To breathe Democracy in Ethiopia , lets us fight together for our Freedom and Justice !!!!!
Friday, October 25, 2013
በኢትዮጵያ የሰሜን ኮርያ ዲፕሎማት በደቡብ ኮርያ ኢምባሲ ጥገኝነት ጠየቁ
ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም
በኢትዮጵያ የሰሜን ኮርያ ዲፕሎማት ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩ ኮርያዊ በደቡብ ኮርያ ኢምባሲ ጥገኝነት መጠየቃቸው ተገለጸ፡፡
ስማቸው ይፋ ያልሆነው ዲፕሎማት የሚወክሉትን ሀገር ትተው ከአንድ ወር በፊት የደቡብ ኮርያን መንግስት አዲስ አበባ በሚገኘው ኢምባሲ በኩል ጥገኝነት መጠየቃቸውን የተለያዩ የሁለቱ ኮርያዎች መገናኛ ብዙሀን በመዘገብ ላይ ናቸው፡፡ዲፕሎማቱ ወደ ደቡብ ኮርያ ኢምባሲ በመግባት ጉዞአቸውን እንዲያመቻችላቸው ጠይቀው ከአዲስ አበባ ወደ ደቡብ ኮርያ ማቅናታቸው ታውቋል፡፡ዲፕሎማቱ የሰሜን ኮርያ ኤምባሲ ውስጥ የንግድ ተወካይ ሆነው ሲያገልግሉ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡የሰሜን ኮርያ መንግስት በእርምጃው መበሳጨቱ የተገለጸ ሲሆን ደቡብ ኮርያ ግን ማረጋገጫን ከመስጠት ተቆጥባለች፡፡በየዓመቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ የሰሜን ኮርያ ዜጎች ወደ ደቡብ ኮርያ ይኮበልላሉ፡፡ከ25 ሺህ በላይ ሰሜን ኮርያውያን በደቡብ ኮርያ የሚገኙ ሲሆን ቻይናን እና ሌሎች ሀገራትን እንደ መሸጋገሪያ ይጠቀሙበታል፡፡ይሁንና የሰሜን ኮርያ ዲፕሎማት ወደ ደቡብ ሲኮበልሉ የተለመደ እንዳልሆነ ተነግሯል፡፡ኢሳት ዜና
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment