To breathe Democracy in Ethiopia , lets us fight together for our Freedom and Justice !!!!!
Wednesday, October 9, 2013
መንገድ ወድቆ አየሁት (ክንፉ አሰፋ)
መንገድ ወድቆ አየሁት (ክንፉ አሰፋ)
October 9, 2013
ርሃብ፣ ድካም እና ሰቆቃው ለላፉት 12 ወራት ተፈራርቀውበታል። አንዴ በሰሃራ በረሃ ሌላ ግዜ ደግሞ በሜዲትራንያን ባህር የሰው አእምሮ ሊቀበለው የማይችል ስቃይ አልፎ እግሩ አውሮፓን ምድር ከረገጠ እነሆ አንድ ሌሊት አለፈ። ሰነድ ገብረጻድቅ ይባላል። ፊቱ እጅግ ተጎሳቅሏል። ከሰውነቱ ላይ አጥንቶቹ ይቆጠራሉ።
ወጣቱ ተስፋ ወዳደረገባት የአውሮፓ ምድር ለመግባት የተነሳው ከአመት በፊት ነው። እንብርቱ የተቀበረችበትን ሃገር ተሰናብቶ ከወጣ ጀምሮ የደረሰበት መከራ ይህ ነው አይባልም። ሰነድን እመንገድ ወድቆ ነበር ያገኘሁት። ለጥቂት ደቂቃ አነጋገርኩት።Migrant sank in Italy
ከ 300 በላይ የኢትዮጵያውያ እና የኤርትራ ተወላጆች የፈጀው የላምፔዱሳ እልቂት በአለም አቀፍ ዜና እየታወጀ ባለበት ሰዓት፤ ሌላ መርከብ ከሊቢያ ተነስታ በጣሊያንዋ የጠረፍ ከተማ በሲሲሊያ ደረሰች። ይህች መርከብ 250 ዜጎችን ጭና ነበር። በዚህች መርከብ ላይ የሞተ ባይኖርም የአራት ቀን ጉዞው የአራት አመት ሰቆቃ ነበር የሆነባቸው። ይህች በርካሽ የተገዛች መርከብ የመጫን አቅሟ 120 ሰዎችን ብቻ ነው። ተጓዦቹ ርሃብና ጥማትን መቋቋም ነበረባቸው። እጅ እግራቸውም ለአራት ቀናት መተጣጠፉ የግድ ነው። እዚያው ይጸዳዳሉ። Migrant In Italy የሊቢያን ጠረፍ እንዳቋረጡ፤ ትልቅ ማእበል ተነስቶ መርከቧን አናወጣት። እናም መሃል መንገድ ላይ ቀጥ ብላ ቆመች። በሶርያ ሹፌሮች ወደሊቢያ ደውለው የህጻናትን ድምጽ ሲያሰሙ ካጣልያን እርዳታ ሊያገኙ እንደቻሉ ሰነድ አጫወተኝ።
የፖለቲካውና የኑሮ ሁኔታ አስገድዶት ስደትን የመረጠው ይህ ወጣት ጋር ባደረግኩት ቆይታ፤ በህይወት እዚህ መድረስ መቻሉ እንደትንግርት ነው የሆነብኝ።
ከሱዳን ተነስቶ ሊቢያ ለመግባት ሰሃራ በረሃን ማቋረጥ ነበረበት። የሰሃራ በረሃን ገሃነመ እሳት ተቋቁሞ ለ 21 ቀናት ተጓዘ። “እዚያ ህይወት ከንቱ ናት።” አለኝ ሰነድ። አብረው ከነበሩት ውስጥ ገሚሱ እዚያው በረሃ ላይ ቀርቷል። በሙቀቱ ብቻ ሰውነታቸው እየፈራረሰ የሞቱ ወገኖች አሉ። ከረጅም የእግር ጉዞ በኋላ ዳግሞ፣ በሁለት ላንድ ክሩዘሮች ተጭነው ተጓዙ። እሱ የነበረበት ላንድ ክሩዘር 125 ሰዎችን ጭኗል። መጫን ከሚገባው አራት እጥፍ መሆኑ ነው። Italy boat “እንደዶሮ ከላይ እና ከታች፤ አንዱ በሌላው ላይ እየተደራረብን ተጫንን” አለኝ። ወጣቱ ሲናገር የሃዘን ስሜት አላየሁበትም። ሃዘኑን ጨርሶ የደነዘዘ በድን አይነት ነው የሆነብኝ። በሰሃራ በረሃ የሞተ ሰው መቅበር ጨርሶ አይታሰብም። እያንዳንዱ ይህ ተራ ስለሚጠብቀው የሚወድቀው ወገኑን እያየ የራሱን ነፍስ ለማትረፍ ነው የሚጓዘው። በዚህ የነብስ አውጭኝ ስቃይ መሃል ሴት እህቶቻችን እንዴት እንደሚደፈሩ ነገረኝ። ይህንን ለመስማት እንኳን ይዘገንናል።
ከነሱ ቀድሞ የተጓዘው ላንድ ክሩዘር ሰዎችን እንደዋዛ እያንጠባጠበ በረሃውን እየሰነጠቀ ይነጉዳል። እነ ሰነድ የተጫኑበት ፒክ አፕ ደግሞ አስከሬኖቹን እየረገጠ ይከተላል።
ከበሽታው፣ ከረሃብና ጥማቱ፣ ከበረሃው ንዳድ እና ከመኪና አደጋው በተአምር አምልጠው ሊቢያ ሲደርሱ፤ ጠረፍ ላይ እስር ነበር የጠበቃቸው። ሰነድ ቤንጋዚ በምትባል የሊቢያ ከተማ ገንፉጣ ከተሰኘ እስር ቤት ውስጥ ተከረቸመ። ለአራት ወራት እዚያ እንደቆየ በደላሎች በኩል 1000 የሊቢያ ዲናር ጉቦ ከፍሎ ከእስር ሊወጣ እንደቻለ ነገረኝ።
በሊቢያ በግምት ከዘጠኝ ሺህ በላይ ስደተኛ እስረኞች አሉ። አብዛኞቹ ኤርትራውያን እና ኢትዮጵያውያን ናቸው። የሱዳን፣የግብጸና የማሊ ስደተኞች አይታሰሩም። በድንገት ከታሰሩም ዜግነታቸውን አረጋግጠው በነጻ ይለቀቃሉ።
ሰነድ ከእስር እንደወጣ በደላሎች አማካኝነት ወደመርከብ ጉዞ ተላከ። ይህንን እየሰሩ ያሉ፤ ሊቢያ ያሉ የአራት ደላሎችን ስም ጠራልኝ። መድህኔ፣ ራፉ፣ ኤርምያስ እና ያሲን። እነዚህ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ደላሎች ናቸው። ከዋናዎቹ የሊቢያ ደላሎች ጋር የሚያገንኙ ናቸው።
እነዚህ ደላሎች ዋስትና የሌለው (Use and throw) መርከብ በርካሽ ይገዙና ሰዎችን ከአቅም በላይ ይጭኑበታል።”እንደ እቃ ደራርበው ያስቀምጡናል።” አለ ሰነድ።
መርከቡ ጉዞውን ካጠናቀቀ ጣልያን – ሲሲሊ ላይ ያራግፍና እዚያው ይጣላል። የነ ሰነድ መርከብ የገባው ከላምፔዱሳው እልቂት በኋላ ነበር። ሲሲሊ እንደደረሰ እነሱን ያመጣው መርከብ እዚያው ተሰባብሮ ተጣለ። 120 ሰው መጫን የሚገባው የካምፐዱሳ መርከብ 500 ሰዎችን በመጫኑ ምክንያት ባህር ውስጥ ሰምጦ ቀረ። ሰነድ እዚህ ሊያገኛቸው ተስፋ ያደረገባቸው ጓደኞቹን ሁሉ እንዳጣ አጫወተኝ። Migrant sank in Italy በለፉት 6 ወራት ብቻ ከስምንት ሺህ በላይ ስደተኞች ከሊቢያ ተነስተው ማልታ ገብተዋል። ጉዞ ከጀመሩት ገሚሶቹ መሆኑ ነው። አሁንም 3000 የሚሆኑ ከሊቢያ እስር ቤት የወጡ ስደተኞች መርከብ እየጠበቁ ናቸው። እድለኞች ከሆኑ መርከቡ ወይ ጣልያን ያደርሳቸዋል፣ አልያም የሻርክ ምግብ ሆነው ታሪካቸው በሜዲትራንያን ላይ ይፈጸማል። Italy አቅራቢያዬ ከሚገኝ ስደተኞች የተጠለሉበት አንድ ህንጻ አምርቼ ነበር። እዚያም ከሶስጥ ቀናት በፊት የገቡ የኤርትራ ስደተኞችን አገኘሁ። አንደኛዋ ስደተኛ እዚህ በገባችበት ማእግስት መርዶ መጣ። አብሯት የተነሳው ወንድሟ በረሃ ላይ እንደወደቀ ተነገራት። ከሟቹ ጋር አብረው የነበሩ ሲናገሩ። “አሸዋ ውስጥ ቀብረነዋል። መቀብሩም ላይ ምልክት አድርገናል።” አሉ።
source http://daniboy8935.wordpress.com/
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment