Thursday, August 7, 2014

በሳምንቱ ከወያኔ ከድተዋል ከተባሉ መኮንኖች ውስጥ ሶስቱ 'ዎው' ከተባለ የደቡብ ሱዳን ከተማ ተይዘዋል።

በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የቀድሞ ሰራዊት (የደርግ) መኮንኖች ማህበር መስርተዋል።


በዚህ ሳምንት ውስጥ ከሰማናቸው አበይት ጉዳዮች ውስጥ አንዱ በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ የቀድሞ የደርግ መኮንኖች ተሰባስበው ማህበር በኒቫዳ ውስጥ እንደመሰረቱ ሲሆን የማህበሩ ተግባር ሃገርን ነጻ ማውጣት ይሁን አሊያም የመረዳጃ እድር እስካሁን አልታወቀም።
የደርግ ወታደሮቹ /መኮንኖች በተለያዩ የጦር ወንጀሎች የተሳተፉ እና አምባገነኑን ደርግ ሲያገለግሉ የነበሩ ሲሆን አሁን ከ እነሱ ስልጣኑን የተረከበው ወያኔም ከደርጎች ባልተናነሰ መልኩ ከባባድ የጦር ወንጀሎችን በመፈጸም ላይ ይገኛል። ለዚሁም በኦጋዴን እና በጋምቤላ ክልል የፈጸመው እንዲሁም በምርጫ 97 የወያኔ ኮማንዶ ጦር አግአዚ የፈጸመው ወንጀል ተጠቃሽ ነው።
በጦር ወንጀለኝነት በቀይ ሽብር ተዋናይነት የሚፈረጁት የደርግ መኮንኖች በሃገሪቱ ታሪክ ውስጥ ለአንድነት እና የውጪ ጠላትን አሳፍሮ በመመለስ ረገድ ሚና የተጫወቱ ቢሆንም ከወያኔ እና ሻእቢያ ጋር በመመሳጠር በገንዘብ ተደልለው ሃገሪቷን አሁን ላለችበት የወያኔ አውሬያዊ መንጋጋ እንዳበቋት የማይካድ ሃቅ ነው። አሁን አሜሪካን አገር መሰረትን የሚሉት ማህበር ስራው እና ተግባሩ በግልጽ ባይታወቅም ለዳግም የስልታን ጥም እንዳያገለግል ይህ ትውልድ ስጋት ሊያድርበት ቢችልም ጎን ለጎን በሃገሪቱ ላይ ለሰሩት ወንጀል ለመጠየቅ መሰባሰባቸው አመቺ መሆኑን የሚገልጹ አልጠፉም ከዚህም ጋር ተያይዞ ለሃገራቸው አንድነት እና ነጻነት አስታውጾ በማድረግ ሕዝቡን ሊያስደስቱ እና ሊክሱት እንደሚችሉም የሚናገሩ አሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በሳምንቱ እንደተሰወሩ የታወቁት 16 የወያኔ መኮንኖች ውስጥ ሁለቱ በደብረዘይት እስር ቢት ከመንገድ ታፍነው እንደተወሰዱ የገለጽን ሲሆን ወደ ደቡብ ሱዳን ገብተዋል ተብልው ከተጠረጠሩት አስረአንዱ ውስጥ ሶስቱ ዎው ከሚባለው የደቡብ ሱዳን ግዛት ታድነው መያዛቸው ታውቋል። የወያኔ ወታደራዊ ደህንነቶች ባደረጉት ክትትል በተሽለ የዶላር ክፍያ ለደቡብ ሱዳን ተቃዋሚ በአሰልጣኝነት ለመቀጠር ከአዋዋይ ደላሎች ጋር የተያዙት ሻለቃ ደምለው ታደለ (ጎጄ) ፣ ሻምበል ደረሰወርቅ ነጬ እንዲሁም ሻምበል ዋበላ እንድሪስ ከደቡብ ሱዳን ዋው ግዛት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል። በአሁኑ ወቅት የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚ ታጣቂ ሃይሎች በጥሩ ክፍያ አሰልጣኝ መክንኖችን ለማግኘት እየጣሩ መሆኑ ታውቋል ። ቀሪዎቹን ለማግኘት ፍለጋው መቀጠሉ ታውቋል።
‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

No comments:

Post a Comment