በጅቡቲ መንገድ ላይ በአድማ ቆመው የነበሩ ከባድ መኪኖች ዛሬ ስራ ጀመሩ የካቲት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንዳንድ የከባድ መኪና ሾፌሮች ለኢሳት እንደገለጹት ከሶስት ቀናት በፊት አንድ ሾፌር እጅግ አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ መገደሉን ተከትሎ የተጀመረው አድማ ዛሬ ተጠናቆ መኪኖች መንቀሳቀስ ጀምረዋል።
የመንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን የሆኑት አቶ ካሳሁንና ኮሚሽነር ግርማይ ከሾፌሮች ጋር የተነጋገሩ ሲሆን፣ ገዳዩን አድነው እንደሚይዙት ቃል በመግባት ሾፌሮች ስራ እንዲጀምሩ መክረዋል።
ሾፌሮች በበኩላቸው ባልደረባቸው የተገደለበት ሁኔታ እጅግ አሰቃቂ መሆኑን በመግለጽ፣ ከእንግዲህ በነጻነት ተንቀሳቅሰው ለመስራት እንደማይችሉ ተናግረዋል። የመንግስት ባለስልጣናቱ በበኩላቸው አስፈላጊው ጥበቃ እንደሚካሄድ ቃል ገብተዋል።
የሟቹ አስከሬን በጸጥታ ሃይሎች ድጋፍ ወደ ትግራይ መላኩንም ሾፌሮች ገልጸዋል። የግድያው መንስኤም ሆነ የገዳዩን ማንነት መንግስት ይፋ አላደረገም።
No comments:
Post a Comment