Monday, July 7, 2014

ከአምቦዩንቨርስቲ‬ ለዘላለም የተፃፈው አስገራሚ ‪#‎ደብዳቤ‬!

መንግስታዊው የአምቦ ዩንቨርስቲ በዩንቨርስቲው የህግ መምህር የነበረውን አሁን በእስር ላይ የሚገኘውን የዞን-፱ ጦማሪ ‪#‎ዘላለምክብረት‬ ን በሚከተለው መልኩ በተፃፈ ደብዳቤ ከስራ አስናብቶታል "በግንቦት 13 ቀን 2006 ዓ.ም በስራ ገበታዎ ባለመገኘተዎ ግንቦት 14 ቀን 2006 ዓ.ም የመጀመሪያ የጥሪ ማስታወቂያ መውጣቱንና በቁጥር አዩ/መ403/1/15/06 ግንቦት 26 በወጣ ማስታወቂያ ለሁለተኛ ጊዜ ጥሪ የተደረገልዎ መሆኑ ይታወቃል።
ስለዚህ በተሰጠዎ የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርበው ሪፖርት ስላላደረጉ ከተጠቀሰው ቀን( 26/10/06) ጀምሮ ከስራ የተሰናበቱ መሆኑን እየገለፅን፣ በእጅዎ የሚገኘውን የዩንቨርስቲው ንብረት ቀርበው እንዲያስረክቡ እናሳስባለን።"
ይገርማል፣ያሳዝናል እንዲሁም ያስተዛዝባል!!
የመንግስት ዩንቨርስቲዎች በኢህአዴግ ድርጅታዊ መዋቀር ውስጥ ያልወደቁ ይመስል፤በአምቦ ዩንቨርስቲ መምህር የነበረው ዘላለም ሲታሰር ዩንቨርስቲው እውቅና የሌለው ይመስል እንዲህ አይነት አስተዛዛቢ ማስታወቂያ ማውጣት ምን ይባላል!?
በጨለማ ክፍል ታስሮ በአግባቡ በቤተሰብና በህግ አማካሪው እንዳይጠየቅ የተደረገውን የዘላለም ሁኔታ ዩንቨርስቲው አላውቅም ለማለት ነው "ንብረት ቀርበው እንዲያስረክቡ እናሳስባለን" ብሎ መፃፍ ያስፈለገው።
ሌላው የገረመኝ "በግንቦት 13 ቀን 2006 ዓ.ም በስራ ገበታዎ ባለመገኘተዎ ግንቦት 14 ቀን 2006 ዓ.ም የመጀመሪያ የጥሪ ማስታወቂያ መውጣቱን..." በየትኛውም የመንግስት ተቋምም ሆነ የግል ለ1 ቀን ከስራ ገበታው ላልተገኘ/ች ግለሰብ እንዲህ አይነት ፈጣን ማስታወቂያ ሲወጣ አይቸም ሰምቸም አላውቅ።
በአጠቃላይ የዩንቨርስቲው ደብዳቤ ይዘት ከደህንነት መስሪያ ቤት ለዩንቨርስቲው የተላከ ለወንጀላቸው ቂላቂል የህግ ሽፋን ለመስጠት ብሎም በዘላለም የግፍ እስር ላይ በመዘባበት ለመሳልቅ የተደገ የእብሪት ተግባር ነው!!
#ከአምቦዩንቨርስቲ ለዘላለም የተፃፈው አስገራሚ #ደብዳቤ!

መንግስታዊው የአምቦ ዩንቨርስቲ በዩንቨርስቲው የህግ መምህር የነበረውን አሁን በእስር ላይ የሚገኘውን የዞን-፱ ጦማሪ #ዘላለምክብረት ን በሚከተለው መልኩ በተፃፈ ደብዳቤ ከስራ አስናብቶታል "በግንቦት 13 ቀን 2006 ዓ.ም በስራ ገበታዎ ባለመገኘተዎ ግንቦት 14 ቀን 2006 ዓ.ም የመጀመሪያ የጥሪ ማስታወቂያ መውጣቱንና በቁጥር አዩ/መ403/1/15/06 ግንቦት 26 በወጣ ማስታወቂያ ለሁለተኛ ጊዜ ጥሪ የተደረገልዎ መሆኑ ይታወቃል።
ስለዚህ በተሰጠዎ የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርበው ሪፖርት ስላላደረጉ ከተጠቀሰው ቀን( 26/10/06) ጀምሮ ከስራ የተሰናበቱ መሆኑን እየገለፅን፣ በእጅዎ የሚገኘውን የዩንቨርስቲው ንብረት ቀርበው እንዲያስረክቡ እናሳስባለን።"

ይገርማል፣ያሳዝናል እንዲሁም ያስተዛዝባል!!

የመንግስት ዩንቨርስቲዎች በኢህአዴግ ድርጅታዊ መዋቀር ውስጥ ያልወደቁ ይመስል፤በአምቦ ዩንቨርስቲ መምህር የነበረው ዘላለም ሲታሰር ዩንቨርስቲው እውቅና የሌለው ይመስል እንዲህ አይነት አስተዛዛቢ ማስታወቂያ ማውጣት ምን ይባላል!? 
በጨለማ ክፍል ታስሮ በአግባቡ በቤተሰብና በህግ አማካሪው እንዳይጠየቅ የተደረገውን የዘላለም ሁኔታ ዩንቨርስቲው አላውቅም ለማለት ነው "ንብረት ቀርበው እንዲያስረክቡ እናሳስባለን" ብሎ መፃፍ ያስፈለገው።
ሌላው የገረመኝ "በግንቦት 13 ቀን 2006 ዓ.ም በስራ ገበታዎ ባለመገኘተዎ ግንቦት 14 ቀን 2006 ዓ.ም የመጀመሪያ የጥሪ ማስታወቂያ መውጣቱን..." በየትኛውም የመንግስት ተቋምም ሆነ የግል ለ1 ቀን ከስራ ገበታው ላልተገኘ/ች ግለሰብ እንዲህ አይነት ፈጣን ማስታወቂያ ሲወጣ አይቸም ሰምቸም አላውቅ።
በአጠቃላይ የዩንቨርስቲው ደብዳቤ ይዘት ከደህንነት መስሪያ ቤት ለዩንቨርስቲው የተላከ ለወንጀላቸው ቂላቂል የህግ ሽፋን ለመስጠት ብሎም በዘላለም የግፍ እስር ላይ በመዘባበት ለመሳልቅ የተደገ የእብሪት ተግባር ነው!!

No comments:

Post a Comment