በአዲስ አበባ ስኬታማ ሰላማዊ ተቃውሞዎችን በማድረግ ጉዞውን የጀመረው ሰማያዊ ፓርቲ በተለያዩ ክፍላተ ሃገራት ያሉ መዋቅሮቹነ በመገምገምና አደረጃጀታቸውን በማጠናከር ላይ ይገኛል፡፡
በዚህም መሰረት ባለፈው እሁድ በ24/2/06 በሰሜን ሸዋ የሚገኙ ወረዳዎችን በደብረ ብርሃን ከተማ በመገኘት የገመገመ ሲሆን
በእለቱም የፓርቲው የአደረጃጀት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ጌታነህ ባልቻ በቦታው በመገኘት ስለ ፓረቲው አጠቃላይ ሁኔታና ጉዞ ገለፃ
በማድረግ ስኬታማ ውይይት ከአባላት ጋር አካሂደዋል፡፡
በተመሳሳይም ከዛሬ ማክሰኞ 26/2/2006 አ/ም ጀምሮ ለ3 ቀናት በአርባ ምንጭ በወላይታ በአዋሳና ሆሳእና ከተሞችላይ ከአባላት ጋር ውይይት የሚደረግ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም በሌሎች ከተሞች ላይ ውይይቱ የሚቀጥል መሆኑ ታውቋል፡፡
No comments:
Post a Comment