ጥቅምት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምክር ቤቱ ነገ በሚያደርገው ስብሰባ ለመንግስት ስልጣን አስጊ ሆኗል ባለው የሽብርተኝነት አደጋ ላይ እንደሚመክር ለማወቅ ተችሎአል።
ምክር ቤቱ ከፍተኛ ስጋት ደቅነዋል ባላቸው ግንቦት7 እና የኤርትራ መንግስት ላይ ተነጋግሮ የመፍትሄ እርምጃ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ምክር ቤቱ በሳውዲ አረቢያ በካምፕ ውስጥ ስላሉ ኢትዮጵያም ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት 4 ሺ 321 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መታሰራቸውን ሪፖርት እንደተደረገለት ለማወቅ ተችሎአል።
የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ከፍተኛ የአመራርአባላትን ላይ ታቅዶ የነበረ የመግደል የተደረገው ሙከራ ከሸፈ። በጠቅላይ ሚንስትር ተብየው ሃይለማሪያም ደሳለኝ እውቅናና ትእዛዝ የግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይል ታጋዮች በሚገኙበት ቦታ ድረስ በመሄድ አመራሩን ለመግደል ሙከራ ቢደረግም ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት በሕዝባዊ ሃይሉ መረጃና ደህንነት ክፍል ከፍተኛ ክትትል ሙከራው መክሸፉን ሕዝባዊ ሃይሉ ገለጸ። ይህ ልዩ ትእዛዝ ጥቅምት 30 2006 ዓ/ም ተፈጻሚ እንዲሆን እቅድ የነበረ ቢሆንም ሕዝባዊ ሃይሉ ጥቅምት 27 2006 ዓ/ም ሊያከሽፈው ችሏል።
ወደ ጅጅጋ መግባትም መውጣትም አይቻልም ተባለ ጥቅምት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በሶማሊ ክልል ዋና ከተማ ጅጅጋ የሚታየው ሁኔታ እስከ ዛሬ ከታዩት ሁሉ የተለየ ነው ይላሉ ነዋሪዎች። ከሌሎች አካባቢዎች በመሄድ ወደ ከተማው መግባት ወይም ከከተማው በመውጣት ወደ ሌሎች አካባቢዎች መሄድ የተከለከለ ነው ይላሉ።
የመከላከያ ሰራዊት አባላት በከተማው በብዛት በመገኘት ቤት ለቤት የሚያካሂዱት ፍተሻ ለነዋሪዎች ጭንቀትን ፈጥሮባቸዋል። በክልሉ ፕሬዚዳንት ትእዛዝ በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች ላፕቶፕ ኮምፒዩተራቸውን ተቀምተዋል። ባለስልጣናቱ ይህን እርምጃ ለመውሰድ ለምን እንደፈለጉ ባይናገሩም የከተማዋ ነዋሪዎች ግን፣ መንግስት መረጃ አገኛለሁ በሚል መውሰዱን ይናገራሉ።
አልሸባብ ጥቃት ሊፈጽም ይችላል በማለት የጸረ ሽብር ግብረሀይል መግለጫ ካወጣ በሁዋላ፣ የክልሉ ፕሬዚዳንት በሰጠው ትእዛዝ ይህንን ሰበብ አድርጎ ምንም አይነት እቃ ከጅጅጋ እንዳይወጣ ወይም ወደ ጅጅጋ እንዳይገባ ለማድረግ ከፍተኛ ፍተሻ እየተካሄደ ነው።
የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጭ ግንባር በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እየደረሰ ያለውን ሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲሁም በአልሸባብ ስም በክልሉ ነዋሪዎች ላይ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ አውግዟል።
ጅጅጋ በመጪዎቹ ሳምንታት የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን እንደምታከብር ይታወቃል።
No comments:
Post a Comment