To breathe Democracy in Ethiopia , lets us fight together for our Freedom and Justice !!!!!
Friday, October 25, 2013
በአዲስአበባ የውሃ ችግርን ተባብሶ ቀጥሎአል
ጥቅምት ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስአበባ ከተማ የውሃ ሽፋን 94 በመቶ ደርሶአል ቢባልም በአሁኑ ወቅት መሃል አዲስአበባን ጨምሮ አብዛኛው አዳዲስ የማስፋፊያ አካባቢዎች በቂ የውሃ ሽፋን የማያገኙት ከ40 በመቶ አይበልጡም።
የአዲስአበባ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ባለሰልጣን እንደሚናገረው የከተማዋ የውሃ ሽፋን እያደገ ቢመጣም ውሃን በቁጠባ የመጠቀም ልምድ ባለመዳበሩ እስከ40 በመቶ የሚደርስ ከፍተኛ ብክነት በከተማዋ ውስጥ አለ ብሎአል፡፡ ይህ ሁኔታም
ያለውን ውሃ በቁጠባ ለማዳረስ የሚደረገውን ጥረት ማስተጓጎሉን ጠቁሟል፡፡
የከተማዋን የውሃ እጥረት ለመቅረፍ በተያዘው 2006 በጀት ዓመት 6 ቢሊየን ብር ገንዘብ መመደቡን የአስተዳደሩ ምንጮች ጠቅሰው በዚህም ሥራ በቀን 110 ሺ ሜትር ኪዩብ የነበረውን ስርጭት ወደ210 ሺህ በማሳደግ ችግሩን
ለመፍታት ጥረት እንደሚደረግ ተወስቶአል፡፡
በተለያዩ የአዲስአበባ አካባቢዎች በየዕለቱ የመጠጥ ውሃ በአግባቡ የሚሰራጭ ባለመሆኑ ሰዎች ስራቸውን በመተው ጭምር ውሃ ፍለጋ ከቦታ ቦታ ሲንከራተቱና ለውሃ ማጓጓዣ ከፍተኛ ወጪ ሲያወጡ ማየት የተለመደ ሆኖአል፡፡ በአንዳንድ
አካባቢዎችም ውሃ በለሊት ይመጣል በሚል በርካታ ቤተሰቦች ውሃ በመጠባበቅ እንቅልፍ ሳይተኙ የሚያድሩበት ሁኔታ መኖሩ ይታወቃል፡፡
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment