ባለፈው ሐሙስ ከሰዓት ላይ አብርሃ ደስታ ወደ ፍርድ ቤት የሚቀርብበት ዕለት ነበርና በአራዳ ፍርድ ቤት ብዙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላትና አመራሮች እንዲሁም አድናቂዎቹ ተገኝተው ነበር። እንደተለመደው ብዙ ካስጠበቁን በኋላ የሰላማዊ ትግል ጀግናው አብርሃ ደስታ በብዙ ታጣቂዎች ታጅቦ መጣ! እጁ በሰንሰለት ታስረዋል፤ እኛም አላሳፈርነም፤ ቋንቋ ብሄር ሃይማኖት ሳይገድበን ለብዙ ሰዓታት ቆመን ጠበቅነው እና ሲመጣ እንደ ተለመደው በፍጮትና በጭብጨባ ተቀበልነው። ቀና ብሎ ሰላምታ ሰጠን! ሲገባ ሀዘን፣ መከፋት ተጫጭኖት ነበር፤ በእርግጥ በኋላ ከፍርድ ቤቱ ሲወጣ ለውጥ ነበረው፤ ፈግግ ለማለት ሞክረዋል። በእውነቱ ሳየው እንባዬ ነው የመጣው።
በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የሰውነት ለውጥ ታይቶበታል፤ ግርጅፍጅፍ ብለዋል። ነገሩ በጣም የሚያሳዝን አጥንት የሚሰብር ነው! ይሄ ልጅ የመሰለውንና ያመነውን ተናገረ ፃፈ በቃ ይሄ ነው ወንጀል ሆኖ እንዲህ ስቃይ እንዲቀበል ያደረገው። ለፍርድ ቤቱ በቃሉ እንዳስረዳው ከሆነ ከፍተኛ የሆነ ድብደባ በመርማሪዎቹ ተፈፅሞበታል፤ እንኳን መደብደብ ከፈለግን እንገድለዋለሀን እንደተባለም አስረድተዋል። ይሄ ሁሉ መረጃ አምጣ እኛ የምንልህን እመን ነው፤ መቼስ አስሮ ስለታሰርክበት ጉዳይ መረጃ ካንተ የሚፈልግ መንግስትና የፍትህ ስርዓት ነው ያለን! ስንቱ የህግ ልዕልና እና ሰብአዊ መብት እንዲያከብር ነው እንጂ እንዲህ ፖሊስና መርማሪ ለአንድ ስርዓት ባለው ፖለቲካዊ ወገንተኝነት ጥቃት የሚያደርስብህ ከሆነ ይሄ በቀል እንጂ ፍትህ ሊባል አይችልም።
No comments:
Post a Comment