Sunday, November 3, 2013

ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት አመታት ከ400 ሺ በላይ ዜጎቿን በስደት አጣች




November 2, 2013
ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ በህዝብና በአገር ላይ የሚፈጽመዉን ግፍና በደል በመሸሽ ከኢትዮጵያን እየጣለ የሚሰደደዉ ሰዉ ቁጥር ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ መምጣቱን ከአገር ዉስጥና ከአለም አቀፍ ተቋሞች የሚመጡ መራዎች ጠቆሙ። በቅርቡ ከወያኔዉ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ባለፉት 2 ዓመታት ዉስጥ ብቻ ከ400 ሺ በላይ ዜጎች ኢትዮጵያን ለቅቀዉ መሰደዳቸዉ ታዉቋል። ይህንን እጅግ በጣም አሳሳቢ መረጃ ይፋ ያደረገዉ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ጨምሮ እንዳስረዳዉ ይህ ቁጥር የወያኔን ጫናና መከራ ላለማየት በሀጋዊ መንግድ አገር እየለቀቁ የሚሄዱትን ሰዎች እንደማይጨምር ታዉቋል።

ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ ኢትዮጵያዉያን ከደርግ ዘመን ጀምሮ በጎንደር፤ በሐረር፤ በወለጋ፤ በባሌና በሲዳሞ በኩል አገር እየጣሉ እንደሚሰደዱ የታወቀ ሲሆን ወያኔ አትዮጵያን ከተቆጣጠረ በኋላ የአገሪቱ የፖለቲካና የኤኮኖሚ ሁኔታ ይሻሻላል በሚል ብዙዎች ኢትዮጵያን እየለቀቀ የሚሰደደዉ ሰዉ ቁጥር ይቀንሳል የሚል እምነት ነበራቸዉ። ሆኖም ወያኔ ብዙም ሳይቆይ የዘረኝነት ፖሊሲዉን ተግባራዊ ማድረግ በመጀመሩ የስደተኘዉ ቁጥር ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መምጣቱ ታዉቋል። በደርግ ዘመን በብዛት ይሰደድ የነበረዉ የቀይ ሽብር ብትር ያርፍበት የነበረዉ ወጣቱና ምሁሩ ሲሆን ዛሬ በወያኔ ዘመን ግን ወንድና ሴት ሳይለይ ወጣቱ፤ተማሪዉ፤ ምሁሩ ፤ሰራተኛዉና ገበሬዉ አንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ። የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ የአለማችን አምስተኛዉ ታዳጊ ኤኮኖሚ ነዉ እያሉ ወያኔና አፈ ቀላጤዎቹ ቢናገሩም ዛሬም ኢትዮጵያ አፍሪካ ዉስጥ ከፍተኛ ህዝብ የሚሰደድባት አገር አንደሆነችና በተለይ በከፍተኛ ደረጃ የተማረዉን የሰዉ ኃይል በተመለከተ ኢትዮጵያ ምሁሮቻቸዉን በአዉሮፓና በአሜሪካ ከተቀሙ ታዳጊ አገሮች ግንባር ቀደሟ እንደሆነች አለም አቀፍ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
በተለይ የወያኔ አገዛዝ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ ስራ ፍለጋ ወደ ፋርስ በህረሰላጤ አገሮችና ወደ መካከለኛዉ ምስራቅኢ አገሮች የሚሄዱ ኢትዮጵያዉያን ሴቶች ቁጥር በከፈተኛ ፍጥነት ማደጉ የሚታወቅ ሲሆን፤ ይህንኑ ተከትሎ አያሌ የዜጎች ወደነዚህ አገሮች የሚያደርጉትን ፍልሰት የሚያፋጥኑ ድርጅቶች አዲስ አበባን ማጨናነቃቸዉ ይታወቀቃል። ወያኔ አገዛዝም ቢሆን በዚህ የሰዉ ልጆች ንግድ ተጠቃሚ ስለሆነ ስራ ፈላጊዎች ከመሰደድ ይልቅ አገር ዉስጥ ስራ እንዲያገኙ ያደረገዉ ምንም ነገር የለም። አርብ አገር የሚሄዱ ኢትዮጵያዉያን ሴቶች የሚደርስባቸዉ ከፈተኛ ችግር፤ ሞትና እንግልት በአለም አቀፍ ሜድያዎች ጭምር በመዘገቡ ወያኔ በቅርቡ ለስራ በሚል ወደ ውጪ በሚጓዙት ላይ እገዳ መጣሉ ይታወቃል።
የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ስምሪት ማስፋፊያ ዳይሬክተር አቶ አበበ ሀይሌ እንዳሉት ፥ እገዳው ከተጣለባቸው ሀገራት መካከል ሊባኖስ ፣ ኳታር ፣ ሳውዲ አረብያ ፣ ኩየት ፣ የመን ፣ ሱዳንና ደቡብ አፍሪካ ይገኙበታል።በእገዳው መሰረት ካሁን ቀደም ቪዛ ያገኙትን ጨምሮ ቪዛ ለማግኘት እየተጣጣሩ ያሉትም ቢሆን ወደ ሀገራቱ መጓዝ አይችሉም።፤ እገዳው በቤት ሰራተኝነት ተቀጥሮ ለመስራት ከሚደረጉት ጉዞዎች ባሻገር አለም አቀፋዊ ተቀባይነት ባላቸው ሙያዎች ላይ የሚደረጉ ጉዞዎችን እንደማይመለክትም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። በመንገድ የቀረው ቀርቶ ወደ መጨረሻ መዳረሻ ሀገር የገቡት ዜጎች እጣ ፈንታ አብዛኛውን ጊዜ ስቃይና እንግልት ቢሆንም ፥ ዛሬም በዚያ የሞት ጎዳና ላይ የሚተሙ ዜጎች ቁጥር ሊቀንስ አልቻለም።

No comments:

Post a Comment