንም ቴዎድሮስን በመወከል ከሸገር ሬዲዮ ለቀረበላቸው ጥያቄ አምባሳደር ዲና መፍቲ ‹‹ችግሩ ያን ያህል እንደሚባለው አይደለም፡፡የማህበረሰብ ገጾች ነገሩን አጋነው አቅርበዋል››ብለዋል፡፡
በዲና መፍቲ ቃለ ምልልስ የተደናገጡት የኢሳት ጋዜጠኞች ወደ ሳውዲ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር በመደወል ማብራሪያ ቢጠይቁም ዲናን ማግኘት አልቻሉም፡፡አቶ መቻል ታከለ ግን ለኢሳት ‹‹ጉዳዮ የተባለውን ያህል የከፋ አይደለም የማህበረሰብ ገጾች እንደሚያራግቡት አለመሆኑን ተረድተናል››ብለዋል፡፡
የውጪ ጉዳይ ባልደረባው እስካሁን ሁለት ሰዎች ነው የተገደሉት ማለታቸውም ቢሮውን አስገምቷል፡፡ዜጎቹ በውጪ አገራት ስቃይና እንግልት ሲደርስባቸው ጥቃት አድራሾቹን የሚከላከል አስተያየት የሚሰጥንና እንደለመደው በቁጥር ለመጫወት የሚደፍርን ቢሮ እንዴት የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ በማለት መጥራት ይቻላል፡፡
via-EthiopianReview

No comments:
Post a Comment