Monday, March 10, 2014

ኢትዮጵያዊነት- ወንጀል፣ሀፍረት፣ውርደት.. ሆኗል።



በሆላንድና በጀመርመን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ቱርኮችና ሞሮኮዎች አሉ።ምዕራባውያኑ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የፈራረሱ
ከተሞቻቸውን መልሰው ሲገነቡ ለጉልበት ሥራ ቀጥረዋቸው ነው ያመጧቸው። እናም ላባቸውን ጠብ አድርገው በመስራት አገር አቅንተዋል። በመሆኑም በአገራቱን እንደ ሁለተኛ አገራቸው ያዩዋቸዋል። ተዋልደዋል፣በዘተዋል ፤ እንደቆይታቸውም በተለይ በሱቆችና በምግብ ቤቶች ኢንቨስትመንት በስፋት ተሰማርተው የተዋጣላቸው ነጋዴዎች ሆነዋል። ያኔ ጀርመኖች- እነ አከንን የመሣሰሉ በጦርነቱ የወደሙባቸውን ከተሞች መልሰው ሲገነቡ ኢትዮጵያውያንም በሥራው እንዲሳተፉ ተመሣሳይ ጥያቄ አቅርበው ነበር። ነገሩን እንደ ባርነት የተመለከቱት ቀዳማዊ ሀይለሥላሴ ግን፤- “ ህዘቤን ለከባድ የጉልበት ሥራ ወደ ባዕድ ምድር አልልክም” ብለው ሳይፈቅዱ ቀሩ። ያኔ-ኢትዮጵያ ዓለማቀፍ ክብርና ተሰሚነት ነበራት።ድህነትም እንዳሁኑ በሰው ላይ ጢብ ጢብ አይጫዎትም ነበር። ይልቁንም እንግሊዘ ውስጥ የጎርፍ አደጋ መድረሱን ተከትሎ መርከብ ሙሉ ቡና እስከመርዳት የደረስንበት ዘመን ነበር።ለትምህርትም ሆነ ለሥራ ወደ ውጪ ሀገራት የሚላኩ ኢትዮጵያውያንም ጉጉታቸው- ተልዕኳቸውን ጨርሰው ወደ አገራቸው መመለስ እንደነበር በባለቤቶቹ ተጽፎ አንብበናል፤ ሲነገር ሰምተናል።
ያኔ በህጋዊ መንገድ በአውሮፓውያኑ ለሥራ ስንጠየቅ የኮራነው ኢትዮጵያውያን እነሆ በመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች የሞግ ዘትነት እንጀራ ለማግኘት መከራችንን እናያለን። “ታፍራና ተከብራ..ነፃነቷን አስጠብቃ…”የኖረች አገር እነሆ ሀፍረቷ ተገላልጦና የሁሉም ማላገጫና መዘባበቻ ሆና ቀርታለች። ኢትዮጵያዊነት- ወንጀል፣ሀፍረት፣ውርደት.. ሆኗል።
አዎ! ተዋርደናል!በጣም ተዋርደናል፣ እጅግ ተዋርደናል!(እየነደደኝ)

No comments:

Post a Comment