To breathe Democracy in Ethiopia , lets us fight together for our Freedom and Justice !!!!!
Tuesday, October 29, 2013
ባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ሰራተኞቹን አባረረ , የንፋስ ሃይል ማመንጫ በስተጀርባ ሙስና መኖሩን መረጃዎች አመለከቱ
ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የባህር ዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ሰራተኞች ባለፈው ነሀሴ ወር ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ በፋብሪካው አስተዳደር ላይ ያላቸውን ቅሬታ ገልፀው ነበር፡፡ ቦርዱ እና ማነጅመንቱ ሰራተኞቹን በመሰብሰብ መልስ እንደሚሠጡ ቃል ገብተው የነበረ ቢሆንም፣ ቃላቸውን በማጠፍ በጥቅምት 15 ቀን 2006 ዓ.ም ሰራተኞቹን ለአመፅ አነሳስተዋል ተብለው የተፈረጁ 27 ሰራተኞች ከስራ አባረዋል ፡፡ በእለቱ የወጣው የማገጃ ደብዳቤ በፋብሪካው ስራ አስኪያጅ አቶ አባይ መላኩ ፊርማ የተጻፈ ነው።
የፋብሪካው ስራስኪያጅ ሰራተኞች መባረራቸውን አምነው ቁጥራቸው ግን 5 ብቻ ብለዋል፡፡ ስራ አስኪያጁ ሰራተኞቹ የተባረሩት ምንም እውቅና የሌለው ህገ ወጥ የስራ ማቆም አድማ ስላደራጁ ነው ብለዋልከአሸጎዳ
ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለትግራይ ክልል የኤሌክትሪክ ሃይል ያመነጫል በሚል በ210 ሚሊዮን ዩሮ ወይም በ5 ቢሊዮን 200 ሚሊዮን ብር ገደማ የተገነባው የአሸጎዳ የንፋስ ሀይል ማመንጫ 120 ሜጋ ዋት ሀይል በማመንጨት፣ በአዳማ ከተገነባው ከሁለት እጥፍ በላይ የሚበልጥ ነው።
ከ90 በመቶ በላይ በፈረንሳይ መንግስት የተሸፈነው ፐሮጀክት ሙስና እንደተፈጸመበት ከጸረ ሙስና ኮሚሽን የተገኘው መረጃ አመልክቷል።
የንፋስ አውታሮች ለሚቆሙባቸው ቦታዎች ከተወሰደው መሬት ጋር የማይጣጣም 95 ሚሊየን ብር ካሳ ተከፍሏል፡፡ በመሬት ግመታ እና ካሳ አወሳሰን ላይ የአካባቢው ባለስልጣናት እጅ ሰፊ እንደነበር የፊደራል የስነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሺን በጥናቱ ቢያረጋግጥም፣ እርምጃ ለመውሰድ የደፈረ ሰው የለም።
አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ፕሮጀክቱን ሲመርቁ ” ፕሮጀክቱ የመለስን ህያውነት” የሚያሳይ ነው ብለዋል።
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment