በአፍቃሬ ወያኔነቷ የምትታወቀው ድምጻዊት ሃመልማል አባተ አዲስ አልበሟን ለማስመረቅና የተለየያዩ ኮንሰርቶችን ለመሥራት ወደሰሜን አሜሪካመጥታ የነበረ ቢሆንም በደረሰባት ቦይኮት በተመልካች እጦትና በፕሮሞተሮች መጥፋት አፍራ ወደ አዲስ አበባ መመለሷ ታወቀ።
ሃመልማል በወያኔ/ኢህአዴግ እየተረገጠ ያለውን ሰፊውን ሕዝብን ክዳ ለመሬት ቀሚው፣ ለመሬት ሻጩ፣ ለበዝባዡ፣ ለጨፍጫፊውና ለሰብአዊ መብትረጋጩ ወያኔ ተቆርቋሪ ሆና በመቅረቧ ከጥቂት ዓመታት በፊት` በጀርመን ሃገር የሙዚቃ ኮንሰርት አዘጋጅታ ሕዝቡ ቦይኮት በማድረጉ 18 ሰዎች ብቻየተገኙ ሲሆን ከ3 አመት በፊትም እንዲሁ ወደ ሚኒሶታ በመምጣት ኮንሰርት አዘጋጅታ ከ12 ያነሰ ሰው ብቻ በመገኘት በተመልካች ድርቅ ተመትታወደ ሃገሯ ተመልሳለች፤ ያሉት የመረጃ ምንጮች ሃመልማል ከስርዓቱ ጋር ያላት የጥቅም ግንኙነት የተረሳላት መስሎ ወደ አሜሪካ በድጋሚብትመጣም በዋሽንግተን ዲሲ 55 ሰዎች ተግኝተው አሳፍረዋታል። በዲሲ ኮንሰርት ሲዘጋጅ እስከ 5 ሺህ ሰው እንደሚገባ ልብ ይሏል።
ዲያስፖራው ከወያኔ ጋር በጥቅም የተሳሰሩ ድምጻዊያንን ቦይኮት ማድረጉ የሚያስመሰግን ነው የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች ይህ ጉዳይ በርትቶ ሊቀጥልእንደሚገባው አስታውቀዋል። እነዚሁ አስተያየት ሰጪዎች የስርዓቱ ደጋፊ የሆኑ አርቲስቶች በሃገር ቤት ከወያኔ ጋር በመሞዳሞድ የሚያገኙት ጥቅምውጭ ሲመጡ ሊያገኙ አይገባም ይላሉ። ዲያስፖራው ሃገሩን የሚያከብረውን አርቲስት እንደሚያክብረው ሁሉ ከወያኔ ጋር ለሆዱ ያደረውንድምጻዊም በማግለል ተመልካች አልባ ማድረግ እንደሚገባው አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።
https://www.zehabesha.com/amharic/archives/13614
No comments:
Post a Comment