Monday, October 7, 2013

የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በግዴታ ስለ አክራሪነት እና ሽብረተኝነት ስልጠና እንዲወስዱ እየተደረገ ነው

የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በግዴታ ስለ አክራሪነት እና ሽብረተኝነት ስልጠና እንዲወስዱ እየተደረገ ነው መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት በ2006 ዓም ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ ባሉ የትምህርት ተቋማት ስለ አክራሪነት፣ ሽብርተኝነት እና ጸረ ሰላም ሀይሎች ትምህርት ለመስጠት የጀመረውን እቅድ በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጀምሯል። ከሁለት ሳምንት በፊት በክልል ለሚገኙ የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞችና መምህራን ስልጠናው በተሰጠበት ወቅት፣ በርካታ ተሳታፊዎች እድሜያቸው ከ15 አመታት በታች የሆኑ ተማሪዎች ስልጠናውን እንዳይወስዱ ጠይቀው ነበር። ባለፈው አርብ እና ቅዳሜ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቴክኖሎጂ ፋኩልቲ ተማሪዎች በአዲሱ የትምህርት ዘመን ለመመዝገብ ወደ ግቢ በገቡበት ሰአት፣ ምዝገባ ቆሞ ተማሪዎች ስድስት ኪሎ ወደሚገኘው የስብሰባ ማእከል እንዲያቀኑ ታዘዋል። ተማሪዎች ” ለምን?’ የሚል ጥያቄ ባነሱበት ወቅት፣ የዩኒቨርስቲ ሀላፊዎች ከመንግስት የመታ ትእዛዝ በመሆኑ ምንም ማድረግ አንችልም የሚል ምላሽ ሰጥተዋቸዋል። ተማሪዎች ከግቢ እንዳይወጡ በሩ የተዘጋባቸው ሲሆን፣ በቀረቡላቸው 2 አውቶቡሶች ተጭነው ስልጠናውን እንዲወስዱ ተደርጓል። መንግስት ለስልጣኑ አደጋ ይፈጥራሉ ብሎ የሚገምታቸውን እንደ ግንቦት7፣ ኦነግና ኦብነግ የመሳሰሉትን ድርጅቶች በጸረ ሰላምነት እና በአሸባሪነት ይፈርጃቸዋል።

No comments:

Post a Comment